Get Mystery Box with random crypto!

ለአስጎብኚ ድርጅት በሊዝ ፋይናንሲንግ የሚቀርቡ የተሸከርካሪ አይነቶች ባንኩ በሊዝ ፋይናንሲንግ | Development Bank of Ethiopia (DBE) : Training to Lease Financing

ለአስጎብኚ ድርጅት በሊዝ ፋይናንሲንግ የሚቀርቡ የተሸከርካሪ አይነቶች

ባንኩ በሊዝ ፋይናንሲንግ ስርአት ፋይናንስ የሚያደርጋቸው ለአስጎብኚነት አገልግሎት የሚፈቀዱ ተሸከርካሪዎች አይነት ካሁን ቀደም ስቴሽን ዋገን ተሽከርካሪዎችን ጭምር እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይሁንና ጥር 2015 ለልማት ፕሮጀክቶች እንዲውሉ ከቀረጥ ነፃ ወደ አገር የሚገቡ ተሸርካሪዎችን ዓይነትና ብዛት ለመወሰን በገንዘብ ሚኒስቴር በወጣው መመሪያ 942/2015 መሠረት ካሁን ቀደም አመልክታችሁ በሂደት ላይ ያላችሁም ሆነ አዲስ አመልካቾች በአስጎብኚነት ለመሰማራት በሊዝ ፋይናንሲንግ የብድር ስርአት ከባንኩ ማግኘት የምትችሉት የተሸከርካሪ አይነቶች 2 ሚኒባስ (ታጣፊ ወንበሮችን ሳይጨምር ከ10 ያላነሰ እና ከ16 ያልበለጠ መቀመጫ ያለው የሰው ማጓጓዣ ተሸርከርካሪ)፣ 2 ሚዲባስ (ታጣፊ ወንበሮችን ሳይጨምር ከ16 ያላነሰ እና ከ29 ያልበለጠ መቀመጫ ያለው የሰው ማጓጓዣ ተሸከርካሪ) እና 2 አውቶቡስ (ታጣፊ ወንበሮችን ሳይጨምር ቢያንስ 30 መቀመጫ ያለው የሰው ማጓጓዣ ተሸከርካሪ) መሆኑንና ስቴሽን ዋገን ተሸከርካሪዎች እንደማይካተቱ እንድታውቁት፡፡