Get Mystery Box with random crypto!

አራተኛ ዙር፣ ምዕራፍ ሁለት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ የሚያንቀ | Development Bank of Ethiopia (DBE) : Training to Lease Financing

አራተኛ ዙር፣ ምዕራፍ ሁለት

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ የሚያንቀሳቅሱና ለማንቀሳቀስ የተዘጋጁ እጩዎችን ለማሰልጠን ባደረገው ምዝገባ ከ400 ሺ በላይ ሰልጣኞች የተመዘገቡ ሲሆን በሶስት ምዕራፎች ከፋፍሎ ለማሰልጠን በወሰነው መሰረት በመጀመርያው ምዕረፍ 114 ሺ ቀ ሰልጣኞች እንዲሳተፉበት የተዘጋጀው ስልጠና ቅዳሜ በቀን 18/06/15 ከሰልጣኞች ለተነሱ ወሳኝ ጥያቄዎች በባንኩ ፕሬዚደንት ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) በተሰጡ አመርቂ ምላሾች ተጠናቋል።

ይህንን ተከትሎ ሁለተኛና ሶስተኛ ምዕራፍ ስልጠናዎች የሚሰጡበትን ጊዜ አስመልክቶ ጥያቄዎች እየቀረቡ እንደሆነ ታውቋል።

በመሆኑም ቀጣይ የ4ኛው ዙር ቀሪ ምዕራፎች/ስልጠናዎች መቼ እንደሚሆኑ ባንኩ ባሉት የሚዲያ አማራጮች የሚያስታውቅ ስለሆነ፣ እንዲሁም ለ2ኛው ምዕራፍ የምትመረጡ ሰልጣኞች ደግሞ በምዝገባ ወቅት ባስመዘገባችሁት ስልክ ቁጥር አማካኝነት ለስልጠናው መመረጣችሁን በቀጥታ እንድታውቁት ስለሚደረግ በትዕግስት እንድትጠብቁ እንጠይቃለን።