Get Mystery Box with random crypto!

Daily News 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ dailynews_et — Daily News 🇪🇹 D
የቴሌግራም ቻናል አርማ dailynews_et — Daily News 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @dailynews_et
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.84K

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-10-01 19:02:22 ጆ ባይደን አሜሪካ የኔቶን ግዛት “እያንዳንዱን ኢንች” እንደምትከላከል ፑቲንን አስጠነቀቁ!!

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፤ የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በኔቶ ግዛት ላይ ምንም አይነት ስጋት እንዳይፈጥሩ በጥብቅ አስጠንቅቀዋል።

"አሜሪካ እያንዳንዱን ኢንች የኔቶ ግዛት ለመከላከል ከኔቶ አጋሮቻችን ጋር ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅታለች፤ እያንዳንዱ ኢንች ፣ ሲሉም ተናግረዋል፡፡ “ሚስተር ፑቲን በተሳሳተ መንገድ እትረዳኝ ፤ እያንዳንዱ ኢንች ነው ያልኩት” ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

ወደ ሩሲያ የተቀላቀሉትን አዳዲሶቹን የዩክሬን ግዛቶች ለመጠበቅ ኒውክሊየር ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል የዛቱት ፑቲን ግዛቶቹ “ለዘላለሙ” የሩሲያ አካል መሆናቸው በይፋ ማወጃቸው ውጥረቱን እንዳያባብሰው ተሰግቷል፡፡ፑቲን ባለፈው ሳምንት ባደረጉት ንግግር አገራቸው “በርካታ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን መታጠቋን” ገልጸው፣ አስፈላጊ ሲሆን ያለንን አማራጭ ሁሉ እንጠቀማለን ብለዋል። ይህንን የምለው ለማስፈራራት አይደለም ሲሉም ተደምጠዋል።

በአዳዲሶቹ ግዛቶች ላይ የሚቃጣ ማንኛው አይነት ጥቃት በሩሲያ ላይ እንደተቃጣ ይቆጣራልም ነበር ያሉት ፕሬዝዳንቱ፡፡ ይህንንም ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሰጡት ምላሽ “ሀገራቸውም ሆነ አጋሮቿ በቭላድሚር ኃላፊነት በጎደላቸው የፑቲን ዛቻዎች የሚደናገጡ አይደሉም” ሲሉ ለክሬምሊን ባለስልጣናት ጠጠር ያለ መልዕክት አስተላለፍዋል።

የኔቶ ዋና ጸሃፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ የግዛቶቹን መጠቅለል “ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ የታየ እጅግ አሳሳቢው ክስተት” ነው ብለዋል።ግዛቶቿ ወደ ሩሲያ የተጣቀለሉባት ዩክሬን በአስቸኳይ የኔቶ አባል እንድትሆን ጥያቄ ያቀረበች ሲሆን፣ የሩሲያን እርምጃ የተቃወሙት የኔቶ አባላት ምን እንደሚወስኑ በቀጣይ ሳምንታት ይሚታወቅ ይሆናል።

@dailyNews_et @dailyNews_et
957 views16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 16:59:44
በአንድ ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የተገነባው የቆዳ ውጤቶች ማምረቻ ድርጅት ተመረቀ።

ፒሲኢ ቬንቸር ማኑፋክቸሪንግ በአዲስ ኢንዱስተሪያል ፓርክ ውስጥ በአንድ ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የገነባውን የቆዳ ውጤቶች ማምረቻ ድርጅት አስመርቋል፡፡

ፋብሪካው ከአንድ መቶ ሰማንያ በላይ ወጣት ወንድና ሴቶችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለ ሲሆን ከዚህ በፊት በትንሽ ቦታና በተወሰኑ ሰራተኞች ስራ ላይ እንደነበር ተገልጿል።

የኢንዱስትሪ ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል ባለሃብቶቹ ለመጀመሪያ ወደ ኢትዮጵያ አመጣጣቸው ለበጎ አድራጎት ስራ እንደነበር ጠቅሰው ለምን ለዜጎች የስራ ዕድል ፈጥረን በተለይ ደግሞ ሴቶችን የተሻለ የስራ ዕድል ኢንዲያገኙ ለምን አናደርግም በሚል ሀሳባቸውን ቀይረው ስራ መጀመራቸውን ተናግረዋል።

ድርጅቱ ሰፊ የስራ ዕድል በመፍጠርና በተለይ በቀጣይ አስር ዓመት ውስጥ ከዚህ ዘርፍ ብቻ እስከ አንድ መቶ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን አምርቶ ወደ ገበያ ለማስገባት አቅዶ እየሰራ በመሆኑ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

@dailyNews_et @dailyNews_et
1.5K viewsedited  13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 16:49:28
አራስ ልጁንና የ5 ወር ልጇን የገደለው ...

በዎላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ አንድ አባት የራሱን ህይወት ጨምሮ የሶስት ሰው ህይወት ማጥፋቱን ፖሊስ ገልጿል። ግለሰቡ የራሱን፣ የልጁንና የልጅ ልጁን ህይወት ማጥፋቱን ነው የከተማው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ወልዴ ጊሊሶ የገለጹት።

አቶ አምዴ ሙሳ የተባለው ይኸው ግለሰብ ከዚህ ቀደም አልፎ አልፎ ከባለቤታቸው ጋር አለመግባባትና ግጭት ይፈጥር እንደነበር መረጃዎች እንደምጠቁሙ አዛዡ አስረድተዋል።

ድርጊቱ የተፈጸመው 17/01/2015 ዓ.ም ረፋድ ላይ ሲሆን ወልዳ እቤት ውስጥ የተኛች የ28 ዓመት አራስ ልጁንና የ5 ወር ልጇን ገድሎ  ሲወጣ ግቢ ውስጥ ባለው ውሃ በትልቅ የውሃ ገንዳ ውስጥ በመግባቱ የግለሰቡ ህይወትም ማለፍ መቻሉን ተናግረዋል።

የወንጀሉን ምክንያት ፖሊስ በማጣራት ላይ እንደሚገኝም ምክትል ኢንስፔክተር ወልዴ ጊሊሶ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በስልክ አስረድተዋል።

ምንጭ: https://wolaitatimes.com/
@dailyNews_et @dailyNews_et
1.3K viewsedited  13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 16:19:27 የማድንጎ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ፡፡

መስከረም 17 ቀን 2015 ዓም ድንገት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው የአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ፍትሀተ የቀብር ሥርአት ዛሬ ስርዓተ-ቀብሩ ተፈጽሟል፡፡

ቀደም ሲል ዛሬ ከእኩለ ቀን ጀምሮ አዲስ አበባ በወዳጅነት መናፈሻ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የሙያ አጋሮቹ፣ አድናቂዎቹ እንዲሁም ወዳጅ ዘመድ በተገኘበት የስንብት ዝግጅት ተካሂዷል።

በ1990ዎቹ ብቅ ካሉት የጥበብ ሰዎች አንዱ የሆነውና በብዙዎች ተወዳጅነትን ያተረፈው አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ስለሀገር፣ ስለፍቅር፣ ስለባህል እና ታሪክን ጨምሮ የተለያዩ ጉዳዮችን የሚዳስሱ የሙዚቃ ሥራዎችን ለአድማጮቹ አቅርቧል።

በቅርብ የሚያውቁት ቅን እና መልካም ሰውነቱን የሚገልጹለት አርቲስት ማዲንጎ ባለትዳር እና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነበር። ነፍ

@dailyNews_et @dailyNews_et
1.2K viewsedited  13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 12:59:06
የአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ የአስክሬን ሽኝት መርሐ ግብር ከመኖሪያ ቤቱ ጀምሮ እየተካሄደ ነው፡፡

ከአርቲስቱ መኖሪያ ቤት ጀምሮ እየተካሄደ ያለው የአስክሬን ሽኝት መርሐ ግብር÷ በመቀጠልም በወዳጅነት ፓርክ በመንግሥት ባለስልጣናት፣ በሙያ አጋሮቹ፣ በአድናቂዎቹ እና ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት የአስክሬን ስንብት ይካሄዳል።

የተወዳጁ አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ የቀብር ሥነ ስርአት በመንበረ ጸባኦት ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል። ተወዳጁ የጥበብ ሰው ማዲንጎ አፈወርቅ ስለ ፍቅር፣ ትዝታ፣ ባህል፣ ሀገር፣ ታሪክና ሌሎች ጉዳዮችን የሚዳስሱ መልዕክቶችን በተስረቅራቂ ድምጹ በማዜም በኢትዮጵያ የኪነጥበብ ስራ ላይ የራሱን አሻራ አሳርፏል።

ማዲንጎ አፈወርቅ ኢትዮጵያ በተፈተነችበት ወቅት እያመመው ግንባር ድረስ በመሄድና ማሰልጠኛም ምልምሎችን በማነቃቃት የራሱ የሆነ ታሪክ የሰራ አርቲስት መሆኑም ይታወቃል። በቀድሞው የጎንደር ክፍለ ሀገር አዘዞ ተወልዶ በደብረታቦር ያደገው አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ መስከረም 17 ቀን 2015 ዓ.ም ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል።

@dailyNews_et @dailyNews_et
1.3K viewsedited  09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 19:55:12
በምዕራብ ሸዋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

የትራፊክ አደጋው ከኢንጪኒ ከተማ ወደ ሽኖ ከተማ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የህዝባ ማመላለሻ አውቶብስ ከተሳቢ ጋር ተጋጭቶ መከሰቱ ተገልጿል፡፡

በአደጋውም የ15 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ያለፈ ሲሆን፤ በ30 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በኹሉት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

@dailyNews_et @dailyNews_et
740 viewsedited  16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 07:18:34
ሰበር መረጃ

አርቲስት Dagne wale የጨነቀለት ከአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ቤት ወጦ ወደቤቱ በመሄድ ላይ እያለ ከምሽቱ 3 ሰዓት ባልታወቁ ሰዎች ከባድ ድ*ብ*ደባ ደርሶበታል ስልኩንም ወስደውበታል፡፡

@dailyNews_et @dailyNews_et
1.2K views04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 14:47:21
ተቋርጦ የነበረው የቪዛ ማራዘምና የመኖሪያ ፈቃድ እድሳት ተጀምሯል።

ከሐምሌ 18/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጦ የቆየው ቪዛቸዉ እና የመኖሪያ ፈቃዳቸው የሚፀናበት ጊዜ ከአንድ ወር በላይ ላለፈባቸው ግለሰቦች የቪዛ ማራዘምና የመኖሪያ ፈቃድ እድሳት ከመስከረም 16 2015 ዓ.ም. ጀምሮ አገልግሎቱን መስጠት መጀመሩን የኢፌዲሪ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል።

@dailyNews_et @dailyNews_et
1.4K views11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 14:15:11 #ጥቆማ!
የት.ወ.ሐ (የትግራይ ወ*ራሪ ሀይል) በጨለቆት ባይባዋ ቆባ ጠጠራ ወደ በርሓ ማሪያም ዛሬ ሌሊት ተጨማሪ ሀይል አስጠግቶ አድሯል። ይህ ሀይል በአምደአምባ እና በጎረንጎሮ አቅጣጫዎች ተኩለሽ ዲኖ አርበት ያለውን የወገን ሀይል ለማጥቃት ያሰበ ነው ተብሏል።

ድል ለወገን ጦር

@dailyNews_et @dailyNews_et
1.3K views11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 14:14:57
#ጥንቃቄ ይደረግ!

ይሄ ልጅ ከአማራ ልዩ ኃይል የያዘውን ድሽቃ እስከ ተተኳሹ ይዞ የከዳ ሰው ነው። ከከዳ በኋላም በተለያዩ የኦሮሞ ሚዲያዎች በመቅረብ በኦሮሞነቱ ጥቃት እየደረሰበት እንደሆነና ይሄን ጥቃትም ለመመከት የኦሮሞ ምሁራን የትጥቅ ድጋፍ እንዲያደርጉለት ሲጠይቅ የነበረ ሰው ነው።

ሰሞኑን ደግሞ ምሬ ወዳጆ የሚመራውን የምስራቅ አማራ ፋኖ እንደተቀላቀለ እየተነገረ ነው። ይሄ ሰው ምን አይነት ተልዕኮ ነው ይዞ የመጣው? በዘሬ ምክንያት ሲገፉኝ ነበር ሲላቸው ከነበሩ ሰዎች ጋር አብሮ ለመታገል ምን አነሳሳው? ጥብቅ ክትትል ይደረግ!

የሰጠውን ኢንተርቪው ስሙት!

@dailyNews_et @dailyNews_et
1.3K views11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ