2022-09-25 11:10:16
<<በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ግጭት በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት በሚደረግ የሰላም ድርድር ለመፍታት ቁርጠኛ ነን>> አቶ ደመቀ መኮንን
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው 77ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር
የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት በሚደረግ የሰላም ድርድር ለመፍታት ቁርጠኛ ናት፣
ከአፍሪካ ሕብረት ውጭ የሚደረግ ሌላ አካሄድ ተቀባይነት አይኖረውም፣
ኢትዮጵያ እየተገበረችው ባለው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በበርካታ ቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞች ተተክለዋል፣
ኢትዮጵያ ዘላቂነት ያለው የኢነርጂ ሽግግርና የአረንጓዴ እድገት እያስመዘገበች ነው፤ ይህ ተግባሯም እውቅናና ተግባራዊ ድጋፍ ሊቸረው ይገባል፣
አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ጠይቀዋል፣
አፍሪካዊያን ጥያቄያችን ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ሁልጊዜም ይህን ጥያቄ አጠናክረን እንቀጥላለን፣
የአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መሆን የሚችለው በፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ተገቢው ውክልና ሲኖራት ነው፣
ኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት በማኅበራዊ ፣ ምጣኔ ሀብትና በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ለውጥ አሰመዝግባለች፣
ኢትዮጵያ የዓባይን ግድብ በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ስር በሚደረግ የሦስትዮሽ ድርድር ጉልሕ ተፅዕኖ በማያደርስና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት መርህን መሰረት በማድረግ ልዩነቶችን ለመፍታት አሁንም ፅኑ አቋም አላት፣
ሁሉም አገራት የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቁ በካይ ጋዞችን ለመቀነስ ከአሁን በፊት የገቡትን ቃል ሊተገብሩት ይገባል፣
ዓለም በበርካታ ፈተናዎች እያለፈች ነው፤ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የከፋ ድህነት፣ ግጭት፣ ሽብርተኝነትና ጂኦ ፖለቲካዊ ሽኩቻዎች የባለብዙ ወገን የግንኙነት መድረክን እየፈተኑት መሆኑን ነው፣
የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና ለመከላከል አሰፈላጊውን ፋይናንስ መመደቡ ላይም በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ይገባናል፣
አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሆኑ በካይ ጋዝ ልቀት ያላት ድርሻ ከቁጥር የማይገባ ቢሆንም ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቁ በካይ ጋዟችን ለመቀነስ ግን የተለያዩ ስራዎችን እየከወነች ነው፣
የአየር ንብረት ለውጥ የሚያደርሰውን ጉዳት አስቀድሞ በመተንበይ በትብብር መስራት ይገባናል።
(ኢፕድ)
@dailyNews_et @dailyNews_et
1.5K views08:10