Get Mystery Box with random crypto!

አልሰራህም ማለት ነው! ፨፨፨፨፨////////፨፨፨፨፨ ካልተጠላህ፣ የሆነ ሰው ካልተቸህ፣ መነጋገሪ | ስነ-ልቦናዊ መፍትሔ

አልሰራህም ማለት ነው!
፨፨፨፨፨////////፨፨፨፨፨
ካልተጠላህ፣ የሆነ ሰው ካልተቸህ፣ መነጋገሪ ካልሆንክ በእርግጥም ምንም አልሰራህም ማለት ነው። ስራህ የሚያስወራብህ፣ የሚያነጋግር፣ መቀኞችህን የሚያናድድ፣ ወዳጆችህን የሚያስደስት መሆን ይኖርበታል። ልዩነት መፍጠሩን ከሃሳብ ትጀምራለህ፤ በተግባር ትደግመዋለህ። ከብዙዎች ጋር በተመሳሳይ እድገት ብታድግም ምርጫህ ግን ልዩነትን መፍጠር ይሆናል። አስተውሎትህ በጨመረ ቁጥር ውሎህ፣ አዳርህ፣ ጓደኛህ፣ ወዳጅህ ይቀየራል።

አዎ! ጀግናዬ..! አልሰራህም ማለት ነው! የማያውቅህ ሰው ያውራብህ፣ አለመቻልህን ይናገር፤ በማያገባው ይግባ፣ ብዙ ያውራ። ተፈላጊው ነገር እርሱ ነው። ካልተወራብህ የተለየ ነገር እንዳረክ በምን ታውቃለህ? ነቃፊዎችህ አይናቸው ካልቀላ፣ ዘወትር የቡና መጠጫ ካላደረጉህ፣ ያንተ ስራ ትልቅነቱ የቱጋር ነው? የጥላቻቸው ሌላኛው ትርጉም ምንድነው? እነርሱ ማድረግ የሚፈልጉትን ነገር ግን ያልቻሉትን አንተ ስላደረከው፣ ችለህ ስላሳየሃቸው ይጠሉሃል፤ ይጠየፉሃል። እርሱ ግን ላንተ ሃይል መሆኑን አያውቁትም፤ ቢያንስ ዝም ቢሉ ጥሩ ነበር ግን አይችሉም። ስለዚህ አንተም ለእነርሱ ሲሆን መስማቱን አትቻል፤ አትስማቸው።

አዎ! የሰው ምላስ ያስፈራል፤ "ምን ይሉኛል" ያሸማቅቃል። እንዲወራብህ ካልፈለክ፣ ስድቡን፣ ትቺቱን ነቀፋውን ከፈራህ ሃሳብህን ይዘህ፣ ህልምህን ታቅፈህ መቀመጥ ያንተ ምርጫ ነው። የፈጣሪ ተዓምር፣ የአምላክ ጥበብ ባንተ ላይ እንዲገለጥ ስትፈቅድ ብቻ ተዓምራቱን ታያለህ፤ ድንቅ ስራውን ትመለከታለህ። በስንት መድረክ ስትጠበቅ በትንሽ የመንድር ወሬ ተጠልፈህ ከወደክ አንተን ብቻ ሳይሆን ብዙዎችን የሚጠቅመውን ህልምህን ይዘህ ትጠፋለህ።

አዎ! እራስህን ተመልከት፤ ስለማን፣ ለምን፣ ስንቴ፣ በምን ጉዳይ በየቀኑ ታወራለህ? ትኩረትህ ነቀፋ ነው ወይስ ሙገሳ? ትቺት ነው ወይስ ምስጋና? የአዎንታዊነትህ ማሳያ ሙገሳ፣ ብርታትና ምስጋና ነው። በእራስህም ሆነ በሌሎች የማብጠልጠልንና ፅንፍ የወጣ ትቺትን አስከፊ ገፅ በሚገባ ተመልክተሃል። ወዳጅህ ሲደግፍህ ጠላትህ መውደቂያህን ሲያመቻች አይተህም ይሆናል። እናም ጠላትህን የሚያስደግጥ ወዳጅህን የሚያስፈነድቅ ግሩም ስራ ከመስራት ወደኋላ አትበል። ትቺት፣ ነቀፋና ዘለፋ ልማዱ የሆነ ሰው የለመደውን ያድርግ ዘንድ ተወው፤ አንተም ትልቁንና አስደማሚውን ህልምህን መኖርህን ቀጥል። አለማቆምህን ሲያይ ሁሉም ዝም ይላል፤ ከነቀፌታው ይገታል፤ ተስፋ አለመቁረጥህን፣ ብርታትህን ሲመለከት ስድቡን ያዝ ያደርገዋል፤ ውጤትህንም ሲመለከት መከተሉን ይጀምራል።

https://telegram.me/counselingA