Get Mystery Box with random crypto!

#የአእምሮ_ህመም_የማይመስሉ_የአእምሮ_ህመሞች ማህተመ ጋንዲ ከአንድ ሰው ጋር ይጣላል። ጥፋቱ የሰ | ስነ-ልቦናዊ መፍትሔ

#የአእምሮ_ህመም_የማይመስሉ_የአእምሮ_ህመሞች

ማህተመ ጋንዲ ከአንድ ሰው ጋር ይጣላል። ጥፋቱ የሰውየው ነው። ማህተመ ጋንዲ ይቅርታ ሊጠይቀው ይሄድና እግሩ ስር ይወድቃል። ሰውየው በእግሩ ፊቱን ይጠልዘዋል። ጋንዲ ጥርሱ ተነቃንቆ ደም በደም ይሆናል። ቀና ብሎ ሰውየውን እየተመለከተ "ወንድሜ ፊቴ እግርህን አልጎዳህም አይደል?" ብሎ ጠየቀው አሉ።

ብዙ ሰው ይህንን ታሪክ ሲሰማ "እንዴት ትሁት ሰው ነው?" ሊል ይችላል። አንዳንድ ሳይካትሪስቶች ደግሞ "Moral masochism" የሚባል ህመም እንዳይሆን ብለው ሊያስቡ ይችላሉ። ማሶኪዝም (Masochism) በፆታዊ ግንኙነት ወቅት ሲገረፉ ብቻ የደስታ ጥግ ላይ የሚደርሱ ሰዎችን ይገልፃል። የሞራል ማሶኪዝም ደግሞ በስቃይና በእንግልት ደስታ የማግኘት ስነ ልቦናዊ ክስተት ነው።

የጋንዲ ጉዳይ አከራካሪ ሊሆን ንችላል። ነገር ግን አንዳንድ ህመም የማይመስሉን ፀባዮች የአእምሮ ህመም ምልክት ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ከፍተኛ ጥንቃቄ፣ ስራ በጣም መስራት፣ ብዙ እቃ መግዛት፣ መኮላተፍ....ዝርዝሩ ረጅም ነው።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ከዶ/ር ዮናስ ላቀው
https://telegram.me/counselingA