2022-05-26 15:15:55
የአታክልት ኦሜሌት
vegetable omelet
አስፈላጊ ግብአቶች እና መጠናቸው
• 1 ½ ኩባያ ጥቅል ጎመን
• 1 ½ ኩባያ ብሮኮሊ
• ½ ሽንኩርት
• 1 ቲማቲም (12 ቼሪ ቲማቲም)
• 2 ትንሽ ቃርያ
• 2 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
• ½ ማንኪያ እርድ
• ½ ማንኪያ የኩመን ዱቄት
• ½ ማንኪያ ነጭ ሽንኩርት ዱቄት -
• ¼ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
• ¼ ማንኪያ ጨው
• 5 እንቁላል
አዘገጃጀት
• -በመጀመሪያ እትክልቶቹን በሙሉ በትንንሽ መክተፍ
• -ዘይቱን የሞቀ መጥበሻ ላይ ጨምሮ ሽንኩርቱን መጨመርና ትንሽ ማቁላላት
• -ቲማቲሙን ጨምሮ መጥበስ (ለ 1 ደቂቃ ማብሰል)
• -ጥቅል ጎመኑን ጨምሮ መጥበስ (ለ 3 ደቂቃ ማብሰል)
• -ሁሉንም ቅመሞች መጨመር (ጨው ሲቀር)
• -ለ ትንሽ ደቂቃ መጥበስ ( 1 -2 ደቂቃ ማብሰል)
• -ብሮኮሊውን መጨመር ( 1 ደቂቃ ማብሰል)
• ጨውንና ቃርያውን ጨምሮ እሳቱን ማጥፋት
• እንቁላሎቹን ሰብሮ ትንሽ ጨውና ቁንዶ በርበሬ መጨመር
• -የማይዝ መጥበሻ ላይ (non-stick pan) ትንሽ ዘይት እድርጎ ማሞቅ
• -መጥበሻው በደንብ ከጋለ በሁዎላ እንቁላሉን መጨመርና በመሃከለኛ እሳት ማብሰል
• -በማማሰያ ጥግ ጥጉን እየከፈቱ ያልበሰለውን እንቁላል ማዳረስ (እላዩ መጠጥ እስኪል)
• -የበሰለውን እትክልት የመጥበሻው ግማሽ ላይ መነስነስና የቀረውን ግማሽ እንቁላል እጥፎ አትክልቱን ማልበስና ከእሳት ላይ ማውጣት
• -መጥበሻውን ከድኖ ለ 2 ደቂቃ በእንፋሎቱ ማብስል
3.2K viewsSamri Asefa, 12:15