Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የደረጃ ጨዋታውን አሸነፈ፡፡ ============= | CBE NOOR ሲቢኢ ኑር

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የደረጃ ጨዋታውን አሸነፈ፡፡
=================

በታንዛኒያ አስተናጋጅነት ሲካሄድ በቆየው እና ዛሬ ፍፃሜውን በሚያገኘው የሴካፋ ክለቦች ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የደረጃ ጨዋታውን በማሸነፍ በ3ኛ ደረጃ አጠናቋል፡፡

ለዋንጫ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶት የነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን በግማሽ ፍጻሜው ከዩጋንዳው ሺ ኮርፖሬት ጋር ባደረገው ጨዋታ 2 ለ 1 ተሸንፎ ዛሬ ባደረገው የደረጃ ጨዋታ የሩዋንዳውን ኤኤስ ኪጋሊ 3 ለ 1 በመርታት ነው በ3ኛ ደረጃ ያጠናቀቀው፡፡

በጨዋታው የቡድኑ አምበል ሎዛ አበራ፣ አረጋሽ ካልሳ እና ሀሳቤ ሙሶ ጎል ማስቆጠር የቻሉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ሎዛ በ11 ጎሎች የሻምፒዮናው ኮኮብ ጎል አስቆጣሪ ሆና የመጨረስ ሰፊ እድል አላት፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻምፒዮናውን በ3ኛ ደረጃ በማጠናቀቁ የነሀስ ሜዳሊያ እና የ10 ሺ ዶላር ተሸላሚ ሆኗል።