Get Mystery Box with random crypto!

ደንበኞች ከአጭበርባሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ፡፡ ========================== | CBE NOOR ሲቢኢ ኑር

ደንበኞች ከአጭበርባሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ፡፡
==========================

ደንበኞች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያዘጋጃቸውን የሽልማት ፕሮግራሞች በመንተራስ የሌብነት ተግባር ከሚፈፅሙ አጭበርባሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ አሳሰቡ፡፡

ወደ ደንበኞች ስልክ ደውለው ሽልማት እንደደረሳቸው በመንገርና ገንዘብ እንዲያስገቡ በመጠየቅ ሌብነት የሚፈጽሙ አጭበርባሪዎች መበራከታቸውን አቶ አቤ ገልፀዋል፡፡

ባንኩ ወደ ደንበኞች ስልክ የሚደውልበት አጋጣሚ መኖሩን የተናገሩት አቶ አቤ፣ ነገር ግን ደንበኞቹ ወደ ባንኩ በአካል እንዲቀርቡ ወይም ሰነድ እንዲያቀርቡ እንጂ በስልክ ይህን አስገቡ ያን አስወጡ የሚለው ነገር እንደሌለ አስረድተዋል፡፡

ደንበኞች ከባንክ ነው በሚል ስልክ ሲደወልላቸው ከሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ምንም አይነት እርምጃ መውሰድ እንደሌለባቸው እና በስልክ መረጃ እንዳይሰጡ ያሳሰቡት አቶ አቤ፣ ይልቁንስ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም 951 ላይ በመደወል የመረጃውን ትክክለኛነት ማጣራት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሚሰጠው አገልግሎት ስልክ ደውሎ ምንም አይነት ክፍያ እንደማይጠይቅም ነው አቶ አቤ ያስገነዘቡት፡፡

በተጨማሪም ደንበኞች ሞባይላቸው ሲጠፋባቸው ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎታቸው እንዲቋረጥ ማስደረግ እንዳለባቸው አቶ አቤ አሳስበዋል፡፡