Get Mystery Box with random crypto!

CBE NOOR ሲቢኢ ኑር

የቴሌግራም ቻናል አርማ combankcbenoorofficial — CBE NOOR ሲቢኢ ኑር C
የቴሌግራም ቻናል አርማ combankcbenoorofficial — CBE NOOR ሲቢኢ ኑር
የሰርጥ አድራሻ: @combankcbenoorofficial
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.91K
የሰርጥ መግለጫ

CBE NOOR is the brand name given to the Interest Free Banking Services of Commercial Bank of Ethiopia. CBE offers full-fledged CBE NOOR Interest Free Banking Services in more than 1,800 branches at window level and in more than 109 dedicated branches.

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 14:57:33
ከውጭ ሀገር ገንዘብ ለማስላክ በርካታ አማራጮች......
59 views11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:25:32
በስህተት ወደ ሌላ ሂሳብ የገባ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ለባለቤቱ ተመለሰ።
===================

አቶ ሲሳይ ተስፋዬ በስልካቸው አንድ መልእክት ይደርሳቸዋል፡፡ በወቅቱ ሀሰተኛ መልእክት ስለመሰላቸው ብዙም ትኩረት አልሰጡትም፡፡ በጡረታ ላይ የሚገኙት አቶ ሲሳይ ዘመድም ወዳጅም ይህን ያደርጋል ብለው የሚጠብቁት ነገር ስላልሆነ በሂሳባቸው ብር 501,840.00 መግባቱን የሚናገረውን መልእክት ሀሰተኛ ነው ብለው አምነዋል፡፡

ከጥቂት ቀናት በኋላ ሂሳባቸውን በኤ.ቲ.ኤም ሲያዩ ግን እውነትም ብር 501,840.00 ወደ ሂሳባቸው ገብቷል፡፡ አቶ ሲሳይ በጡረታ ዘመኔ ያገኘሁት ሲሳይ ነው ብለው አልተደሰቱም፡፡ ይልቁንስ በስህተት የገባ ገንዘብ መሆኑ ስለገባቸው የገንዘቡን ባለቤት ማፈላለግ ጀመሩ እንጂ፡፡

ወደ ባንክ በመሄድ የሂሳብ ዝርዝር አስወጥተው ገንዘቡን ወደ ሂሳባቸው ያስገባውን ሰው ስም አገኙ፣ የውጭ ሀገር ዜጋ ነው፡፡ ስልኩን ከባንኩ ተቀብለው ደወሉለት፡፡ እውነትም በስህተት የገባ ገንዘብ መሆኑን አረጋገጡ፡፡ አስፈላጊውን ማጣራት አድርገው የገንዘቡ ትክክለኛ ባለቤት መሆኑን ሲያረጋግጡም ገንዘቡን በታማኝነት መለሱ፡፡

ገንዘቡ ህይወታቸውን ሊለውጥ ቢችልም ህሊናቸውን ግን ሊለውጥ እንደማይችል የተናገሩት አቶ ሲሳይ፣ ገንዘቡን ሲመልሱ የተሰማቸው ደስታ ወደር የለውም፡፡ የሰው ገንዘብ በፍፁም እንደማይፈልጉ እምነታቸው አድርገው የኖሩት አቶ ሲሳይ፣ አጋጣሚው የሚሉትን በተግባር ሆነው ያገኙበት ሆኖ ማለፉን ተናግረዋል፡፡

ገንዘቡ በስህተት ገቢ የተደረገበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን ቅርንጫፍም ለአቶ ሲሳይ ተስፋዬ ታማኝነት እና አራያነት ያለው ተግባር የምስጋና እና የአድናቆት ደብዳቤ ሰጥቷቸዋል፡፡
425 views10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 16:43:22
በታንዛኒያ አስተናጋጅነት ሲካሄድ በቆየውና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በ3ኛ ደረጃ ባጠናቀቀበት የሴካፋ ክለቦች ሻምፒዮና የቡድኑ አምበል ሎዛ አበራ በ11 ጎሎች የኮኮብ ጎል አስቆጣሪ ሽልማትን ወስዳለች፡፡

ሎዛ አምና ኬኒያ ላይ በተካሄደው ሻምፒዮና እንዲሁ በ13 ጎሎች ኮኮብ ጎል አስቆጣሪ እንደነበረች ይታወሳል፡፡
534 views13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 15:35:22
እንኳን ደስ አለን!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲቲ ትሬዠሪ እና ትሬድ ሶሉሽንስ ግሩፕ (Citi Treasury and Trade Solutions Group) ተሸለመ!
565 views12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:14:28
ደንበኞች ከአጭበርባሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ፡፡
==========================

ደንበኞች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያዘጋጃቸውን የሽልማት ፕሮግራሞች በመንተራስ የሌብነት ተግባር ከሚፈፅሙ አጭበርባሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ አሳሰቡ፡፡

ወደ ደንበኞች ስልክ ደውለው ሽልማት እንደደረሳቸው በመንገርና ገንዘብ እንዲያስገቡ በመጠየቅ ሌብነት የሚፈጽሙ አጭበርባሪዎች መበራከታቸውን አቶ አቤ ገልፀዋል፡፡

ባንኩ ወደ ደንበኞች ስልክ የሚደውልበት አጋጣሚ መኖሩን የተናገሩት አቶ አቤ፣ ነገር ግን ደንበኞቹ ወደ ባንኩ በአካል እንዲቀርቡ ወይም ሰነድ እንዲያቀርቡ እንጂ በስልክ ይህን አስገቡ ያን አስወጡ የሚለው ነገር እንደሌለ አስረድተዋል፡፡

ደንበኞች ከባንክ ነው በሚል ስልክ ሲደወልላቸው ከሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ምንም አይነት እርምጃ መውሰድ እንደሌለባቸው እና በስልክ መረጃ እንዳይሰጡ ያሳሰቡት አቶ አቤ፣ ይልቁንስ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም 951 ላይ በመደወል የመረጃውን ትክክለኛነት ማጣራት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሚሰጠው አገልግሎት ስልክ ደውሎ ምንም አይነት ክፍያ እንደማይጠይቅም ነው አቶ አቤ ያስገነዘቡት፡፡

በተጨማሪም ደንበኞች ሞባይላቸው ሲጠፋባቸው ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎታቸው እንዲቋረጥ ማስደረግ እንዳለባቸው አቶ አቤ አሳስበዋል፡፡
565 viewsedited  08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 18:15:43
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የደረጃ ጨዋታውን አሸነፈ፡፡
=================

በታንዛኒያ አስተናጋጅነት ሲካሄድ በቆየው እና ዛሬ ፍፃሜውን በሚያገኘው የሴካፋ ክለቦች ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የደረጃ ጨዋታውን በማሸነፍ በ3ኛ ደረጃ አጠናቋል፡፡

ለዋንጫ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶት የነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን በግማሽ ፍጻሜው ከዩጋንዳው ሺ ኮርፖሬት ጋር ባደረገው ጨዋታ 2 ለ 1 ተሸንፎ ዛሬ ባደረገው የደረጃ ጨዋታ የሩዋንዳውን ኤኤስ ኪጋሊ 3 ለ 1 በመርታት ነው በ3ኛ ደረጃ ያጠናቀቀው፡፡

በጨዋታው የቡድኑ አምበል ሎዛ አበራ፣ አረጋሽ ካልሳ እና ሀሳቤ ሙሶ ጎል ማስቆጠር የቻሉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ሎዛ በ11 ጎሎች የሻምፒዮናው ኮኮብ ጎል አስቆጣሪ ሆና የመጨረስ ሰፊ እድል አላት፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻምፒዮናውን በ3ኛ ደረጃ በማጠናቀቁ የነሀስ ሜዳሊያ እና የ10 ሺ ዶላር ተሸላሚ ሆኗል።
289 views15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:19:58
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባዘጋጃቸው 10ኛው ዙር “ይቆጥቡ፣ ይሸለሙ” እንዲሁም 21ኛ፣ 22ኛ እና 23ኛ ዙሮች “ይቀበሉ፤ ይመንዝሩ፤ ይሸለሙ!” መርሃ-ግብሮች ተሳታፊ በመሆን እደለኛ መሆን የቻሉ ደንበኞች ዛሬ ነሀሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም የብሄራዊ ባንክ ገዢ የተከበሩ ዶ/ር ይናገር ደሴ፣ የብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ፍቃዱ ድጋፌ፣ የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ገረመው ጋርጄ፣ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ሥነ-ስርዓት ሽልማታቸውን ተረክበዋል፡፡
378 views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 09:14:37
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ነሀሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም በ10ኛ ዙር “ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!” እንዲሁም በ21ኛ፣ 22ኛ እና 23ኛ ዙሮች “ይቀበሉ፤ ይመንዝሩ፤ ይሸለሙ!” መርሃ-ግብር ተሳትፈው ተሸላሚ መሆን ለቻሉ ደንበኞች ሽልማታቸውን ያስረክባል ፡፡

2 ባለ ሦስት መኝታ አፓርትመንቶች፣ 13 አውቶሞቢሎች፣ 36 ስድስት ሰዎችን የማሳፈር አቅም ያላቸው ባለ 3 እግር ተሸከርካሪዎች እና 90 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ለእድለኞች የሚተላለፉ ሽልማቶች ናቸው
445 views06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 14:20:22
553 views11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:33:36
ነገ ነሀሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም ለ10ኛ ዙር “ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!” እንዲሁም ለ21ኛ፣ 22ኛ እና 23ኛ ዙሮች የ “ይቀበሉ፤ ይመንዝሩ፤ ይሸለሙ!” መርሃ-ግብር ተሸላሚዎች ሽልማት የሚተላለፍበት መርሃ-ግብር በባንካችን አዲሱ የዋና መ/ቤት ህንፃ ይከናወናል፡፡
605 views07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ