Get Mystery Box with random crypto!

CNN News አማርኛ

የቴሌግራም ቻናል አርማ cnn_amharic1 — CNN News አማርኛ C
የቴሌግራም ቻናል አርማ cnn_amharic1 — CNN News አማርኛ
የሰርጥ አድራሻ: @cnn_amharic1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.77K
የሰርጥ መግለጫ

Do you enjoy reading this channel?
Perhaps you have thought about placing ads on it?
To do this, follow three simple steps:
1) Sign up: https://telega.io/c/cnn_amharic1
2) Top up the balance in a convenient way
3) Create an advertising post

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 22:02:18
የሸዋሮቢት ከንቲባ ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸው ተሰማ!

የሸዋሮቢት ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው  አሁን ከመሸ 3:00 ሰዓት አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ሀይሎች ጥቃት ተፈፅሞበት ህይወቱ እንዳለፈ መረጃዎች ያሳያሉ።

@cnn_amharic1
@cnn_amharic1
170 viewsedited  19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:36:11
አንድ ከፍተኛ አመራር ጠንቋይ ቤት ተያዙ !

አንድ የሰ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ አመራር የክልል፣የሰ/ሸዋ እና የደብረብርሃን ከተማ አመራር በጥቅሉ የ12 ከፍተኛ አመራሮች ስም ዝርዝርን ለጠንቋይ መስጠታቸውን የመረጃ ምንጮቻችን ነግረውናል። 

ጠንቋዩ በደብረብርሃን ከተማ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ሲውል የአመራሮችን ዝርዝር ይዞ እጅ ከፍንጅ በመያዙ ተጠርጣሪው የሰ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ አመራር ለ4 ሰዓት ያክል በእስር ከቆዩ በኋላ ድርጊቱን መፈፀማቸውን አምነው ከእስር ተለቀዋል።  

ድርጊቱ ኋላቀር እና አፀያፊ በመሆኑ የሰ/ሸዋ ዞን አስተዳደር ይሄንን ድርጊት ፈፅመዋል የተባሉትን የዞኑ ከፍተኛ አመራር ከስራ አግዷል። 

ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም ይባል የለ!

@cnn_amharic1
@cnn_amharic1
323 viewsedited  17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:49:59
አሳዛኝ ዜና!

ቦሌ አራብሳ ኮንዶሚንየም በሰራተኛው የተገደሉ ሁለቱ ህፃናት!

በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ቦሌ አራብሳ ኮምዶሚኒየም በሁለት ህፃናት ላይ የተፈፀመው የግድያ ወንጀል፤ የተፈፀመው ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ ነው፡፡በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ በምትሰራ ወንጀል ፈፃሚ አማካኝነት ክርስቲያን መላኩና ወንጌላዊት መላኩ የተባሉ የሁለት ዓመትና የሶስት አመት ህፃናት በስለት ተወጋግተው ህይወታቸው አልፏል፡፡

የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮምሽን ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ እንደተናገሩት ወንጀል ፈፃሚው በቁጥጥር ስር ውላለች፡፡የህፃናቱ ህይወት በወንጀል ፈፃሚዋ እንዴት እንዳለፈና ሌሎችንም መረጃዎች ፓሊስ ተጨማሪ መረጃ እያጣራ እንደሚገኝ እና ህብረሰተቡም እንዲረጋጋም ም/ ኮማንደር ማርቆስ አደራ ብለዋል፡፡

@cnn_amharic1
@cnn_amharic1
301 viewsedited  16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 15:23:44
በማዕከላዊ እዝ የሚመራው የሰቆጣ ግንባር ጥምር ጦር ለአመታት የገነቡትን ምሽግ እየሰባበረ ለመቀሌ ከ50 ኪሜ ያልበለጠ ርቀት ያላችን ከአበርገሌን ከተማ አለፍ ብላ የምትገኘውን #የዛካ ከተማን ተቆጣጥሯል።

@cnn_amharic1
@cnn_amharic1
419 viewsedited  12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 14:21:44
የትግራይ ኃይሎች ከአማራ ክልል እንዲወጡ የብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጠየቁ

የትግራይ ኃይሎች በአማራ ክልል የጀመሩትን ውጊያ አቁመው ወደ ትግራይ ክልል እንዲመለሱ የብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ጠየቁ። ሚኒስትሯ በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ኃይሎች ክልሉን ለቀቅው መውጣት አለባቸው ብለዋል።

ቪኪ ፎርድ ይህን ያሉት የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና የኢትዮጵያ መንግስት ኃይሎች ዳግም ወደ ግጭት መመለሳቸውን በተመለከተ ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 26፤ 2014 ባወጡት መግለጫ ነው። ሁለቱ ኃይሎች እንደገና ወደ ግጭት መግባታቸው ለኢትዮጵያ ህዝብ “መከራ የሚያመጣ” ነው ያሉት የብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር፤ በክስተቱ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸውን የማጣት አደጋ እንደተጋረጠባቸው ገልጸዋል።

በሁለቱ ኃይሎች ውጊያ ምክንያት በቀጥታ ከሚደርሰው የሰዎች ሞት ባሻገር፤ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ የሚገኘው ሰብዓዊ ሁኔታ በግጭቱ ምክንያት ይበልጥ ስለሚባባስ የሰዎችን ሞት ሊያስከትል እንደሚችል ፎርድ በመግለጫቸው ጠቁመዋል። የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት በትግራይ፣ በአማራ እና አፋር የሚገኙ 13 ሚሊዮን ሰዎችን የሰብዓዊ እርዳታ ፈላጊ እንዳደረጋቸው ያስታወሱት ሚኒስትሯ፤ የአሁኑ ውጊያ እና በህወሓት የተያዘው የዓለም የምግብ ድርጅት ነዳጅ፤ የሰብዓዊ ድርጅቶችን ስራ “ይበልጥ አስቸጋሪ ያደርገዋል” ብለዋል።

የብሪታንያ መንግስት፤ ህወሓት የያዘውን ነዳጅ ለእርዳታ ማከፋፈል እና ለሌሎች አንገብጋቢ አገልግሎቶች እንዲውል እንዲያደርግ ጥሪ ያቀርባል ሲሉም የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትሯ አክለዋል።

@cnn_amharic1
@cnn_amharic1
421 viewsedited  11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 14:14:24

@cnn_amharic1
@cnn_amharic1
369 viewsedited  11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 13:56:00
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ በወረዳ 07 ልዩ ቦታው ቤተል ትምህርት ቤት ጀርባ በተባለ አካባቢ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በአንድ የመጋዘን ህንፃ የእሳት አደጋ መከሰቱ ተገልጿል።

@cnn_amharic1
@cnn_amharic1
369 viewsedited  10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 13:06:59

@cnn_amharic1
@cnn_amharic1
357 viewsedited  10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:48:26
ሕወሐት ወረራውን እያስፋፋ መጮኹን ቀጥሎበታል - የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት

ሕወሐት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ገፍቶ በየአቅጣጫው በለኮሰው እና ዛሬም እያስፋፋ ባለው እሳት ንጹሐን እየተገደሉ ነው፣ ሕዝብ እየተፈናቀለ፣ ንብረትም እየወደመ ነው።

አሁን እንደሚታየው አሸባሪውን ሕወሐት ከሀገር አጥፊነት ተግባሩ የማስቆም ግዴታ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ላይ ወድቋል።
ምክንያቱም:-
1. የሽብር ቡድኑ ሰላማችንን እንዳያደፈርስና ሀገራችንን እንዳያፈርስ መከላከል ስለሚገባ፤
2. ሕወሐት ወደ ትግራይ የሚላከውን ርዳታ ለተቸገረው ሕዝብ እንዳይደርስ፣ በተቃራኒው ርዳታው ለጦርነት እንዲውል እያደረገ በመሆኑ መንግሥት ርዳታው ለተረጂው ሕዝብ እንዲደርስና ትግራይ ውስጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ሕዝቡን ከችግር የመከላከል ግዴታ ስላለበት፤
3. ሕወሐት በእኩይ ተግባሩ ሕዝብን በረሃብ ለመቅጣት ዐቅዶ ተደጋጋሚ ጦርነት የሚከፍተው በክረምት የግብርና ወቅት በመሆኑ መንግሥት ወረራውን እየተከላከለ ያለው ሕዝብን ከረሃብ የማዳን ግዴታ ስላለበት ጭምር ነው።

ይሁንና በሕወሐት የሽብር ቡድን እየደረሱ የሚገኙ ጥፋቶችን ለማስቆም መንግሥት ለሰላማዊ አማራጭ ያደረጋቸው ጥረቶች ሁሉ እየመከኑ ባሉበት ሁኔታ፣ አሸባሪውን ሕወሐት መጫን ሲገባቸው "ሁለቱም ወገኖች" በሚል የሚወጡ መግለጫዎች ከእውነታው ያፈነገጡ በመሆናቸው ተቀባይነት የላቸውም።
በመሆኑም ሕወሐት ተደጋጋሚ የሰላም አማራጮችን በመግፋት የከፈተው ጥቃት ሃገራችንን እንዳይበትን፣ የመከላከያ ኃይላችን በሁሉም አቅጣጫ የተከፈተበትን ወረራ ከሰላም ወዳዱ ደጀን ሕዝብ ጋር በመሆን በጽኑ ጀግንነት በመከላከል ላይ ይገኛል።
ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት

@cnn_amharic1
@cnn_amharic1
377 viewsedited  08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:47:10

@cnn_amharic1
@cnn_amharic1
345 viewsedited  08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ