Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፵፭ @yanetmasra በ | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፵፭
@yanetmasra

በነጋታው ጠዋት የእናቴ አሰሪ የሆነችው ሴትዬ ከባለቤቷ ጋር በግ ይዘው ሊጠይቆት መጡ ። ይመስለኛል የተሠበረ ሰው እንዲጠገን የስጋ ተዋፅኦ የሆኑ ምግቦች መመገብ አለበት ከዛ ስለጤንነቷ ጠይቀው እንዲሻላት የልብ ምኞታቸውን ገልፀው በሌላ ጊዜ እንደሚጠይቋት ተናግረው ወጡ ። አንዳንድ ጎረቤቶቻችንም ከቤታችን አልጠፉም ፤ በጉ ከታረደ  በሗላ ከታረደ በሗላ ለቆንጣ ተዘልዝሎ መዘጋጀት ስለነበረበት ይህን ያደረጉት የበሱፈቃድ እናት ነበሩ ። ለእናቴ ምሳ ሰርተው እንድትበላ አቀረቡላት ፤ ምግብ ግን እስከዚም ሆና ስለነበር ለአመል ይህል ቀመስ ቀመስ አርጋ ብቻ ተወችው ገና ህመሟን በማስታመም ላይ ነበረች ። ህመም ለካ ሰውም  ያስጠላል እንዲሉ ለማናችንም ግድ አልነበራት ፤ ለነገሩ እውነቷን ነው የሰው ልጅ ጤና ከሌለው ምንስ ያስደስተዋል ? ዝም ብሎ የሚያዳምጠው ህመሙን ነው ።
   ከጥቂት ቀናት በሗላ ዱላ መጣላት እና በእሱ እቤት ውስጥ እንድትንቀሳቀስ ተደረገ ብዙ ጊዜ እኔ ነበርኩ እንድትንቀሳቀስ የማግዛት ታድያ በዚህ ምክንያት ከትምህርት ገበታዬ ብዙ ጊዜ መጓደል ጀመርኩ ይሄ ያሳሰባቸው የበሱፈቃድ ቤተሰቦች ብዙ ጊዜ ለትምህርት ትኩረት እንድሰጥ እና የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና ወሳጅ እንደሆንኩ አበክረው በመደጋገም ይነግሩኛል ግን ምን ላርግ ማን አጋዥ አለን ? ወይስ እኔ ልማር እናንተ ቅሩና እናታችንን ጠብቁ አልላቸው እህቶቼን በዛ ላይ የሰው ወከባ እየበረደ እየረገበ ጭራሹን ዝር የሚል ጠፋና ከደጅ ሆኗል " ደህና ዋልሽ ? ፣ በጎ ነሽ ?       ፣ እናትህ ተሻላት ? ፣ እግዚአብሔር ይማርሽ ። " የሚሉትን ቃላት ብቻ ሰንዘር ሰንዘር አድርገውልን የሚሄዱት



እግዚአብሔር በደህና ጊዜ የሰጠኝ እነ በሱፈቃድን ነው ።ቤተሰብ ሆነውናል ምንም እንኳን እናቴ እያገገመች ስትመጣ የነሱን መምጣት ባትፈልገውም ከጎዳቸው እያካፈሉ እኔና እህቶቼን የሚመግቡ እነሱ ናቸው ግን የነገሮች አካሄድ እየጣመኝ አልመጣም እናቴ እንደሆነች እደጅ ወጥታ መስራት እንደማትችል ግልፅ ነው ስለዚህ ያለኝ ምርጫ እነበሱፈቃድ ጋር መኖር ከጀመርኩ በሗላ ያቆምኩትን የጫማ መጥረግ ስራ ድጋሚ መስራት ነው ከትምህርት ስመለስ ባለኝ ጊዜ ይህን መስራት አለብኝ ይብቃም ይነስ የቤተሰቦቼን ቀዳዳ በጥቂቱም ቢሆን  ሊሸፍን ይችላል የሰው ፊት ማየት በጣም ከባድ ነገር ነው ። ልክ እንደ እሳት ይለበልባል ። ለነገሩ መስራቴን የውዴታ ግዴታ የሚያደርገው አልሰራም ብዬ ብቀመጥ ማን ይረዳናል ወይ ልመና ወይ ጎዳና ነው እጣችን እቴቴና ጋሼም ካላቸው ቁራሽ ላይ እየቆረሱ ለኛ መስጠት ለነሱ ከባድ እንደሚሆንባቸው አውቃለሁ ምንም እንኳን እነሱ ለመስጠት ባይሰስቱም

   እህቶቼ ቢያዝኑልኝምና ቢረዱኝም እንደኔ ግን ስቃይን እንዲያዩ አልፈልግም ሌላው ቢቀር ትምህርቴን አቁሜ ሌላ ስራም እየሰራሁ ቢሆን ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉና ከሰው በታች የመሆን ስሜት እንዲሰማቸው አልፈልግም ። በእናታችንም ህመም ምክንያት በጣም አዝነውና ተጎድተዋል ምንም እንኳን ባዝንና ብከፋም እነሱን ማበርታት ስላለብኝ የጠነከርኩ መስዬ አጠነክራቸዋለሁ ከፍቅርተ በላይ መሠረት ነገሮችን መቋቋም አትችልም ትንሽ ነገር ያስደስታታል ደሞ ትንሽ ነገር ይሰብራታል  ባይሆን ፍቅር በተፈጥሮዋ አስተዋይ እና ብልህ ስለሆነች ነገሮችን በፅሞና ከማሰቦ በፊት ተስፋ በመቁረጥ ለመሠበር አትቸኩልም ....ይቀጥላል
#share

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur