Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፵፬ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፵፬
@yanetmasra

እደጅ ከተሰበሰቡት ሰዎች መካከል አንደኛዋ ሴትዬ ወደውስጥ ገብታ ወደኔ ተጠጋች ፤ ከገፅታዋ ልታናግረኝ ፈልጋ መሆኑን ተረድቻለሁ " አንተ ነህ ልጇ  " አለቺን በአገጮ እናቴን እየጠቆመች " አዎ እኔ ነኝ ወንድ ልጇ " አልኳት ከዛ ልታወራኝ ስለፈለገች እደጅ ብቻዬን ይዛኝ ወጣች " ልጄ እኔ የእናትህ አሰሪ ነኝ የኔን ልብስ ለማስጣት ስትንጠራራ ነው የወደቀችው ስለዚህ ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም ልላችሁ አልችልም እኔም ልጆች እና ቤተሰብ አለኝ በዛ ላይ አባታችሁ እንደሞተም አውቃለሁ ስለዚህ እናታችሁ እስክታገግም የቻልኩትን ላግዛችሁ እጥራለሁ ያው ትረዳኛለህ ብዬ አስባለሁ እኔም የቤት እመቤት ነኝ ከትዳሬ ቀንሼ ነው የማካፍላችሁ ማረግ ከምችለው በላይ ግን ማድረግ አልችልም " አለቺኝ እንዲህም ደግ መሆኗ አስገርሞኛል አያገባኝም ብትል ማን የሚጠይቃት አለ ገፍትራ አልጣለቻት ብቻ " ቀጣዩን እግዚአብሔር ያውቃል ስለመልካም ሀሳብሽ  እግዚአብሔር ይባርክልኝ አመሠግናለሁ " አልኳት " በል እንግዲህ በርታ በል ያለሀት አንተ ነህ የሚረዳም የቅርብ ዘመድ ያላችሁ አልመሰለኝም " አለቺኝ " አዎ ልክ ነሽ የኛ የምንለው የሚረዳን ዘመድ ቀርቶ ወዳጅም የለንም አባቴ ሲቀር ሁሉም ቀርተዋል ከጎናችን ያለው እግዚአብሔር ነው ። አሁን ቁምነገሩ የእናቴ ደህና መሆን ነው ብቻ ጤናዋን ይመልስላት የአካል ጉዳት ከደረሰባት እንዴት ነው የምት... " ቃላቱን መቀጠል ተስኖኝ እንባ ቀደመኝ " እንዴ ኧረ  አታልቅስ በለቅሶ እኮ የሚሆን ምንም ነገር የለም ፤ በርታ ብለህ ተፅናና ደሞ የምን መጥፎ መጥፎ ነገር ማረብ ነው ትድናለች " አለቺኝ ምናለ እንደ አፏ ባደረገልኝ ብዬ ተመኘሁ 



ወደነበሱፈቃድ ጋር ተመልሼ በመሄድ ሁኔታውን ነገርኳቸው በጣም በማዘን " ዩሀንሴ ምንም እንዳትጨነቅ እኛም የምንችለውን ነገር በማድረግ እናግዝሀለን እግዚአብሔር እናትህን እንዲምራት እንፀልይልሀለን " አለቺኝ እቴቴ ፤ የነሱ ማፅናናት ብርታትን ሰጠኝ ማንኛውም ችግር የከፋ ቢሆንም በችግርና በመከራ ሰአት ደሞ ብቻን እንደመሆን ምንም የሚያስከፋ ነገር የለም ። ወደ እናቴ ቤት ስመለስ እቴቴ እና ጋሼ አብረውኝ ሄዱ ።  አንዳንድ የነበሩ ጎረቤቶቻችን በግልምጫ ተቀበሏቸው ፤ የሰው ቤት ነው ብለው እንጂ ከሁኔታቸው አንፃር  ቢያስወጧቸው እራሱ ደስታቸው ነበር ። እናቴ ለራሷ የውስጧን ህመም  እያዳመጠች መምጣታቸውን ብታይም ከቁብም አልቆጠረቻቸው ሁለቱ እህቶቼ ብቻ ፈገግ ብለው ከመቀመጫቸው በመነሳት አክብሮታቸውን ገለፁላቸው ። የእናቴ ነገር ማቃሰት ብቻ ሆነ የተሰበሰቡት ሰዎች የባጥ የቆጡን ያወራሉ የርዕሱ መነሻ የእናቴ መታመም ቢሆንም ስንቱ ቤት ውስጥ ስንቱ ነገር ውስጥ እየገቡ በወሬ አዳረሱት እነ ጋሼን ሰው የሚላቸው ስለጠፋ ካጠገባቸው ተቀምጬ ላወራቸው ሞከርኩ ሀሳቤን ግን መሰብሰብ ተስኖኝ ነበር በቃ እኔ እኔን አልነበርኩም  " እቴት በቃ እናንተ ሂድ ምንም አታደርጉም ባይሆን ነገ ትመጣላችሁ እኔ ግን በዚህ ሰአት ግዴታ መኖር ስላለብኝ እዚህ ነው የማድረው ቢያንስ እስኪሻላት " አልኳት  " እንዴ መጠየቅም አይገባህ ፤ እናትህ አይደለች ሲሆን ሲሆን እኮ አብረህ መኖርም ይገባህ ነበር የተፈጠሩ ክፍተቶች አልደፈን አሉ እንጂ ፤ ደሞ እራትም ያላችሁ አልመሠለኝ ናና ያዘጋጀሁት ነገር አለ ወስዳችሁ ቀማምሱ " አለቺኝ ነገርግን ቀን ላይ የእናቴ አሰሪ የሆነችው ሴት ለእህቶቼ ብላ ምሳ ላይ የሰራችው ምግብ ስላላለቅ ሌላ ስለማያስፈልግ እንዳለና ሳይጨነቁ ወደ ቤት እንዲሄዱ ነገርኳቸው ....ይቀጥላል
#share

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur