Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፵፫ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ
ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፵፫
@yanetmasra

አንድ የቀን ክፉ የሆነ ቀን እቤት ሆኜ ሳለሁ ፍቅር እየተንደረደረች መጥታ " እማዬ እማዬ " አለቺኝ እንባ ያረገዘው አይኗ መንታ መንታውን እየወለደ ። ከመቀመጫዬ ተስፈንጥሬ ተነስቼ በእንጥልጥል ያቆመችውን ወሬ እንድትቀጥልልኝ " ምን ሆነች ? " ብዬ አፈጠጥኩባት እየበረረች እንደመጣችው በፍጥነት ከመናገር ይልቅ ተጠምጥማብኝ እዬዬዋን አስነካችው እሶን ላባብል ወይስ የእናቴን ሁኔታ ልወቅ አይምሮዬ ተበረዘ ፤ በጣም ደነገጥኩ ፤ ተረጋግታ እንድትነግረኝ በብዙ ጣርኩ ነገር ግን አንድ ቃል ሳታወጣ ቀረች አማራጭ ሳጣ እዛው ትቻት ወደቤት በፍጥነት ሄድኩ አንድ አራት ሰዎች ቤታችን አካባቢ ይታዩኛል እናቴ ግን አልነበረችም በዛን ሰአት ልቤ ያሰበው በጣም ክፉ ክፉ ነገር ነበር በህይወት የማገኛትም አልመሠለኝ ። በሩ ላይ የተሰበሰቡትን ሰዎች ከመገፍተር ባልተናነሰ ሁኔታ አልፍያቸው ከቤት  ስገባ መኝታዋ ላይ እንደተጠቀለለች እንቅልፍ እንዲወስዳት ትታገላለች በህይወት ስላገኘሗት ደስ ቢለኝም " ግን ምን ሆና ነው ? " ብዬ አጠገቦ የተቀመጡትን ጎረቤታችን ወይዘሮ ብርቄን ጠየቅኳቸው " የምትሰራበት ቤት ጊቢ ውስጥ ከፍ ያለ ድንጋይ አለ እዛ ላይ ወጥታ ልብስ ልታሰጣ ስትል እግሯን ሳት ብሏት ነው መሠለኝ እንዳትሞት እንዳትሽር ሆና ወደቀች ስብርብር  ነው ያለችው የኔ እናት ፤ ወይ ደሀ መሆን ሳያምርብህ እንደባከንክ ኑረህ ዘመንህን መጨረስ ነው ። የእሶስ ከሁሉ ተለየ ገና ባሏን ከማጣቷ በልጅም ሳትባረክ ቀረች ፈተናዋን እያበዛችሁባት ደፋ ቀና እያለች ሰርታ እንኳን እንዳትበላ ተሣስራ መቅረቷ ነው ። በትኩስ ቁስል ላይ ሌላ ቁስል ተደራረበባት ፤ ወይ ፈጣሪዬ እንዴት ታረገኝ ይሆን ? የኛስ መጨረሻ ምን ይሆን አሄሄ "አሉ  በልጅ አልተባረከችም ሲሉ እኔን በነገር ወጋ ሊያደርጉኝ ፈልገው እንደሆነ ሳይገባኝ አልቀረሁም መቼስ እህቶቼን እንዳልሆነ እኔም እሳቸውም የምናውቀው ነገር ነው



ግን የገረመኝ መርዶ እንኳን ሲነገር ቃስ ተብሎ ይሀን ሰው አረጋግቶ ነው እሳቸው ግን የእናቴን ህመም ሲናገሩ ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁኔታ እና ቅስሜን በሚሰብር ንግግር ነው ። እንደሳቸው አባባል ዳግመኛ ተነስታ መራመድ የምትችልም አልመሠለኝ ፤ በአንድ በኩል ደሞ የተናገሩት ነገሮ እውነት ከሆነ ቀጣዩ የቤተሰቤ ህይወት ምን ሊመስል እንደሚችል ማሰቡን እራሱ ሳስበው ሰቀጠጠኝ ጠጋ ብዬ እናቴን በአትኩሮት ስመለከታት ጋደም እንዳለች ታቃስታለች ስቃዩ አላስተኛ እንዳላት ከሁኔታዋ ተረዳሁ የለበሰችውን ጋቢ ገለጥ አድርጌ እግሯን ለማየት ስሞክር በነጠላ ጨርቅ ከጉልበቷ አንስቶ እስከ ቁርጭምጭሚቷ በታች ተጠቅልሏል ነፍሴ ከስጋዬ ልቅቅ ያለ መሠለኝ በጣም አዘንኩ ከዛ ፍቅር እያለቀሰች ለምን ልትነግረኝ እንዳልቻለች ተረዳሗት ከዛም የጎረቤታችን ንግግር ምንም እንኳን ባይጥመኝም ይበልጥ ነገሩን ለመረዳት ስል " ታድያ ማነው መውደቋን ያየው ? እዚህስ ማን አመጣት ? ወጌሻ ቤት ሄዳ ነበር  እንዴ ? " አልኳቸው " ያው ስትጮህ የሰሟት አሰሪዋ ናቸው የደረሱላት አሉ ፤ ከዛም አፋፍሰው አካባቢው ካለ ወጌሻ ወሰዶት እና እንደሚሆን አደረጉላት ያው ሲመስለኝ ግን ውልቃት ሳይሆን ስብራት ነው  ፤ ከእንግዲህ በሗላ መራመድ የምትችልም አይመስለኝም ብትራመድ እንኳን ካለዱላ የምትችል ይመስልሀል ? " አሉኝ ይበልጥ ሆዴን አባቡት ከተቀመጥኩበት እጄን ጭንቅላቴ ላይ ጭኜ ፍፁም ፀጥታ በሰፈነበት የውስጤ ጩኸት ብቻ በሚያስተጋባበት ሁኔታ እንባዬን አፈሰስኩት መስራት አለመቻሏ ብቻ ሳይሆን መራመድ ካልቻለች የሚደርስባት የስነልቦና ጉዳት በልጦ ታየኝ ....ይቀጥላል
#share

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur