Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፵፪ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፵፪
@yanetmasra

" ለምን ተገደለ ? " ብዬ ጠየቅኩት ይበልጥ ዝርዝሩን ለማወቅ " ምን መሠለህ አዲስ አበባ መኖር ከመጀመራቸው በፊት ኑሯቸው በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ነበር ተወልደው ያደጉትም እዛው ነው ታድያ አንድ ሚሽነሪ ወደዛ በሄደ ሰአት ወንጌልን መስክሮላቸው ወደ ጌታ ሊመጡ ችለዋል ከአካባቢው ሰው ጋር ተመሣስለው መኖር በከበዳቸው ሰአት ሁሉም አማኝ መሆናቸውን ደረሱባቸው በአካባቢው ማህበረሰብ የነበራቸው ክብር ሁሉ ተሟጦ ወደ መናቅ ተቀየረ በቤተሰብ ፣ በዘመድ ፣ በሽማግሌ መጤ ሀይማኖትን ትተው የእናት እና የአባታቸውን እምነት እንዲቀጥሉ ተነገራቸው ሆኖም ግን አቋማቸውን ተናግረው ማድረግ እንደማይችሉ እና ላመኑት ወንጌል እንደሚኖሩ ውሳኔያቸውን በነገሯቸው ሰአት ነገሮች ከልምምጥ ፣ ከምልጃ አልፎ ክፋት ላይ ደረሰ አስመርረው ከሀገሩ እንዲለቁ አደረጓቸው መጀመሪያ ግን እንዲሁ እንደዋዛ የለመዱትን ቀዬ ለቀው አዲስ ከተማ መኖር ስለማይሆንላቸው ነገሮች ይረግባሉ ሲሰለቻቸው ይተውናል ብለው በትዕግስት ነገሮችን ማለፍ ጀመሩ ሆኖም ግን አንድ ቀን ቤታቸው ላይ በድንጋይ ወገራ በሚያካሂዱ ሰአት ታዳጊው ልጃቸው ከቤቱ በራፍ ኖሮ ኖሯል የተወረወረው ድንጋይ አናቱን ብሎ ይጥለዋል ደም በብዙ ስለፈሰሰው አጉል ምት ስለሆነ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል ከሀዘን ውጪ የሚያደርጉት ነገር ጠፋ ቤተሰቦቻቸውም በእምነታቸው ምክንያት አንቅረው ስለተፏቸው እናት እና አባት እንዲሁም እህቱ ነበር ለለቅሶ የተቀመጡት ብቻ እሱም ሳይበቃቸው ጉዳታቸውን በመናቅ ሲያንጓጥጦቸው እና ጥላቻቸው ቢበዛ እትብታቸው የተቀበረበትን መንደር ትተው ወደዚህችው አዲስ አበባ መጡ መጀመሪያ ላይ ነገሮች እንዳሰቡት ጥሩ ባይሆንም እያደር ግን



ሠው ሲያውቁ ፣ ሀገሩን ሲለምዱ ስደቱ ቀረ ባይባልም በፊት ከነበረው ግን እየተሻለ መጣ ኑሮአቸውንም እዚህ ካደረጉ በሗላ በብዙ ውጣ ውረድ ቢሆንም እዚህ ደርሰዋል እና የልጃቸው ሰርግ ደሞ ለነሱ ደስታን ካለወሰን አምጥቶ ልባቸውን በሀሴት ቢሞላም ይሀ በቤተሰቡ ተወዳጅ የነበረ መንትያ ወንድሟ ይሄን ቀን ሊያይ ስላልቻለ እና ቤተሰቡን መለየቱ ደስታው ከሀዘኑ ጋር እንዲበረዝ ምክነያት ይሆነዋል " አለኝ የሠማሁት ታሪክ አስገርሞኛልም አስደንቆኛል የሠው ልጅ ተወልዶ እስከሚሞት ድረስ ያለው ታሪኩ ሊገመት የማይችል እንደ መፅሀፍ በየምዕራፉ የተለያየ የህይወት ወጣ ውረድ የሚያጋጥመው ውስብስብ ነገር ነው አሁን ይሄን ታሪክ እንደኔ ያልሰማ ሰው እንባቸው የደስታ ስለሚመስላቸው የቤተሰቡን ሁኔታ ይቀኑበት ነበር ግን በሳቅ የተሸፈነ ጠባሳ በእንባ የታጀበ የተስፋ ጭላንጭል ከፊታቸው መነበቡን ልብ ላለው እና በቅርብ የሚያውቃቸው ሠው ነው ሊረዳው የሚችለው ።

   ሙሽሮቹ የቤተክርስቲያኑን ስርአት ጨርሰው ወደ ግብዥው ቦታ ሲሄዱ እኛም ተከተልናቸው እዛ ያለውን ዝግጁት ጨርሰን ወደ ቤት መመለሳችን አይቀርም እና ወደ ቤት ተመለስን ያየሁት ዝግጅት ሁሉ አስደስቶኛል ከዛ በፊት አይቼ የማላውቀው ስለሆነ መቼም ቢሆን ከአይምሮዬ አይጠፋም እያንዳንዱ ሁኔታ እና ዝግጅት በቅደም ተከተል በአይምሮዬ መዝገብ ላይ አስፍሬዋለሁ ከሁሉም በላይ የሠማሁት ታሪክ ግን ልቤን ነክቶኛል እንደውም በአይምሮዬ ሳስብ የነበረው ስንት አይነት መከራ እና ህይወት በስንቱ ቤት ውስጥ ይኖር ይሆን ወንጌልን ለማስቀጠል ምን ያህል ዋጋ እና ምን አይነት ከሠማሁት እና ካየሁት የተለየ ታሪክ ይኖር ይሆን የኔስ ህይወት ምን አይነት የህይወት አቅጣጫ ይይዛል ? ብዬ ሚሰቤ አልቀረም ....ይቀጥላል
#share

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur