Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፵፩ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፵፩
@yanetmasra

በወቅቱ አስደናቂ ዝማሬዎች የእግዚአብሔር ክብርን የሚገልጡ የሰዎች ልብ ውስጥ ዘልቀው ገብተው መንፈስን የሚቆጣጠሩ ስለነበሩ ብዙ ምዕመኖች እኔንም ጨምሮ ተባርከንበታል ፤አማኝ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን የማያምኑትም  ውስጥ ውስጡን የሚያዳምጡ ነበሩ አንዳንዶቹ አላማኞች ችግራቸው አለማመን ሳይሆን የይሉንታ ችግር ነው። ወንጌል ሲመሰከርላቸው እንዲሁም ይበልጥ ስለእውነቱ ያውቁና ለመወሰን ይቸገራሉ ቤተሰቦቼስ ፣ጎረቤቶቿስ፣ትዳሬስ ፣ልጆቼስ ብለው ወደኃላ ያፈገፍጋሉ እነሱ ሰዎች ይበልጥ ክርስቶስን ያውቁ እና የመስቀሉ ስራ የገባቸው አይመስለኝም ምክንያቱም ክርስቶስ ከሁሉም በላይ ነው ሌላው ቢቀር እኛ እንኳን የራሳችን ሳይሆን የእርሱ ነን።

  በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የጴንጤ ሠርግ አየሁ፤ከዛን ቀደም ያየኃቸው ሠርጎች ሁሉ አላማዊ የሆኑ የሚዘፈንበት ፣የሚጨፈርበት ፣የሚጠጣበት ከክርስቶስ በላይ ሙሽሪት እና ሙሽራው ፣ሚዜ እና ቤተሠብ የሚደነቅበት ነበር የጴንጤ ሰርግ ስነስርአት ምን ሊመስል ይችላል የሚለው ሀሳብ ልቤ ጠይቆ ቢያቅም አጋጥሞኝ ስለማያውቅ ላውቀው አልቻልኩም ከዛን ግን ጋሼ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎደኛው ሴት ልጅ ልትዳር ስለነበር የዛ ፕሮግራም ላይ ይዞኝ ተገኘ ይህን ሠርግ ልዩ የሚያደርገው ነገር ቤተክርስቲያንአችን ከተቆረቆረች ጀምሮ ሠርግ ተከናውኖባት  ስለማይታወቅ ይሀ የመጀመሪያ ነበር ታዲያ ሙሽሮቹን ከቤታቸው ጀምሮ አጅበን ወደ ቤተክርስቲያናችን ሄድን  መጀመሪያ በቤት ውስጥ እየተዘፈነ ሳይሆን እየተዘመረ ሙሽሪት ከቤተሰቦቿ ጋር እንዲሁም ከሚዜዎቿ ጋር በመሆን ሙሽራውን እየጠበቀች ነበር



በወቅቱ ያየሁት ሁኔታ በውስጤ ደስታን ፈጥሮልኛል ካሰብኩትም በላይ ደስ የሚል እና ከምድራዊው ሙሽራ በላይ የሠማያዊውን ሙሽራ የሚያከብር ስለነበር ነው በቤተክርስቲይናችን ውስጥ በዝማሬ ፣በቃል፣በፀሎት ስነስርዓት ታጅቦ ሙሽራው እና ሙሽሪት ጋብቻቸውን ፈፀሙ ምንም እንኳን በወቅታዊ ችግር ምክንያት የታሠበውን ያክል ሞቅ ደመቅ ባይልም ቆንጆ በሚባል ሁኔታ ጋብቻቸውን ፈፀሙ እግዚአብሔር ሲረዳ እና የሠርጋቸው ቀን መጥፎ ጠባሳ እንዳያርፍበት ሲጠነቀቅላቸው ምንም አይነት ረብሻ እና ብጥብጥ ያስነሳ ግለሰብም መንግስትም አልነበረም የሙሽሪት ቤተሰቦች ከደስታቸው የተነሳ እንባቸው እንደጎርፍ ያዘንባል ሀዘን ነው እንዳልል በልጃቸው። የደስታ  ቀን መሆኑ ሀሳቤን አከሸፈው የደስታ ነው እንዳልል ከጎናቸው ያሉ ሠዎች ትክሻቸውን መታ መታ እያደረጉ ያፅናኑአቸዋል ቀስ ብዬ አንገቴን ወደ ጋሼ ጠጋ አድርጌ በጆሮው "እንባቸው የደስታ ነው ወይስ የሀዘን ?ሁል ጊዜው ሙሽራ ስትዳር ማልቀስ ወግ ነው እንዴ?"ብዬ ጠየኩት "ደስታም ያስለቅሳል ግን አንዳንዴ  ደስታ እና ሀዘን ይቀላቀላል እና ያስለቅሳል  " አለኝ ትክዝ ተብሎ ፊቱ ላይ የመረበሽ ስሜት ይታይበታል "እንዴት ?" አልኩት ነገሩ ምንም እንዳልገባኝ በሚያሳብቅ አስተያየት። እየተመለከትኩት "አው ምን መሠለህ አሁን የምታገባው ልጃቸው ሀዜብ መንታ ነበራት አባታቸው እንደነገረኝ ከሆነ ከእህቱ ጋር እና ከቤተሠቡ ጋር የተለየ አቅርቦት ነበረው ሆኖም ግን ቤተሠቡ ባልጠበቀው ሁኔታ ከደጃፋቸው ተገደለ ይመስለኛል የእሱ አለመኖር ነው ያስለቀሳቸው "አለኝ ፊቱን ቅጭም አድርጎ .........ይቀጥላል
#share

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur