Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፵ @yanetmasra ' | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፵
@yanetmasra

"አው ጋሼ እሱንስ ልክ ነህ እግዚአብሔር አለ ነገር ግን መልካም መልካሙን ማሠብ ይሻላል " ብዬ የጀመርኩትን ጥያቄ ዘጋሁ 

  እውነትም ግን ቢታሰርስ ብዬ አሰብኩ ከባድ እንደሚሆንበት አልተጠራጠርኩም እንደውም ምን ትዝ አለኝ በእኛ እድሜ ክልል ውስጥ ያለ ዩሴፍ የተባለ ልጅ መታሰርን እና በቅርብ መፈታቱን ነግሮኝ ነበር ታድያ ምንም ልጅ ቢሆንም ደፋር እና ወንጌልን ሲናገር የማይፈራ ስለነበር እሱን እና የተወሰኑ ጓደኞቹን ለጥቂት ቀናት በእስር አቆይተዋቸው ነበር ታድያ በጣም ክትትል ያደርጉባቸው ነበር ውስጥ አንድ አንድ የሚሰልሉ ሰዎችን በማያውቁበት መንገድ ቢያስገቡም እነሱ ግን መጠርጠራቸው አልቀረም ስለዚህ ፀሎት በሚያደርጉ ጊዜ ከታወቀ ተወስደው መቀጣታቸው እና የእስር ጊዜያቸው መራዘሙ ስለማይቀር መፍትሄ አድርገው የወሰድት እዛው እስር ውስጥ እንዳሉ ዩሴፍ ጮክ ብሎ ጉሮሮውን ሲጠራርግ ሁሉም በአንድ መንፈስ ሆነው በውስጣቸው ፀሎት ያደርጋሉ መልሶም ከጥቂት ደቂቃ በሗላ በተመሳሳይ ሁኔታ ጉሮሮውን የሚጠራርግ አስመስሎ ድምፅ ያወጣል ያኔ ጨረሱ ማለት ነው ሆኖም ግን እንዴት አድርገው እንዳወቁ ባይታወቅም ይህንንም ዘዴ አወቁባቸው ስለዚህ ያላቸው አማራጭ መፀዳጃ ቤት ቤት በሚል ሰበብ ባለቻቸው ጥቂት ደቂቃ መፀለይ ነው እኔን የገረመኝ ምንም ያህል ለወንጌል እንቅፋት ቢሆኑም እግዚአብሔር ግን ከስር ከስር ስራቸውን ስለሚያከሽፍባቸው ማድረግ የፈለጉትን ያህል ሊያደርጉ ቀርቶ አንገቴን ለቢላ እያለ የሚያመልከው መብዛቱ ነው ። አይናቸው እያየ ማስተዋል ስለተሳነው ልባቸው ስለደነደነ እንጂ የአማኙን ጥንካሬ እና የእግዚአብሔርን ድንቅ እና ተአምራት እያዩ እነሱ እራሳቸው ለመዳን ይችሉ ነበር



እስር ቤት ውስጥ መፅሀፍ ቅዱስ ማስገባት በፍፁም አይፈቀድም ውስጥ እንኳን ታስረው ህብረት ማድረግ የቻሉ ሰዎች በቃላቸው ያለን ጥቅስ በመናገር በእርሱ እርስ በእርስ እየተወያዩ እንደሚልዩ ሰምቻለሁ ታድያ በዛን ሰአት መፅሐፍ ቅዱስ ለማግኘት የነበራቸው ርሀብ ልዩ እንደነበር ታስሮ የተፈታው ወንጌላዊ ዘላለም በአንድ ስብከቱ ላይ ከጥቂት ቀናት በፊት አስተምሮ ነበር ታድያ በዚህ ስደት ውስጥ ወንድ ነው ሴት ናት ወጣት አዛውንት የሚባል የቅጣት ድልድል የለም የወታደራዊውን መንግስት ህግ ያልሰማ እና ያልተከተለ ቅጣቱን ይቀበላል ድብደባ ፣ መታሰር እንዳለ ሁሉ ባስ ሲልም ሊገደሉ ይችላሉ ለወንጌለሸ ብለው ተሰደው የሞቱ ስማቸው በዘለአለም ህይወት መዝገብ ላይ መስፈሩ ጥርጥር የለኝም
በወቅቱ ከድብደባ ውጪ የደረሰብኝ ከባድ ነገር ባይኖርም እነሱ እንደሚሉት ማድረግ ካልቻልኩ በወሬ የምሰማውን የእስርቤት ታሪክ በአካል እንደማየው አልጠራጠርም
   ከጥቂት ቀን በሗላ ወደ ክፍል ሀገር እንዲሄዱ የተደረጉ አገልጋዬች በመምታጣቸው ቤተክርስቲያኗ ያዘጋጀችው የምረቃ ዝግጅት በከፊሉም ቢሆን ተካሂዶ እዚህ ለመድረሱ ዋጋ የከፈሉ አሁን ግን በቦታው ስላልተገኙ ሁሉ ተፀልዮ መደበኛ ፕሮግራም ተጀመረ በቋሚነት እሁድ እና ማክሰኞ የወጣቶች ፕሮግራም እንዲሆን ተወሰነ አካሄዱ አስደስቶናል ፤ በሌላ አካልም የደረሰ ጫና እና ግፊት አልነበረም አይሰሙም ብለው ትተውን ይሆን ወይም ደሞ ጊዜውን ጠብቀው የሚያፈነድትን ቦንብ አጥምደውልን ይሆን በጊዜው የታወቀ ነገር አልነበረም  ። እኔም ቤተክርስቲያኗ ፕሮግራሞችን በመደበኛ መልኩ ማስኬድ ከጀመረች ጀምሮ የማደርጋቸው እንቅስቃሴዎች እየጎሉ መጡ ወንጌልን መናገር ስለወንጌል መመስከር ቋሚ ስራዬ ሆነ ....ይቀጥላሉ
#share

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur