Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፵፮ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፵፮
@yanetmasra

ትምህርት ጀመርኩ ። ውዬ ብመጣም ተማርኩ ማለት ግን አልችልም እህቶቼ ትምህርት ቤት ስለሚሆኑና እናቴ ብቻዋን ስለምትሆን የእሷ ነገር ይበልጥ እያሳሰበኝ ለአይምሮዬ ፋታ ነሳኝ ። ዱላዋን ተደግፋ እቤት ውስጥ መዘዋወር ብትችልና አንዳንድ ነገሮችን ማድረግ ባያቅታትም  የፈለገችውን ሁሉ ማድረግ ግን ይቸግራታል ጎንበስ ብላ እቃ ማንሳት ፣ ብዙ መዘዋወር ፣ ረጅም ደቂቃ መቆም የማትችለው ነገር ነው ለዚህም አማራጩ መተኛት ነው የተባለ ይመስል ትተኛለች ፤ እሱ ደሞ ይበልኝ ያደቃታል ።

   ከትምህርት ቤት እንደተለቀቅኩ በፍጥነት ወደ ቤት ሄጄ እናቴን አያትና የሊስትሮ እቃዬን ይዤ እስኪመሽ ጫማዎችን እጠርጋለሁ ያገኘሗትን ሳንቲም ለቃቅሜ ወደ ቤት ይዤ እሄዳለሁ ያመጣሁት ብር ጥቂት ነገር ብትሸፍንም የአራት ሰው ፍላጎት ግን ማሟላት አትችልም ሌላው ቢቀር ለኔ ራሱ በቅጡ አይበቃኝም ሆኖም ግን እኔ የምኖረው እነበሱፈቃድ ጋር ስለሆነ የማገኛትን ነገር ለነሱ ከማዋል ውጪ ለራሴ አንድ ሳንቲም አላነሳም ፤ መኖሪያዬን ግን እናቴ ከታመመች በሗላ እነሱ ጋር ማድረግ ብፈልግም የታመመች ሰሞን እዛው ማደር ከጀመርኩ በሗላ ሻል ሲላትና መንቀሳቀስ ስትጀምር " ' ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል '  አሉ በል እዚህች ቤት የምትኖረው መጤ እምነትህን ስትተው ብቻ ነው አለዛ ግን እንዳታስበው ታማለች ፣ ምንም አታመጣም ብለህ እንደሆነ የማመጣውን አምጥቼ ጉድ ነው የማደርግህ ስለዚህ እዛው የለመድክበት ማደር ትችላለህ " አለቺኝ እውነት ለመናገር ቅስሜን ነው የሰበረችው በዛ ሰአት ስለሌላ ነገር ማሰብና መጣላታችንን ሁሉ ዘንግቼ የማስበው ስለእናቴ የጤና ሁኔታ እና መዳን ነበር በዛ ሰአት እንደዛ ስትለኝ ቂም ሁሉ ልቋጥርባት ምንም አልቀረኝ ነበር ።



" ምናለ ግትርነቷን ትታ እንደ እናትና ልጅ ብናወራ የመጣብንን መከራ ተባብረን ብንመካከርና ብንወጣው ጭራሽ በዚህ ሰአት ለምን ደካማ ጎኔን ነክታ ታቆስለኛለች " ብዬ ከልብ ተሰማኝ የዛች ቀን ተናድጄ ስለነበር እስከሚቀጥለው ቀን በማኩረፍ ሳላያት ቀረሁ በንጋታው ግን አላስቻለኝም ማደሩን ብትከለክለኝም ገባ ወጣ ማለቴን ግን አልተውኩም ምናልባት ግዴታ ስለሆነባት ነው መሠል ባታወራኝም እንኳን ጭራሹን እንዳልገባ አልከለከለችኝም  ። እኔም በነገሮች ተወጣጥሬ ከሌላው ጊዜ በተለየ ወደ እግዚአብሔር መጠጋት ቢገባኝም ጭራሹኑ ሳላስበው እራቅኩ የቅዳሜ የፀሎት ህብረት ፣ የቸርች አገልግሎት ላይ መሳተፍ ፣ እሁድ እሁድ የመደበኛ አገልግሎት ላይ መገኘት ቢያንስ ለሁለት ሳምንት እርግፍ አድርጌ ተውኩት ብዙ ጊዜ ከሚገርሙኝ ነገሮች አንዱ በጣም ስንደሰት እና ስንከፋ ወይም በህይወታችን ከባድ ፈተና ሲገጥመን ለምን እግዚአብሔርን እንደምንረሳው ነው  ደካማ ስለሆንን ችግራችን እንዳያጎብጠን  ቶሎ ብለን ልንደገፈው ሲገባ እርስት አድርገነው እኛው አዋቂ የመፍትሄ ባለቤት ሆነን እንገኛለን ብለን ብለን ሲያቅተን እናማርራለን ከሱ ከፍ ሲል ደሞ መጀመሪያ ማድረግ የነበረብንን ገሸሽ ያደረግነውን እግዚአብሔር ሄደን " ጌታ ሆይ አልቻልኩም መሞቴ ነው ስለኔ ግድ አይሰጥህም ወይ " ብለን እንጨቀጭቀዋለን  መፀለያችን ባይከፋም የመጨረሻ መፍትሄ ማድረጋችን ግን አግባብ አደለም እኔም በዛ ምክንያት በራሴ አፈርኩ  " አቤት ጌታ ሆይ ምን ትለኝ ይሆን ? እንዴትስ ትታዘኝ ይሆን ? " ብዬ በመጠየቅ እራሴኑ ታዘብኩት ከዛን በሗላ ግን ከልቤ እኔ ደካማ በመሆኔ ላደርግ የማልችለውን እሱ እንዲያረግልኝ ፣ እንዲደግፈኝ እና እንዲያበረታች ፀለይኩ ....ይቀጥላል
#share

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur