Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፴፱ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፴፱
@yanetmasra

ቀኑ ደረሰ ፕሮግራሙ የሚደረግበት ቀን ልባችንን ደስታ ቢሞላም ግርግር ሊፈጠር እንደሚችል ማንም ሳይጠረጥር የቀረ አልነበረም ምክንያቱም ሌላው ቢቀር እንኳ ከሠሞኑ ብዙ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ሲያደርጉ ነበር። ከምዕመናን በላይ አገልጋዮች ላይ የበለጠ ጫናው እየጠነከረ መጥቷል እንደውም ምርቃቱ በሚዘጋጅበት ቀን ሊያስሯቸሙ እንደሚያስቡ ጭምጭምታ ስለተሠማ አንዳንዶቹ ከከተማ እንዲወጡ ግፊት ተደርጎባቸው ነበር። ሁሉም ተገኝተው ከተወሰዱ ቤተክርስቲያኑን ሊመራ የሚችል  አልነበረም ታዲያ ያልተጠሩት እንግዶቻችን ግን እንደሚመጡ የምናውቀው የቀበሌ ወጣቶች እና የቀበሌ ወጣት ሊቀመንበር የነበረው እድሜው ከ30ዎቹ መጀመሪያ የሚገመተውን ወጣት ጨምሮ መጡ እንደገቡ ትርምስን ፈጠሩ ' ለቀባሪ አረድት ' እንደሚባል ሁሉ በመምጣታቸው የተገረመም የተደናገጠም አልነበረም የመጡት ግን የመጡት ግን ፍርሃት እና መደናገጥ ይታይባቸዋል ብለው ስላሰቡ ስላልታየብን ተገርመው ነበር ቢሆንም ግን ሠብሠብ አርገው የቀሩትን አገልጋዮች ወደ ቀበሌው ወሰዶቸው ሌሎቻችን ግን እንድንበተን ተደረገ ብዙ ጊዜ ጭቆናውን ባስ እና ጠበቅ የሚያረጉት በአገልጋዮች ላይ ነበር ሲመስለኝ "እረኛውን ምታ መንጋው ይበተናል" የሚለውን መርህ የጨበጡ ይመስላል ታዲያ የዛን ቀን እንደታሰበው ፕሮግራሙ ሳይካሄድ ቀረ እነሱም እዛው እስር ቤት አደሩ ይህን ያደረጉበት ምክንያት በእምነታቸው  የተነሳ ቢሆንም ነገሩን የአብዮቱ  ተቃዋሚዎች ብለው ለማድበስበስ ጥረት አደረጉ እውነታው ግን የአደባባይ ሚስጥር ነው። የቤተክርስቲያን መደበኛ ፕሮግራም ላልተወሰነ ቀናት ማካሄድ ባለመቻሉ ሁሉም አማኝ ቤቱ በሚመቸው መልኩ  ፆምና ፀሎት በመያዝ ለታሰሩት አገልጋዮች



እንዲፀልዩ እና በግላቸውም ቢሆን ወይም ከቤተሠቦቻቸው ጋር በጋራ ህብረት በማድረግ እንዲበረቱ  ተደረገ ፤እኛም በቤት ውስጥ በመሆን ፀሎተችንን ማሠማት ቀጠልን የምድሩ መሪ የራሱን እቅድ የሚያስፈፅም እንጂ የሀይማኖትን እኩልነት የማያራምድ ባለመሆኑ ከዙፋኑ ሆኖ የሚያየን ልቡ ለኛ የሚራራ እውነተኛ ፈራጅ ለሆነው እግዚአብሔር ጩኸታችንን እናሰማ ነበር

   ሳይፈቱ ከአንድ ወር በላይ የቆዩት አገልጋዬች በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ለማወቅ ስለፈለኩ ጋሼ እቤት ሲመጣ " ጋሼ የታሰሩት አገልጋዬች ነገር ከምን ደረሰ ' ቄሱም ዝም መፅሀፉም ዝም ሆነሳ ነገሩ ፤ ሳይፈቱ ለእረጅም ጊዜ ቆዩ ፤ እዛ ውስጥ የተመቻቸው ይመስልሀል ?" አልኩኝ በልቤ ውስጥ የታመቀውን እንቆቅልሽ ቢፈታልኝ በማለት " ወይ ዩሀንስ ተመቻቸው ትላለህ እንዴ የአንበሳ መንጋጋ ውስጥ ገብተው እዛው ያኝኳቸዋል እንጂ ምን ይመቻቸዋል ብለህ ነው ? እንደውም አንድ ሁለት ቀን ሄጄ ላያቸው ሞክሬ ነበር " በምክር እና በማስፈራሪያ አልሆን ሲላቸው የጉልበት ስራም ያሰሯቸው ጀምሯል ባስ ሲልም የድላ ውርጅብኝ ያወርድባቸዋል ዘንድሮስ ለብቻው ነው ሰይጣን ሀይሉን አጠራቅሞ እየተዋጋን ነው ደግነቱ የሚጠብቀን አይተኛም እንጂ እንደሱ ፍላጎት ቢሆን ኖሮ አንድ አማኝ ባልኖረ ነበር እኔንም ቢሆን አልወደድኝም ምን እንደሚሉ ባላውቅም በሄድኩ ቁጥር ገልመጥ ገልመጥ አድርገው በሹክሹክታ የሆነነገር ሲዶልቱብኝ ሰምቻለሁ እኔም የእነሱ እጣ እንደሚደርስብኝ አልጠራጠርም ግን ፈርቼ አይምሰልህ አንዳች ልቤ አይታወክም ቢሆንም ግን አንዳንዴ የቤተሰብ ሀላፊ ስትሆን የነሱ ነገር ያስጨንቅሀል ባለቤቴ ስራ ስለማትሰራ የልጆቹ ህይወት እንዴት ይሆናል የሚለው ነገር ያሰጋኛል በሌላ በኩል ደሞ ከኔ በላይ እግዚአብሔር እንዳለላቸው ሳስብ እፅናናለሁ " አሉኝ ....ይቀጥላል
#share

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur