Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፴፰ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፴፰
@yanetmasra

" ዋናው ሰላም መሆንሽ እና መመለስሽ ነው " አልናት
    ያን ጊዜ ነበር ወፌ ላላ ግርፋት ሲባል የሰማሁት ያው ቤተክርስቲያን በወቅቱ ስላልተቀረቆረ ህብረት የሚደረገው እቤት ውስጥ ፣ ወይም ቅዳሜ ቅዳሜ ወደምንገናኝበት የፀሎት ዝግጅት ላይ ነበር ታድያ በዛን ወቅት የምናውቃቸው ወጣት አገልጋዬች ከፀሎት ህብረት መሪያችን ከአብርሀም ጋር የማይጠፉትን እና እራሱን አብርሀም ጨምር ሊያስሯቸው እንደወሰዷቸው ሠማን በጣም በማዘናችን የተነሳ የተደናገጥነውም ጥቂቶች የምንባል አይደለንም ዋናው ጭንቀታችን መታሰራቸው ብቻ ሳይሆን ከታሰሩ በሗላ ምን ይሆናሉ የሚለው ጥያቄ ነበር ታድያ ለአንድ ሳምንት አስረው ከለቀቋቸው በሗላ የተደረጉትን ከአንድ አንዶቹ ሰማን በፖሊስ ጣቢያው ውስጥ ወፌይ ላላ በተከታታይ ቀናት ውስጥ እንደተገረፉ ሠማን በአንድ ሳምንት ቆይታቸው ውስጥ  ፊታቸው ግርጥት ማለቱ ምን ያህል ስቃይ እንዳሳለፉ ማረጋገጫ ሆነን ለተወሰነ ቀናት ከቤታቸው ሆነው አገግመዋል ታድያ ግን ነገሮች በዚ ሳያበቁ እና ሳይቋጩ ቀሩ እንደውም በሰው ቤት የሚደረገው ህብረት እና ፀሎት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ብዙ ወጣት እና ልጆች ተይዘው እንዲማሩ ለምዕመኑም ሠፊ እንዲሆን በማለት ቤተክርስቲያን የመቆርቆር ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ተሠማ የሁሉም ልብ የመጣው ይምጣ እንጂ ማድረጋችን አይቀርም የሚል ገፅታ ይነበብበታል አንድ በጌታ የሆኑ እድሜያቸው ከ60 አመት በላይ የሚገመቱ አባት መኖርያ ቤታቸው ቤተክርስቲያኗ እንድትቆረቆርበት ሲሉ በፍላጎት ሰጡ ይሄ ደሞ አስደሳች ዜና ነበር የእሳቸው መውደቂያ ያሳሰበው ሠውም ሌላ ቤት እንዳላቸው ሲጠይቁ " ከእንግዲህ ለየትኛው እድሜዬ እኔ ወደ ልጄ ሄጄ ከእርሷ ጋር እኖራለሁ ቤቷ ለኔ ለአባቷ መሠብሰቢያ በቂ ነው ።



ይሄ ውሳኔም እሷን ያስደስታታል እንጂ ፈፅሞ የሚያስከፋት ነገር አደለም " ብለው መለሱ  ከዛን ቀን በሗላ መኖሪያ ቤቱን ወደ አምልኮ ቤት ለመቀየር አንዳንድ ለውጦች ተደረጉበት ሁሉም ያለውን ከጉሮሮው ፣ ከልጆቹ ፣ ካለው ቀንሶ እያዋጣ አብሮ በመስራት እና በመደጎም ቤተክርስቲያኗ ተሰራች እኛም ደሞ ትምህርት በሌለ ሰአት እና ቅዳሜ እና እሁድን እዛው በመዋል አንድ አንድ ነገር እናግዝ ነበር ሁሉም ምዕመን ወጣት ሳይል አዛውንት በደስታ እና በተስፋ ነበር ጉልበቱን የሚያፈሰው " እኛ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን እቺ ቤተክርስቲያን በተስፋ እና በምኞት ብቻ አትቀርም ተሰርታ ታበቃለች የፈለጉትን ቢያደርጉ ቀሪውን እግዚአብሔር ያውቃል " የሚል አስተሳሰብ በሁሉም ልብ ውስጥ ዘልቆ ገብቶ ነበር ። ወደ መጨረሻው ማገባደጃ ሲደረስ የሁሉም ደስታ ወደር አጣ በየሰው ቤት ማምለክ ቀርቶ በቤተክርስቲያን ማምለክ ልንጀምር ነበር የማስመረቂያ ዝግጅትን ለማዘጋጀት ሁሉም እየተሰናዳ አንዳንድ የሙዚቃ መሳሪያዎችን በውሰት ከሌላ ቦታ ለማምጣት እንዲሁም የሙሉ ጊዜ አገልጋዬች የነበሩ ያላቸው የየራሳቸውን ጊታር ይዘው እንዲመጡ ተደረገ በፀሎት ህብረት ውስት ያሉ የመዘመር ፀጋ ያላቸው ልጆች በእግዚአብሔር ፀጋና በራሳቸው ትጋት ለዝማሬ ይዘጋጅ ነበር የኔ የፀጋ ስጦታ ወንጌል መናገር ነው እና በዕለቱ ከኛ ህብረት ውስጥ ተመርጬ የምስራችን ቃል እንድናገር እድል ተሰጠኝ ይህች ቤተከርስቲያን ድንቅ ነገር እንደሚሰራባት ብዙ ሠዎች ወደ ጌታ መጥተው እንደሚማሩባት እና ለአዲስ ትውልድ መሠረቱ የፀና የማይገለበጥ እምነት እንደሚተላለፍበት የሁሉ ተስፋ ነበር ....ይቀጥላል
#share

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur