Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፴፮ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፴፮
@yanetmasra

" ምን መሰለህ እዩዬ በጣም እርቦህ ምግብ ሲቀርብልህ እና እንዲሁ ምግብ በሞላበት ለመብላት ስትዘጋጅ ያለህ ስሜት ይለያያል በጣም እርቦህ ከምግብ እርቀህ ትንሽ ነገር እየቀማመስክ ስትኖር ለምግብ ያለህ ፍላጎት እና ጉጉት ይጨምራል እንዲሁም የምግብ ቡፌ እየቀረበልህ  አማርጠህ  የምትበላ ከሆነ ግን ይሄን ያህል ጉጉት አይኖርህም የተሰጠህን በቅጡ ላትበላ ወይም ደሞ ቁንጣን ሊያጨናንቅህ ይችላል ። ክርስትናም እንደዚሁ ነው ማምለክ በማትችልበት ሰአት እና ሁኔታ ላይ ሆነህ መንግስትም ቤተሰብም ቢነሳብህ በድብብቆሽ እና በመከራ ሲሆን እምነትህ ይበልጥ ኢየሱስን ለማወቅ ያለህ ጥማት እየጨመረ ርሀቡ ያንገበግብሀል መንፈሳዊ ነገሮችን ተሻምተህ ትካፈላለህ ምክንያቱም የረሀብህ ማስታገሻ ስለሆነ ፤ አሁን ላይ ግን ብዙ ነገሮች እንደልብህ ነው ቤተክርስቲያን መሄድ ብትፈልግ ፣ በቤትህም ሆነ በሰው ቤት ፕሮግራም ብታዘጋጅ የሚያስቆምህ የለ ፣ ከበፊቱ በተሻለ መንገድ ላይ ወንጌልን መናገር ትችላለህ ብቻ ብዙ ነገሮች በነፃነት እየተገኘ ስለሆነ ቢፈልጉ ማድረግ ስለሚችሉ ረሀቡ ወደ ቅንጦት ተዘዋውሯል ለሌላ ነገር ቅድሚያ እየሰጠን መንፈሳዊ ነገሮችን ወደሗላ መገፍተር ጀምረናል በዛ ላይ ደሞ አንዳንዴ ዋጋ ከፍለህ የምታገኘው ነገር እና እንዲሁ በነፃ የምታገኘውን ነገር ስትጠቀም አጠቃቀምህ አንድ አይነት አይሆንም ። ለከፈልክበት ነገር ይበልጥ ትጠነቀቃለህ ለነፃው ነገር ግን ብዙ ትኩረት አትሰጠውም እና በግልፅ የሚታየው እየሆነ ያለው ይሄ ነው ፤ እንዳልከው ጭራሽ አሁን ላይ በደንብ መትጋት ሲገባን ጥቂቶች ግን የማይሆን ነገር ሲያደርጉ ይታያል ግን ማወቅ ያለብህ ነገር ቃሉም ቢሆን ስለሀሰተኛ ነብያት ስለሚናገር ከእነሱ ተጠብቀህ በፍፅም ልብህ ጌታ እግዚአብሔር አምላክህን ተከተለው



ሰዎችን ካየህ ትስታለህ እግዚአብሔር ካየህ ደሞ ታተርፋለህ በዛው ልክም ደሞ አብዛኛው አማኝ ማህበረሰብ ፈሪሀ እግዚአብሔር ያለው እና ቃሉን ለመኖር የሚጥር ሰው ነው ቢሆንም ግን የተበላሽ ፍራፍሬ ከጤነኛው ጋር አብሮ ሲቀላቀል እንደሚያበላሸው ሁሉ እኛም ብንሆን እራሳችንን ከሚያበላሹ አሳቾች መጠበቅ አለብን ። በንዴት ፣ በጥላቻ ፣ በክፋት ወይም በብልጣብልጥነት የሚሆን ነገር የለም መፍትሄው እውነት ነው ። እውነትን በመናገር ለእውነት  መኖር በንፁህ ልብ

   መፅሀፉን ለመቀጠል ጉጉት ቢኖረኝም ሶፋ ላይ እንደተንጋለልኩ በሀሳብ እሩቅ ነጎድኩ ጓደኞቼን ፣ እራሴን ፣ ዘመናችንን ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ፣ በህይወት የሌለው አባቴ ያሰፈረውን ቃል ብዙ ነገሮችን አብሰለሰልኩ ለምን ? ለምን ? ለምን ? እንደዚህ ሆነ የሰው ልጅ ልብ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ምነው ደነደነ ፈጣሪውን እረሳ በምን መልኩ ወንጌልን ብንሰብክ ልባቸው ይራራል ? ኢየሱስን ያልተቀበለ እኛን ያምናል ? የኛስ አካሄድ ወዴት ወዴት ነው አንድ ክርስቶስን እኛመንን አንድ ሺ የሳተ ትምህርቶችን አዛብተን እናስተምራለን ፤ አዳንን እያልን በግብዝነት ስንቶቻችን ነን ገደል ጠራርገን ፤ ተጠራርገን የምንገባው ? ከመመካከር ፣ ከመወያየት ፣ ከመተራረም ይልቅ ጉዳችንን እየሸፋፈንን የሆዳችንን በሆዳችን ይዘን ሌሎች ላይ ጣታችንን የምንቀስረው ? የኛ መበላሸት ሳያንሰን በድርጊታችን እና በሁኔታችን የማያምኑ እንዳያምኑ ሊያምኑ ጫፍ የደረሱ አፈግፍገው እንዲሸሹ ምክንያት የምንሆነውስ ስንቶቻችን ነን ? እጅግ በጣም ብዙ ብቻዬን አስቤ መልስ ያጣሁለትን ጥያቄ ከማሰብ ገታ ብዬ ያቆምኩትን ፅሁፍ ለመቀጠል ገለጥ  ፣ ገለጥ አደረግኩት ....ይቀጥላል
#share
ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur