Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፴፯ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፴፯
@yanetmasra

እሷን የመለሱ እየመሰላቸው ጭራሽ መከራዋን አበዙት ት/ቤት ተምራ ብትመጣም ቤት ውስጥ ያለው ሀላፊነት እሷ ላይ ወደቀ ቤት ውስጥ ካሉ ልጆች በተለየ እሷ ላይ የስራ ጫና እንዲሁም ታናናሾቿን የመንከባከብ ሀላፊነት ተጣለባት ትዝ ይለኛል ለማጥናት ጊዜ ስለሌላት ከት/ቤት መልስ ስራዋን ሰርታ ከእንቅልፋ ተሻምታ ታጠና ነበር ባንድ በኩል እናቷ ጤናቸው ወሰድ መለስረ ያደርጋቸዋል አባቷ ደግሞ ቄስ በመሆናቸው " አሰደብሺኝ የሰው መሳቂያ መሳለቅያ አደረግሺኝ በተከበርኩበት ሀገር የመዋረዴ ምክንያት ሆንሽ በሄድኩበት ሁሉ  'የቄስ ከበደ ልጁ ጴንጤ ሆና አረፈችው ' እያሉ በአፋቸው ያላምጡኛል ባንቺ ምክንያት አንገቴን ደፋሁ አንቺ ከምትወለጂ የእናትሽ ማህፀን ደረቅ ቢሆን ይሻል ነበር "ይሏታል አንዳንድ ጊዜ ምርር ሲላት ቅዳሜ ቅዳሜ ስንገናኝ ከህብረት በኋላ ለሁላችንም ትነግረናለች "በቃ የአባቴ ጭቅጭቅ ሲበዛ ፣ የቤቱ ስራ ሲበዛብኝ ብን ብለሽ ጥፊጥፊ ይለኛል መኖር ምርር ሲለኝ ደግሞ በትምህርትም ተስፋ እቆርጥና የማጠናበትን ጊዜ በእንቅልፍ አሳልፋለሁ ከኔ ጋር ፉክክር ውስጥ በመግባታቸው ምክንያት ታናናሾቼን አያሰሯቸውም ልክ እንደ ቤት ውስጥ ሰራተኛ ሆኛለሁ ሌላው ቢቀር ወንድሞቼ እና እህቴ ካላቸው ነፃነት የተነሳ እንደ ታላቅ እህት ሳይሆን እንደ ሞግዚት ሊያዙኝ ይፈልጋሉ ብቻ የእግዚያብሄር ቃል ስለሚያበረታኝ እና የእናቴም ጤና ስላልተስተካከለ በዚ ሁኔታ ውስጥ ጥያቸው ብወጣ ምን ይሆናሉ ብዬ አስባለሁ እንጂ በፊት ቤታቸው እንድኖር የፈቀዱልኝ ሰዎችም ቢሆኑ ቤታቸው ለኔ ሁሌ ክፍት እንደሆነ ይነግሩኛል መሄድ እንደምችል ባውቅም ልቤ ግን ጨክኖ መሄድ አልቻለም ብቻ የኔ ነገር ግራ እየገባኝ ነው እራሴን ለማጠንከር ብሞክርም መልፈስፈሴ አልቀረም



የሆነ የሚመክረኝ እና የሚያወራኝ ሰው እፈልግ እና እኔን ተረድቶ ምክር የሚሰጠኝ ሰው በዙሪያዬ አጣሁ ስለዚህ ያለኝ አማራጭ በውስጤ መብከንከን ስለሆነ በትንሹም በትልቁም ይከፋኝ ጀምሯል ፤ እዚህ የምነግራችሁም ለራሴ መቻል ሲያቅተኝ ብታዳምጡኝ እና ብትመክሩኝ ብዬ ነው " ትለናለች እንደ ወተት የጠራው አይኗ እንባዋን ፍልቅ ፍልቅ ያደርጋል ያን ጊዜ ሆዴ ውስጥ የሆነ ገብቶ ያለ ነገር ይመስላል አንጀቴ ይላወሳል በዚህ ጊዜ ከኔ በተሻለ ሴቶች እህቶቻችን እንዲሁም የፀሎት ህብረታችን መሪ ምክር ይሰጧታል እንደውም አንድ ሰሞን ብዙ ጊዜ አብዝተን ስለሷ እንፀልይ ነበር ሁኔታዋ ከቀን ወደ ቀን እየባሰ ሄደና ለረጅም ጊዜ ህብረት ሳትመጣ ቀረች መጀመሪያ አከባቢ በቃል እውቀት የበረታች ስላልነበረች የመዳከም ነገር ይበዛ ነበር ኋላ ግን ከቀን ወደ ቀን መበርታቷ እየጨመረ መቶ ለኔ እስከሚያስደንቀኝ ድረስ ብስለቷ አስገረመኝ ከኔም በተሻለ ብርቱ ሆነች የቀረችበትንም ምክንያት ስንጠይቃት የእናቷ እህት ከገጠር መጥተው ሁኔታውን ሁሉ ሲሰሙ ሀይለኝነታቸው ተባብሶ ጭራሽ ከቤት እንዳትወጣ አደረጓት አመጣጣቸው የታመመች እህታቸውን ለመጠየቅ ቢሆንም ሶስተኛ ሰው ሆነው ከቤተሰቦቿ በላይ ጫናን እና ቁጥጥርን አበዙባት እናቷ ህመማቸው እያየለ ፋታ ስለነሳቸው ከሷ በላይ ጤናቸው ላይ ጭንቀት አብዝተዋል ታድያ ለወራት የቆዩት አክስቷ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲመለሱ እሷም ወደ ፀሎት ህብረት ተመለሰች ሁሉም ምስራቅ የት ሄደች ብሎ በልቡ የሚያብሰለስለውን ነገር እና በጋራ የሚወያዩበትን ጉዳይ የመምጧቷ ነገር ሲሰማ በማከታተል ምክንያቷን ጠየቋት የገጠማትን ስትነግረን እኔንም ጨምሮ ስለሷ መጥፋት የተጨነቀ ሁሉ "ዋናው ሠላም መሆንሽ እና መመለስሽ ነው አልናት....ይቀጥላል


ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur