Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፴፭ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፴፭
@yanetmasra

ይሄን ታሪክ አውቀዋለሁ ስሟም አዲስ አልሆነብኝም የምስራች የእናቴ ስም ነው ታሪኳም እዚህ መፅሀፍ ላይ እንደሰፈረው ነው ለሰአታት ተመስጬ ሳነበው የነበረውን የአባቴን ታሪክ ከድኜ ወደ እናቴ ሄድኩ እናቴ መኝታ ክፍሏ ጋደም ብላ ነበር ያገኘሗት " እማ አንድ ነገር ልጠይቅሽ ነበር እዚህ ፅሁፍ ላይ ካንቺ ጋር ተመሳሳይ ታሪክ እና ስም ያላት ልጅ ሳነብ አጊንቻለሁ አንቺ ነሽ ወይስ አስገራሚ ምስስሎሽ ነው " ብዬ ጠየቅኳት ጋደም ካለችበት ለመነሳት እየሞከረች " አንብበህ ብትጨርሰው እኮ ሁሉንም ትረዳው ነበር " አለቺኝ እኔም እንዳላስቻለኝ ነግሬ ከአንደበቷ ማረጋገጥ እንደምፈልግ ነገርኳት እሷም ቀጠል ብላ " አዎ እኔው ነኝ ይሄ አስገራሚ ምስስሎሽ ሳይሆን እውነታ ነው መጀመሪያ አካባቢ ላይ ከትውውቆሽ ከዛም ሲዘል ከጓደኝነት ውጪ ምንም አልነበረንም ሗላ ላይ ግን የፍቅር ግንኙነት ጀመርን ተጋብተንም አንተን የመሰለ ሸበላ ወለድን " አለቺኝ ፈገግ ብላ ይሄን ስሰማ ይበልጥ ታሪካቸውን ለማወቅ አጓጓኝ " እስቲ አብራሪልኝ ? " ብዬ ስጠይቃት " እኔ ከምነግርህ በላይ አባትህ እሱ የያዝከው መፅሀፍ ውስጥ ቁልጭ አድርጎ እያንዳንድን ክስተት ዘርዝሮታል ይልቁንስ አንብበህ ጨርስ እና እናወራበታለን "  አለቺኝ በሀሳቧ ተስማምቼ መፅሀፉን መጀመሪያ ባነበው ይሻላል ብዬ ወሰንኩ ከዛ በፊት ግ " እማ መፅሀፉን ሳነበው በጣም ተገርሜም ፣ አዝኜም ፣ ካሁኑ ጊዜ ጋርም አመዛዝኜው ነበር ጠዋት ተናድጄ ባልኩት ነገር እራሱ አፍርየለሁ የእውነት እናንተ በዛን ወቅት መከራውን ፣ ስደቱን ተቋቁማችሁ ወንጌልን በመስበክ አደራችሁን በመወጣት ለኛ አስተላልፋችሁ ሳለ እኛ በዚ ጊዜ በጥቂቱ ነገር ስንበሳጭ ወይ ስንፈተን ቶሎ መናደድ እና ገፋ ሲልም " ባክ ለማድረግ "እንቸኩላለን ከበፊቱ የተሻለ ነፃነት ስናገኝ የበለጠ ከመትጋት እና ከመበርታት ይልቅ የስም ክርስቲያን መሆን እና ብዙ መተረማመስ ይታይብናል



አንዳንድ ወጣቶች ደሞ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሲኖሩ ሁሉን ነገር ቤተሰቦቻቸው እያደረጉላቸው በግላቸው ሳይበረቱ ይቀሩ እና ከቤተሰቦቻቸው የተለዩ ቀን ወደማይሆን ነገር ይገባሉ እኛ እራሳችን እራሱ ከበፊቶቹ ጋር ልንነፃፀር አንችልም እውነት መከራ ቢመጣ አሜን ብሎ በፀጋ መቀበል እንችላለን ወይ ብዬ እጠራጠራለሁ አሁን እኮ እማዬ የበፊቶቹ አገልጋዬች በድህነት እና በታማኝነት ወንጌልን እየሰበኩ ለዛሬው ትውልድ እንዳላስተላለፉ አሁን ላይ ደሞ የእግዚአብሔርን ስም መነገጃ ያደረጉ ፤ ወንጌል ሳይሆን ሀብታቸው የሚያሳስባቸው ፤ ባስ ሲልም ህዝቦችን የሚያስቱ ፤ ኑሮሯቸው አርቴፊሻል የሆነ አገልጋዬች ብቅ ብቅ ከማለታቸውም በላይ እየተስፋፉ መጥተዋል አሁን ከቀድሞው ጊዜ በበለጠ መትጋት ሲኖርብን ጭራሽ እየተንሸራተትን መጥተናል ልላውን ተይው እና እራሴን እራሱ እንደ ሌላ ሰው ታዘብኩት ከዚ በላይ ወንጌልን መስበክ ሲኖርብኝ በወንጌል የሚመጣብኝን መከራ በማሰብ ተዝረክርክ ያለሁ ታውቅያለሽ ወንጌል ቅብብሎሽ ነው እኔ አወቅኩ ፣ ዳንኩ ብዬ የምዘጋው ነገር ሳይሆን ደሞ ለሌሎችም ያወቅኩትን አውቀው እንዲድኑ የምናገርበት ነው ካለዛ ልክ ' እንደ ጋን ውስጥ መብራት ' ይሆናል የኔ ማወቅ ታድያ ዋናው ልልሽ የምፈልገው ነገር ቢኖር እንዴት ነው መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ በማይገባበት ጊዜ ላይ ሆነን እንደቀድሞው ወይም  ከዛ በበለጠ መልኩ እምነታችን በድርጊት የምንገልፀው ? መቼ ነው ክርስቶስን መስለን ለክርስቶስ የምንኖረው ? የምድር የቅራቅንቦ ቡፌን ለማንሳት የምንስገበገበው እንስፍስፍነት ገታ አድርገን ለዘለአለሙ የምንንሰፈሰፈው እንደውም ሳስበው እግዚአብሔር አባታችን ነው ብለን ስንናገር ከዛ በላይም ደሞ እየተዳፈርነው ያለን ይመስለኛል ቁጡ መሆኑን ማወቅ የተሳነን ይመስላል ብቻ ጉድ ብዙ ነው አንድ እግዚአብሔር ያስተካክለው እንጂ ....ይቀጥላል
#share

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur