Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፳፯ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፳፯
@yanetmasra

ቤተሰቡ ተሰብስቦ ምህረትን በመጠበቅ በር በሩን ይመለከታል መምጫዋ ደረሰና በሩን ወከክ አድርጋ ገባች ገና የቤተሰቧን ፊት ከማየቷ በፈገግታ ተሞላች እማዬ ፣ አባዬ ፣ ወንድሜ እያለች በየተራ አገላብጣ ሳመቻቸው ሁሉም በደስታ አፀፋውን መለሱላት ምህረት ቀይ ዳማ ፣ ቁመቷ ለሴት ልጅ ረጅም የምትባል ፣ ፈገግ ስትል ጉንጮ ላይ ስርጉድ ያላት መልከ መልካም ልጅ ናት ። ማንነቴን ባለማወቋ ፊቷ ላይ የግርታ ስሜት ቢታይባትም ለሰላምታ እጆን በመዘርጋት " ሠላም ነው " አለቺኝ እኔም እጆቼን ዘርግቼ ሰላምታዋን ተቀበልኳት ከዛን ከቤተሰቦቿ ጋር ስትጫወት ፣ ስታወራ በማህል እረሱኝ ለነገሩ እኔን የሚያማክል ወሬ ስላልተወራ ነው የጨዋታው አንድ አካል ያልሆንኩት እውነትም ግን በሱፈቃድ እንደነገረኝ ምህረት በሳልና ብልህ ልጅ ናት የምታወራውን ነገር በሰማሁ ቁጥር ከእድሜዋ በላይ መብሰሏን ተረድቻለሁ በተለይ ደሞ የማያምኑትን አያቷ የማታምን መስላ እንዴት እንደምትንከባከባቸው ስትነግረን እና እንዴት በስውር እንደምታመልክ ስታጫውተን ተረገምኩባት ለነገሩ የእሷ ላቅ ያለ ስለሆነ ነው እንጂ በሱፈቃድም ቢሆን አስተዋይ እና መንፈሳዊ ህይወቱ የጠነከረ ልጅ ነው ። ማንነታቸው ከአስተዳደጋቸው ጭምር የመጣ ይመስለኛል ።

    ወደኔ በመመልከት " የበሱቃድ ጓደኛ ወይም ጎረቤት ነህ ከዚህ በፊት አይቼህ አላውቅም  "አለቺኝ በእርግጥ ብትፈልግም ከዚ በፊት ልታየኝ አትችልም ምክንያቱም እነሱ ወደሰፈራችን ከገቡ ገና ሁለት አመታቸው ነው እሷም ባለፈው አመት ስላልመጣች ልታየኝ የምትችለው ዛሬ ገና ነበር ። " ያው ሁለቱንም ነኝ ማለቴ ጎረቤቱም ጓደኛውም ነኝ " አልኳት ለጥያቄዎቿ አጭር ምላሽ ነበር የምሰጣት



" መልካም እንግዲህ በቆይታዬ ብዙ ጊዜ እዚህ የምትመጣ ከሆነ ከእኔም ጋር በደንብ እንተዋወቃለን " አለቺኝ ይሄን ጊዜ በሱፈቃድ ጣልቃ ገብቶ " እንግዳ አደለም አሁን የቤተሰባችን አባል ሆኗል ስለዚ ሁሌ እዚ ይኖራል " አላት ነገሩ ስላልገባት "ማለት " ብላ ጠየቀችው "ማለት እማ የሚኖረው ከኛ ጋር ነው በወንጌል ምክንያት ከቤተሰቡ ጋር ተጣልቶ ከቤት ስለወጣ እዚህ አብሮን ይኖራል ከጎረቤትም ከጎደኛም በላይ ወንድሜ ሆኗል ላንቺም ከእንግዲህ ታናሽ ወንድምሽ ነው " አላት " እውነት በጣም ደስ ይላል አንድ ወንድም ብቻ ነው ያለኝ እል ነበር ከእንግዲህ በሗላ ሁለት ወንድሞች አሉኝ ማለት እችላለሁ ፤ በነገራችን ላይ ለወንጌል ብለው ዋጋ የሚከፍሉ ሰዎች በጣም ነው የሚያስደስቱኝ በተመቻቸ መንፈሳዊ ህይወት ውስጥ ከሚኖሩት በላይ አባጣ ጎርባጣ በሆነው መንገድ ውስጥ ኢየሱስን የማያመልኩ የሚያስቀና የህብረት ህይወት አላቸው አንተም ከእነሱ መካከል በመሆንህ ልትደሰት ይገባል ለወንጌል የሚከፈል መስዋዕትነት መከራ ብቻ ሳይሆን እድልም ነው ስለተመረጥክ ደስ ይበልህ " አለቺኝ " አመሠግናለሁ ያልሽው ነገር ልክ ነው ባልመረጥ እና እግዚአብሔር ባያየኝ ኖሮ ይሄኔ ከሚሞቱት መካከል እየባዘንኩ እኖር ነበር ይሄ እንዳይሆን ደሞ እንድድን ተመርጫለሁ ሌላው ቢቀር ይሄ ብቻ ለኔ በቂ ነው " አልኳት " አዎ ከዚ በሗላ በነገር ሁሉ እግዚአብሔር ይረዳሀል እሱ አባት ነው ተስፋ ይሆናል ከቤተሰቦችህ ጋር ያለህ ግንኙነት ሁሉ እንደሚስተካከል እምነቴ ነው " አለች
  " በሉ ልጆች ጨዋታችሁን አቁሙና ወደ ማዕድ ኑ ክረምቱ ገና መጀመሩ ነው ሰፉ የመጫወቻ ጊዜ አላችሁ አንቺም ከመንገድ መምጣትሽ ነው እኛም ስንጠብቅሽ እህል አልቀመስንም ተሰብሰቡ እና እንብላ " አሉ አቶ ታሪኩ....ይቀጥላል


ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur