Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፳፮ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፳፮
@yanetmasra

አይኔን እየጠራረግኩ ከመኝታዬ ተነሳሁ "ዩሀንስ የት ሄደህ ነው የጠፋኸው ያልፈለግንህ ቦታ እኮ አልነበረም ሀገሩን ሙሉ አሰስነው ብንል ይቀለናል ፤ ፊትህ ደሞ ምንድነው ? ማነው እንደዚህ አድርጎ የደበደበህ ? አሉኝ አቶ ታሪኩ እኔን በመፈለግ የደከሙትን ድካም ከፊታቸው ማንበብ ችያለሁ ፤ አሳዘኑኝ ! እኔም መልሼ ለበሱቃድ እናት የነገርኳቸውን መልሼ ለነሱ ነገርኳቸው " እንዴ ከበሱፈቃድ ጋር አልነበራችሁ እንዴ ? ከምኔው ተለያይታችሁ ነው የደበደቡህ ? " በማለት የበሱፈቃድ አባት ጠየቁኝ   " እሱን የሆነ ልጅ ጠርቶት ለጥቂት ከመለያየታችን ነው እኔን ያገኙኝ ምን አልባት ኖሮ ቢሆን ግን የኔ እጣ ለሱም ነበር የሚተርፈው እንደውም እንደነገሩኝ ከሆነ ለሱ ያሰቡት ከኔም ይብስ ነበር አለመኖሩ በጣም የተሻለ ነው ካለዛ ምን ያረጉት እንደነበር የሚያውቀው  እግዚአብሔር ብቻ ነው እንደውም ከመንገድ ሁሉ ካየሀቸው ጠንቀቅ ብለህ መራቁ የተሻለ ነው " አልኩት እሱም መልሶ " እንዴ እንደሱማ አይባልም እንደውም አብሬህ ብሆን የተሻለ ነበር እንዲህ እስክትሆን  አይደበድቡህም ለክፉም ለደጉም 'ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሀኒቱ ' እንደሚባለው አብረን ብንሆን መልካም ነበር ብዬ አስባለሁ ፤ ባንደበድባቸውም የሚደበድቡህን እጋራህ ነበር " አለኝ ባይደበድብልኝም የተመታሁትን እንደሚጋራኝ ሲነግረኝ ከልቤ አሳቀኝ አርቆ አለማሰቡ ነው እንጂ ለቤተሰቡ እዳ ነበር የሚጨምረው በዚ ኑሮ ላይ ሁለት በሽተኛ ማስታመሙ እዳ ከመጨመር ውጪ ሌላ ትርፍ አይኖረውም " በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ " ማለት ይሄ ነው ። " ጉድ እኮ ነው ዘንድሮ ለመደብደብም መጋራትን ታስባለህ ሆ ! ሆ ! አሁን ዋናው ነገር ከዚ የባሰ የአፋ ነገር አለመፈጠሩ ነው የእናንተ መጎዳት መልሶ እኛንም ይጎዳናል በምትችሉት ተጠንቀቁ የቀረውን እራሱ እግዚአብሔር ያስተካክለዋል " ብለው የምክርን ተግሳፅ አቶ ታሪኩ ለገሱን ያን ቀን በዛ አለፈ የኔም ህመምና ቁስል መሽቶ በነጋ ቁጥር እየዳነ መጣ ።



  ክረምት እንደመሆኑ መጠን የበሱፈቃድ እህት እንደምትመጣ ከራሱ ከበሱፈቃድ አንደበት ሰማሁ ። አያቱ አሁን ደና ስለሆኑ እንደ ባለፈው አመት የሚያስቀራት ነገር አልነበረም  ልተዋወቃት በመሆኑ ብደሰትና ብቸኩልም በሌላ በኩል ደሞ ምን አይነት ሰው ትሆን ወይም የኔ ከነሱ ጋር መኖር ምቾት አይሰጣት ይሆነሸ ብዬ ማሰቤ አልቀረም ፤ እንደ  እውነቱ ከሆነ ብዙ ሰው አዲስ ሰው ለመተዋወቅና ለመቅረብ ይከብደዋል እኔም ብሆን እንደሱ አይነት ስሜት ነበር የተሰማኝ ።

    አስታውሳለሁ ቅዳሜ ነበር ቀኑ ምህረት ትመጣለች የተባለው በዛን ቀን ነበር የበሱፈቃድ እናት ደስታቸው ፊታቸው ላይ ጎልቶ ይታያል እንደ ህፃን ልጅ መቦረቅ የቃጣቸው ይመስላል ለነገሩ ልክ ናቸው እንደ ዘመን መለወጫ በአመት አንድ ጊዜ እየመጣች መናፈቃቸው አይቀርም ሊያውም ያለፈውን አመት ቀርታ ። ታድያ የእናት ነገር ሆኖ መሰለኝ ከሁሉም በላይ ሊያዯት የጓጉ ይመስላሉ በሱፈቃድም ቢሆን እንደ እናቱ ባይንሰፈሰፍም ሊያያት ግን ናፍቋል ፤ አባቷም ቢሆኑ አገልግሎት ስለነበረባቸው እንጂ የወጡት ልጃቸውን ለማየት የቸኮሉ ይመስላሉ ታድያ ከመሄዳቸው በፊት " እንደጨረስኩ ቶሎ ነው የምመጣው ከመድረሷ በፊት ቀድሜ እደርሳለሁ " ብለውናል እኔ ግን ስለማላውቃት ነው መሰለኝ የደስታም የሀዘንም ስሜት አልታየብኝም ነበር ብቻ " ማን ትሆን ? የቤተሰቡን ትኩረት እንዲህ ስባ ልባቸውን በናፍቆት  ያራደችው ስል እራሴኑ ጠየቅኩት በትዝብት እየተመለከትኩ ። እኔም ለልጃቸው መምጣት ብለው ቤቱን የአመት ባህል እያስመሠሉ ጉድ ጉድ የሚሉትን እናቷ እቃ በማቀባበል አግዛቸው ነበር ....ይቀጥላል


ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur