Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፳፫ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፳፫
@yanetmasra

" ቀኔ መጥፎ ነበር ከትምህርቴ ቤት ልጆች ጋር ተጣልቼ እንደዚህ አድርገው ለቀቁኝ ነገር ግን መንገድ ላይ መሄድ አቅቶኝ ወድቄ ሳለሁ የሱ ቤተሰብ የሆነች አንዲት ሴት አግኝታኝ ቤቷ ወስዳ ተንከባከበቺኝ ራሴን ስቼ ከወደቅኩበት ሰአት ጀምሮ እስካሁን ድረስ እነሱ ጋር ቆይቼ ስነቃ ወደናንተ መጣሁ እንደምትጨነቁ በጣም እርግጠኛ ነበርኩ ነገር ግን ምንም ማድረግ አልቻልኩም ያለኝ አማራጭ ቶሎ መምጣት ነው በጣም ይቅርታ " አልኳቸው " ዋናው መምጣትህ ነው ግን አልተረፍክም እኮ ፊትህ ራሱ ብልሽትሽት ብሏል እኔ አፈር ልብላለህ ካለወትሮህ ስትቆይ ጊዜ ደብድበውት ይሆን ብዬ መጠርጠሬ አልቀረም ነበር ልቤ ራሱ አላረፈም ግን ምን ልሁን ብለው ነው እንደዚህ ያደረጉህ በትምህርት ቤት ጉዳይ ነው ወይስ በዚ በሀይማ..." አላስጨረስኳቸውም " እህ እያመመኝ ነው ንፋሱ ሲነካኝ ወደ ቤት እንግባና እናወራለን " አልኩ አዬ የኔ ነገር ሀሳቤ ተበታትኖ እደጅ መሆናችንንም ረሳሁት ና ግባ ልጄ " አሉኝ ሊሸኘኝ የመጣው ልጅ ተመልሶ ስላልሄደ ወደ ቤት እንዲገባ ብንጠይቀውም ስለመሸ መሄድን መረጠ እኛም አላስጨነቅነውም አመስግነን ተሰናበትነው ። የተመታሁበትን ምክንያት እሱ ፊት ማውራት ስላልፈለኩ ነበር ወሬውን ያቋረጥኳቸው እዛ ስጠየቅ ከተማሪ ጋር ተጣላሁ ብዬ እዚ ደሞ በሀይማኖት ምክንያት ነው ብል ውሸታም መስዬ መታየት ነው እሱን ደሞ አልፈለኩም ከዛ በሗላ ግን የተፈጠረውን አንዳች ሳላስቀር ነገርኳቸው የምር አለቀሱ በጣም ደነገጥኩ በሱፈቃድ እና አባቱ ሲመቱ ጥልቅ ስሜት ቢሰማቸውም ከአይናቸው ግን እንባ አልፈሰሰም ነበር በኤ ምክንያት ግን ሲያለቅሱ በጣም ተደናገጥኩ " ለምን ያለቅሳሉ ደና እኮ ነኝ ፤ ብዙ የተጎዳሁ መስሏችሁ ነው እንዴ ? " አልኳቸው ትክዝ ብለው " አዬ ዩሀንስ ምኑን ደና ሆንህና ደና ነኝ ትላለህ ደና አለመሆንህን ይኸው እያየሁት ደሞ ማልቀሴ አሳስቦህ ከሆነ ስለኔ አታስብ ከሆዴ ያጠራቀምኩት ብሶት ግንፍል ብሎብኝ ነው



ባለፈው ባለቤቴ እና በሱፈቃድ ተደበደቡ እሱ አለፈ ዋናው ደና መሆናቸው ነው ብዬ ራሴን ፅናናሁ መጎዳቴን ፣ ማዘኔን አይታችሁ እንድትደክሙና እንድታዝኑ ማድረግ አልፈለግኩም ዛሬ ግን አንተ እንዲ ሆነህ ሳይህ አላስቻለኝም መከራችን በዛ ፤ ጥላቻቸው ያለ ልክ እደገፋ መጣ በኔና በባለቤቴ ላይ የፈለጉትን ቢያረጉ አይገርመኝም በልጆች ላይ ግን ይሄን ያህል ጭካኔ ሲደረግ በጣም ያሳዝናል ግን ብከፋም ፣ ባዝንም ምንም ብሆን እግዚአብሔር ከጎኔ መሆኑን መቼም አልረሳም ከዚ መከራና ጭንቀት አንድ ቀን ይገላግለናል አምናለሁ ቃሉና የተናገረው ነገር አንድ ቀን እውን ይሆናል " አሉኝ አይናቸውን ቡዝዝ አድርገው በሀሳብ ማዕበል ተዋጡ ጭልጥ ...አሉ ዝም ብዬ ሳያቸው ቆየሁና በማህላችን ያለውን ዝምታ ለመገርሰስ ስል "በሱፈቃድ የት ሄዶ ነው እስካሁን ያልመጣው አባቱም ቆዩ እንዲ አያመሹም ነበር " አልኳቸው "ውይ !ውይ ! ሞት ይርሳኝ አንተኑ ፍለጋ እንደወጡ አልተመለሱም አዬ አሁን የት ብዬ ልፈልጋቸው ወይ እስኪመጡ መጠበቅ ነው እንጂ ...ቆይ ግን እኔምልህ ብዙ ጊዜ እነግርሀለሁ ብዬ አስብና እረሳዋለሁ ለምንድነው አንቱ እያልክ የምትጠራን በዛ ላይ የበሱፈቃድ እናትና አባት እያልህ ነው የምትጠራን እኛ አደለንም አላልን የውጭ ሰው ብትሆን እሺ እንደ ቤተሰብ እየኖርን ግን እንዲ ማለቱ ደግ አይደለም አንቱታህን ተውና ብትፈልግ እማዬ አልያም እቴቴ በለኝ እሱንም ቢሆን አባዬ ወይም ያሻህን ስም አውጥተህ በለው አይከፋውም " አሉኝ " እሺ እርሶን እቴቴ እሎታለሁ እሳቸውን ደሞ ጋሼ ብላቸው ይሻለኛል አንቱታውን ግን ባንዴ መተው ይከብደኛል ቀስ ብዬ እተወዋለሁ " አልኳቸው ....ይቀጥላል


ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur