Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፳፪ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፳፪
@yanetmasra

" ልጄ ተነሳህ እንዴት ነህ ?" አለችኝ።ጭንቅላቴን እየነቀነቅኩ ደና መሆኔን ገለፅኩላት ቀጥዬም " የት ነው ያለሁት እናንተ እነማን ናችሁ?" ብዬ ጠየኳት እሷም ከገበያ ስመለስ ወድቀህ አገኘሁህ ክፉኛ ተጎድተህ ስለነበር ወደ ቤት አስገብተን ቁስልህን ጠራረግንልህ። ማነው ግን እንደዚ ጨክኖ የደበደበህ ሰው በሰው ላይ እንደዚ መጨከን ይከብዳል።አለችኝ እኔም ትምህርት ቤት ከልጆች ጋር በትንሽ ነገር ተጋጭተን ዛሬ የአመቱ መጨረሻ መዝጊያ ስለሆነ እንደዚ አርገው ደብድበውኝ ሄዱ። አልኳት ...."እኔን! ምን አይነት ጨካኝ ልጆች ናቸው ይሄን ያህል ምን ብታደርጋቸው ነው!?" አለችኝ። እውነቱን መናገር አልመረጥኩም እሷ ምን መሆኗን በምን አውቃለሁ....ጴንጤ መሆኔን ብታውቅ ኖሮ እንኳን ልትንከባከበኝ ልትረዳኝ ቀርቶ እሰይ ይበሉህ ብላኝ ልትሄድ ትችል ነበር ማን ያውቃል። ያው ከጥያቄው ግን መሸሽ ስለማልችል "... ፈተና እንዳስኮርጃቸው ጠይቀውኝ ሳላስኮርጃቸው ቀርቼ በዛ ቂም ይዘውብኝ ነው ዛሬ እልሀቸውን የተወጡብኝ እኔ ደግሞ ብቻዬን ነኝ እነርሱ ከአምስት ያልፋሉ።ሳልችላቸው ቀርቼ እንደዚ ተጫወቱብኝ" አልኳት። አጠገቧ ያለችው ልጅ ቀደም ብላ " እውነት ነው ሰርተፍኬቱን ሳየው ነበር አንደኛ ነው የወጣው ጎበዝ ልጅ ነህ ደግሞ የምን ማስኮረጅ ነው ደግ አደረግክ። ዝም ብለው አመቱን ሙሉ ሲዘሉ ይከርሙና ልክ የፈተና ቀን ይጉረጠረጣሉ። የሞቱ። አንተ ቆይ ለምን ለአስተማሪ አትናገርም እንደዚ ያደረጉህን ልጆች ጠቁም ካልሆነ ቤተሰብህ ጋር ሄደህ መናገር ነው አንተን ባይሰሙህ እነርሱን ይሰማሉ" አለችኝ። ቤተሰብ ስትል ቤተሰቦቼ ትዝ አሉኝ አሁን በዚ ሰአት ምን እያሰቡ ይሆናል ብዬ ተጨነቅኩ። ወደ በሩ አይኔን ሳማትር ጨላልሟል በፍጥነት ከተኛሁበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁ



ግን አነሳሴ ልክ ስላልነበር ጎኔ አካባቢ የተመታሁት ቦታ ላይ ወጋኝ ህመሙ አየለብኝና መልሼ ተቀመጥኩ "እንዴ ምን ሆነህ ነው ?ምን ነካህ የማይሆን ነገር አወራሁ እንዴ ፤ ከና ከመናገሬ ቤቱን ጥለህ ለመውጣት ቸኮልክሳ " አለቺኝ የሁሉም አይን እኔ ላይ ሆነ በሌላ በኩል ደሞ የህመሜ ምክንያት ትንሽም ቢሆን ያስደነገጣቸው ይመስላል " ኧረ አንቺ ምንም አላደረግሽኝ ድንገት ቤተሰብ ስትዪ ቤተሰቦቼ ትዝ ብለውኝ ነው ጠዋት የወጣሁ እስከማታ ሳልገባ ስቀር ስንት ክፉ ክፉ ነገር ያስባሉ ብዬ ፈርቻለሁ ደሞ ሰማዩም ጠቋቁሯል ቶሎ ካልሄድኩ ልባቸው አያርፍም ይሄኔ እዛ እየተፈጠረ ያለውን ነገር የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው ስለዚህ ልሂድ ስላደረጋችሁልኝ ነገር በጣም አመሠግናለሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ ባይሆን ሌላ ቀን መጥቼ እጠይቃችሗለሁ " ብዬ ለመሄድ ተነሳሁ መጀመሪያ ያወራችኝ ሴትዬ " ቆይ እንጂ ከሄድክም ብቻህን አትሄድም በዚ በማታ አሞህ ብቻህን እንድትሄድ አላደርግህም " ማነህ አብርሀም እስከሰፈሩ ሸኘው "ብላ ከጓዳ አንድ ሰው ጠራች ልጁ ወደ ሀያዎቹ መጀመሪያ ይገመታል ቁመቱና ሰውነቱ ሲታይ የሰማይ ስባሪ ያህላል እንኳን ሰው አደለም ከሱ ጋር ሆኜ ንፋስ አይነካኝም ። እንዳለችው ከልጁ ጋር መንገድ ቀጠልን ። ዝምታው በጣም ያስፈራል ! እቤት እስከምንደርስ ድረሰ አንድ ቃል አልተነፈሰም ለነገሩ እኔም ብሆን ህመሜን እያዳመጥኩና ቤተሰቦቼ ምን ያስባሉ የሚለውን እያንሰላሰልኩ ነበር ገና ወደደጃፉ ከመጠጋቴ የበሱፈቃድ እናት "ዩሀንስ ! ዩሀንሴ !  "  እያሉ ወደኔ መጥተው ከእቅፋቸው አስገቡኝ " የት ሄደህ ነው ? ፊትህ የቆሳሰለው ከማን ጋር ተጣልተህ ነው ? አንተንም ደበደቡህ እንዴ ...? " ብዙ ነገር አሉ ፤ እንደ እውነተኛ  እናት እንስፍስፍ አሉልኝ ። በሳቸው ዘንድ እንዲ መወደዴ አስደሰተኝ ....ይቀጥላል


ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur