Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፳፩ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፳፩
@yanetmasra

ሲቆይ የተረሳ ቢመስልም መሆኑ የማይቀር ሆኖ የአመቱ መጨረሻ ላይ ለመዝጊያ ፕሮግራሙ ድምቀት ብለው ይሁን ወይም ደሞ ጥላቻቸው ገንፍሎ መቋቋም ስላቃታቸው መሆኑን ባለውቅም ከበር ሊደበድቡኝ አድፍጠው ጠበቁኝ ገና ሳያቸው መትረፌን ተጠራጠርኩ አንዴ ብቻ ወደ ሰማይ ቀና ብዬ " ጌታ ሆይ ነፍሴን ተቀበላት" አልኩ መመለስ የማልችልበት  ሁኔታ ውስጥ ሆኜ እግሬን ለመንገድ አዘጋጅቼ ያላየዋቸው  በመምሰል  ለማለፍ ጣርኩ ግን አልተሳካልኝም አንደኛው ከመሀከላቸው ተስፈንጥሮ መቶ ትከሻዬን ነካ አደረገኝ እየቀፈፈኝ ዞርኩ ማንነትን በሚያስረሳ ቦክስ እንዴ ሲለኝ ከመሬቱ ተጣበኩ  አፍንጫዬም አለመሰበሩ እግዜር ሲረዳኝ ነው። ታድያ በዛ ቦታ  ሆኜ ከአፍንጫዬ የሚፈሰው ደም ሳስተውል በሱፍቃድ በሀሳቤ ውልብ አለ ባለፈው ለካ ወዶ አይደለም "ደና ነኝ ከአፍንጫዬ የወጣ ንስር ነው "ያለኝ ባንዴ ደሙያበሻቅጣል እነሱም የክፋታቸው ክፋት በዛ አልበቃ ብሏቸው በእግራቸው እንዴ ጀርባዬን ፣ ከዛ ሆዴን ፣ እግሬን ደስ ያለው ደግሞ እጄን ደገም ደገም አርገው   በመዘንዘር ተረባረቡብኝ ካላማጋነን የሞት ደጃፍ አድርሰው መለሱኝ ብል ውሸት አይሆንብኝም በዛ ላይ እየተደበደብኩ መልስ እንድመልስላቸው ጥያቄ አይሉት ሀሳብ በንግግራቸው ያንፀባርቁብኛል " ይሄ በሱፍቃድ የት ሄዶ ነው ? አመለጠን ማለት ነው ? እንጂ ካንተ በላይ ዋናው እሱ ነበር መቅመስ የሚገባው የት አባቱ ሄዶ ነው " ይሉኛል
ግራ ገባኝ የነሱን ጥያቄ ልመልስ ወይስ ህመሜን ላዳምጥ ደግሞ ስሙን ማወቃቸው ገረመኝ በዚህ አይነት የኔንም ያቁታል ብዬ ደመደምኩ ከዛን ለጠየቁኝ ነገር መልስ ሳልሰጣቸው ቀረሁ  ሆኖም ግን አልተውኝም " አንተን አይደል የምለው " ብሎ አንዴ በሀይል ጀርባዬን ሲመታኝ አይኔ እንደፈጠጠ "እኔጃ አላውቅም" ብዬ መለስኩለት እሱም "ያመለጠ መስሎታል ሂድና ቀንህን ጠብቅ አይቀርልህም ብለህንገረው አንተም ደግሞ አላርፍ ካልክ በዚ አያበቃም እንደግምሀለን" አለኝ



ጥፋቴ ምን እንደሆነ ባላውቅም እሺ አልኳቸው። በዛን ሰአት እውነት ግን በሱፈቃድ የት ሄዶ ነው ብዬ አሰብኩ ምክንያቱም ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አብሮኝ ነበረ። ብቻ አንድ የክፍሉ ልጅ ጠርቶት መጣሁ ብሎኝ እንደሄደ አስታወስኩ ትረፊ ያላት ነፍስ መውጫዋና ማምለጫዋ አይታወቅም ይሄ ልጅ ምክንያት ሰጥቶ ባይጠራው ኖሮ ይሄኔ ከጎኔ ወድቆ አየው ነበር ብዬ አሰብኩ። ደሞ በሌላ በኩል መልሶ ዛሬም ቢመታ ምን ያህል ያሳዝናል ብዬ ራሴው አዘንኩለት ግን ያም ሆነ ይህ የባለፈውን ህመሙን እና ስቃዩን ቀመስኩለት። ውልቅልቅ አድርገውኛል። ደሞ የጠበቁኝ ቦታ ጭር ያለ በመሆኑ ማንም አይቶ ሊያነሳኝ የሚሞክር አንድም ሰው ጠፋ መጨረሻዬ እዚሁ ወድቆ መቅረት መሆኑን ሳስብ ለራሴ ራሴው ደጋፊ ሆኜ እግዚአብሔር እንደሚያግዘኝ እያሰብኩ ተነሳው። ልክ እንደ ሰከረ ሰው ወደዚ ወደዛ እንደ ንፋስ እየተወዛወዝኩ ቀኙ እጄ የተመታው ሆዴን ደግፎ ግራው ደግሞ ከትምህርት ቤት የተሰጠኝን የውጤት መስጫ ካርድ በደም እንጥብጣቢ ማህተም የተደረገበት እንደመሰለ ይዤው ጉዞ ቀጠልኩ ለስሙ ሲታይ አንደኛ ነበር የወጣሁት የነበሱፈቃድ ቤት ከኛ ቤት በተሻለ ለጥናት ስለሚመች ውጤቴ ከበፊቱ ይበልጥ ተሻሽሏል እናቴ ይሄን ብታይ ደስታዬ ነበር። ግን ሳያድለኝ ቀረ።

  መንገዴ ረጅም ሆነብኝ ብሄደው ብሄደው አላልቅ አለ። ከሌላው ቀን በተለየ መንገዱ ላይ መንገድ የተጨመረ እስኪመስለኝ ድረስ አሰለቸኝ። በዛም ላይ በዛ ፍጥነቴ ህመሜ ተጨምሮ የማያልቅ ሆነ በመጨረሻም ግን ተዝለፍልፌ ወደቅኩ።... ከደቂቃዎች በኋላ ስነቃ ራሴን ያገኘሁት ሰዎች ቤት ነበር። በግራና በቀኝ ከበው ያዩኛል ደሜ ከፊቴና ከእጆቼ ተጠርጓል ሊረዱኝ እንዳመጡኝ ብጠረጥርም እንዴት የሚለው ግን ጥያቄ ፈጠረብኝ ወዲያው አንዲት ሴትዮ.... ይቀጥላል


ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur