Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ከፍል  ፳፬ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ከፍል  ፳፬
@yanetmasra

"በል እንዳሻህ ጥራን ዋናው አንቱታህን መተውህ ነው አሁን አንተ ጋደም በል እኔ ወጣብዬ ትንሽም ቢሆን እነበሱፈቃድን አየት አየት አድርጊያቸው ልምጣ ስመለስ ደሞ አፍህ ላች የምታደርገው ነገር እሰራልሀለው " ብለውኝ ወጡ እኔም ብሆን እረፍት ለማድረግ ወደ ውስጥ ገባሁ የተቀጠቀጠው ቦታ ላይ እና የቆሳሰለው አካሌ ላይ ጥዝጣዜ እና ህመም ይሰማኛል ጋደም ያልኩበት ቦታ ላይ ሆኜ የት ሄደው ይሆን ብዬ አወጣ አወርድ ጀመር መቼስ እናቴ ጋር ይሄዳሉ ብዬ ተስፋ አላደረኩም እንደዛ ቢሆን ግን እጅግ በጣም መጥፎ ነገር ይፈጠራል ወይ እኔኑ መልሳ ደግ አረጉህ እሰይ እንኳን ተደበደብክ ትለኛለች አልያም ደሞ እኔን ! ብላ ነገሩን ወደነበሱፈቃድ ቤተሰቦች ትጠመዝዘዋለች እንኳንም ዘንቦብሽ ድሮንም ጤዛነሽ ይባል የለ እንዲሁም ከበሱፈቃድ እናት ጋር ተናቁራለች እንኳን ተደበደበ ተመታ ተብላ ሌላ ነገር እንዳታመጣ በውስጤ ተጨነቅኩ ፤የበሱፈቃድ እናትም ከወጡ ግማሽ ሰአት አለፋቸው ከዛ ግን በሩ ሲከፈት ተሰማኝ ባገኟቸው ብዬ በልቤ  በመመኘት አንገቴን ቀና አድርጌ ላያቸው ሞከርኩ ነገር ግን ብቻቸውን ነበሩ " ምነው አላገኟቸውም እንዴ ? " አልኳቸው " አዎ አላገኘሗቸውም የት ብዬ እንደምፈልገቸው ግራ ገባኝ ጭራሽ አየሗቸው የሚለኝም ጠፋ ለነገሩ ባልጠይቃቸው ነው የሚሻል የነበረው እንኳን አየሗቸው ሊሉኝ እኔን ሰው ብሎ ለጥያቄዬ መልስ የሚሰጠኝ አልነበረም እንግዲህ እግዚአብሔር በሰላም ያምጣቸው እንጂ በዚህ ምሽት የት ብዬ እፈልጋቸዋለሁ " አሉኝ  እኔም በልቤ ሳስብ የነበረውን ጠየቅኳቸው " መቼስ ጠፋ ብላችሁ ለእናቴ አልጠየቋትም አደል ፤ ማለቴ ጠፋብለው ነግረው ወይም አይተሽዋል ብለዋታል ?" አልኳቸው " አይ ልጄ ልጠይቃት ብዬ ካንዴም ሁለቴ ሄድኩና ተመለስኩ



መጀመሪያ ይፈልጉህና ከዛ ካልመጣህ እንጠይቃቸዋለን ብዬ ተውኩት አንተም ብትሆን ሳትነግረን እዛ ታመሻለህ ብዬ አላሰብኩም እሷም ብትሆን መጥፋትህን ሰምታ እንዲሁ እንደ ዋዛ ዝም አትልም መናገር እንኳን ቢኖርብኝም ነገሮችን አትረዳም ብዬ ዝም አልኳት " አሉኝ ለነገሩ ልክ ናቸው ሌላ ግር ግር ቤት ውስጥ መፍጠር ነው "ልክ ኖት እንኳን አልነገሯት ብትሰማም ለውጥ የለውም ለችግሩ መፍትሄ ሳይሆን ሌላ ችግር ነበር የምታመጣው " አልኳቸው እሳቸውም ጠጋ ብለው " እናትህ ለምን እንዲ እንደምትሆን ታውቃለህ ? በጣም ስለምትወድህ ነው ባሏ ሞቶባት ስትጎዳና ስታዝን አለኝ የምትለው አጋዧ አንተ ነበርክ ታድያ እሷ ወደማትፈልገው ነገር ስትገባና ስታጣህ ምን ይሰማት ይመስልሀል ባሏ ሞቶ ልጆ ከሷ ተለይቶ ልቧ በጣም ይጎዳል ስለኢየሱስ ስላልገባት እሳት ውስጥ የገባህ ፣ የምትሞት ፣ ሀጥያተኛ የሆንህ ከሀዲ አድርጋ ነው የምትመለከትህ ይሄ ደሞ እንዲሆን እንኳን እናት ለልጇ ማንም ለወዳጁ አይመኝም ላንተ መልካም ነገር ከመመኘት አንፃር ጉዳትህን አትፈልግም አሁን ያለህበት ነገር ደሞ ጉዳት ይመስላታል ስለዚህ ታዝናለች ሀዘኗን ልትረዳት ስላልቻልክ በብስጭትና በቁጣ ታወራሀለች የልቧን ጩኸት ነው አንተ ላይ የምታስተጋባብህ ትዳሯም ቤቷም ተበተነ በዚህ ሰአት እህቶችህን እንድትቆጣጠርና እሷንም እንድትደግፋት ትፈልጋለች ይሄ ግን ሊሆን አልቻለም በእሷ ቦታ ሆነህ ብትመለከታት ሀዘኗ ልክ ነው ባንተ ቦታ ሆና ልትረዳህ ስላልቻለች ለእናትህ መዳን አብዝተህ ፀልይላት ግን መቼም ቢሆን እንደ ክፉ አይተህ እንዳትጠላት እንደውም ከጎኗ ሁነህ ባስፈለጋት ሰአት ከጎኗ ተገኝ እየጨቆነችህም ቢሆን መልካም ሁንላት ከፍቅሯ የተነሳ ነው ቁጣዋን የምታሳይህ " አሉኝ ....ይቀጥላል


ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur