Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፲፯ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፲፯
@yanetmasra

የሚባለው ነገር እውነት ነው የምናውቀውንና የተገራንበትን ነገር ነው በህይወታችን የምናንፀባርቀው

    ቀን ቀንን እየተካ ወራቶችም ሲያልፉ ከቤት የመባረሬ ነገር እርግጥ ሆነ የእናቴ አንጀት ጨክኖ እንድወጣ ወሰነብኝ የተባልኩትን ከመቀበል ውጪ አማራጭ አልነበረኝም ያለቺኝን ጥቂት ልብስ ሰብስቤ ወደበሱፈቃድ ጋር ለመሄድ ተነሳሁ ካሁን ካሁን ተመለስ ትለኛለች ብዬ በብዙ ጠበቅኳት እሷ ግን ወይ ፍንክች ልቧ ደነደነ ይልቁንስ እህቶቼ በሀዘን ተሞሉ አይናቸው እምባ ቋጠረ እነሱን ባየሁ ቁጥር ውስጤ እርብሽብሽ ይላል በጣም ተላምጃቸዋለሁ ከዚህም የተነሳ አቅራቦታችን እየጨመረና ከበፊቱ አብልጬ እየወደድኳቸው ያለሁ መሰለኝ ከመሄዴ በፊት መለስ ብዬ ስምያቸው ለመሠናበት እንኳን እድሉን ሳላገኝ ቀረሁ ያጋደለውን በር ይለይልህ ብላ ጠረቀመችው እኔም የተዘጋ በር ማየቱ ሲሰለቸኝ እግሮቼን ለመንገድ አዘጋጀሗቸው ዘርጋ ዘርጋ እያረኩ ቅርዝዝ ብዬ እነበሱፈቃድ ደጃፍ ደረስኩ ዘው ብሎ መግባቱ ነውር መሠለኝ አለመግባትን መወሠን ደሞ መሄጃ ማደሪያ በሌለኝ ቦታ ወይ የጅብ እራት መሆን አልያም እጣዬ በረንዳ መሆኑ ታወሰኝ በመግባትና ባለመግባት መካከል ላይ ቆሜ ባለሁበት ቁጭ አልኩ የበሱፈቃድ እናት ውሀ ለመድፋት ከቤታቸው ወጣ ሲሉ ከተቀመጥኩበት አዩኝ " ዩሀንስ ምነው በር ላይ ተቀመጥክሳ አትገባም እንዴ ? ደሞ በእጅህ የያዝከው የምን ልብስ ነው ? "አሉኝ የምላቸው ጠፍቶኝ መሬት መሬት እያየሁ እንዳቀረቀርኩ ቀረው ያኔ የውሀ መድፊያውን እቃ አስቀምጠው ወደኔ ተጠጉ ፤ ቀርበውም በእጃቸው እራሴን እየዳሰሱ  " ዩሀንስ ምን ሆነሀል  ? እስቲ ንገረኝ እኔ እናትህ ማለት አደለሁ ለምን ትደብቀኛለህ ? አሉኝ እኔም " እናቴ ከቤት አባረረቺኝ ጴንጤ ሆንህ ብላ ፤ መሄጃ ስላልነበረኝ ወደናንተ መጣሁ ግን ደሞ ለመግባት ፈራሁ " አልኳቸው ለሰከንድ እንኳን ፊታቸውን ሳያጨልሙብኝ " ለምን ትፈራለህ ግባ እንጂ እዚሁ ከኛ ጋር እንደቤተሰብ መኖር ትችላለህ 



ምንም የሚያስፈራ ነገር የለውም ማንም በሌለህ ሰአት እንዴት ከንፈር መጠን የራስህ ጉዳይ እንልሀለን በፍፁም አናደርገውም አሁን በል ሀይለኛ ንፋስ እየተነሳ ነው ስለዚ ግባ " አሉኝ መልካምነታቸው ለኔ ተስፋ ሆነኝ የያዝኩትን ይዤ ወደ ቤት ውስጥ ገባሁ ማንም አልነበረም በሱፈቃድ የት ሄዶ እንደሆነ ባላውቅም እቤት ሳላገኘው ቀረሁ " ቁጭ በል ምንም ሀሳብ እንዳይገባህ እኛ የበላነውን እየበላህ እኛ የጠጣነውን እየጠጣህ ከኛ ጋር ትኖራለህ ከልጃችን ለይተን አናሳድግህም አንተ ከእንግዲ ከእግዚአብሔር የተሰጠኸኝ የአደራ ልጄ ማለት ነህ አንተም እንደ እናትህ እየኝ " አሉኝ በዚህ ግዜ ካይኔ እምባ ቀረረ " በጣም ነው የማመሠግነው በዚህ ሰአት እናንተ ባትቀበሉኝ የት እንደምሄድ አላውቅም ነበር እውነት ከልቤ ፈርቼ ነበር አሁን ግን ማረፊያ ስላገኘሁ ሌላው አያስጨንቀኝም ግን የበሱፈቃድ አባት ሲመጡ እና ሲያዩኝ ቅር አይላቸውም ማለት እሳቸው ሳይወስኑ እንድኖር ስለፈቀዱልኝ " ብዬ ጠየቅኳቸው ፤ አንደኛው ስጋቴ ይሄ ነበር " ኧረ እሱ እንደዚህ አያውቅም በተቃራኒው እንደውም ልቡንም ቤቱንም ከፍቶ ነው የሚቀበልህ እንደውም ቢችልና አቅሙ ቢፈቅድ ለወንጌል ተብሎ የተሰደደን ሠው ቢያኖር ደስታው ነው እኔ ካልኩህ ውጪ ምንም መጥፎ ቃል አይናገርህም እሱን እንደ አባት እኔን እንደ እናት በሱፈቃድን ወንድምህ እያየህ ትኖራለህ እናትህ ብትራራና ብትመልስህ ያኔ መሄድ ትችላለህ ካለዛ ግን ምንም ሳታስብና ሳትጨነቅ ቤታችንን እንደ ቤትህ ተመልክተህ መኖር ትችላለህ " አሉኝ እውነት እንዳሉኝም የበሱፈቃድ አባት ፊታቸውን ሳያጠቁሩ ተቀበሉኝ ቤታቸው ውስጥ ያለው መከባበር አስቀናኝ ሁሉም ደሞ በአንድ መንፈስ ሆነው እግዚአብሔርን በአንድነት ያመልካሉ መንፈሳዊ ቅናት ተሰማኝ ምናለ እኔና ቤተሰቤም እንዲ ብንሆን ብዬ ተመኘሁ ....ይቀጥላል


ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur