Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፲፰ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፲፰
@yanetmasra

ኑሮን ከነበሱፈቃድ ጋር አሀድ ብዬ ጀመርኩት የኑሮ ዘይቤያቸውን ፣ የቤተሰቡን ባህሪ ሁሉ ተላመድኩት ከጥቂት ጊዜ በሗላ እንደ እንግዳ ሳይሆን እንደ ነባር ቤተሰቡ አባል ሆንኩ ቤተሰቦቼ ጋር ሄጄ እንዳላገኛቸው እናቴ ፍቃደኛ ባለመሆኗ እህቶቼን ብቻ ከደጅ አገኛቸዋለሁ እኔ በመውጣቴ ምክንያት መፅሀፍ ቅዱስ ማንበብ እንዳያቆሙና የመንፈሳዊ ህይወታቸው ጉዞ እንዳይቋጭ ፈርቼ ነበር ምክንያቱም ችላ ማለት ነገሮችን እርግፍ አድርገን እንድንተው ምክንያት ይሆናል ታድያ እኔ የለሁም ብላችሁ ማንበብ እንዳትተው አጥኑ ብዬ በብዙ መከርኳቸው ንግግሬ ከመማፀን አይተናነስም በተለይ ደሞ ፍቅርተ ታላቅ ስለሆነች ሀላፊነቱን እንድትወስድ ጫናውን በሷ ላይ አደረኩ ደስ የሚለው ነገር ግን የኔ አለመኖር እንዳሰብኩት ክፍተት አልፈጠረም መፅሀፍ ቅዱሴን እቤት ትቼው ስለወጣሁ እናታችን ሳትኖር ተደብቀው እንደሚያነቡና በቀላሉ እንዳታገኘው ሸሽገዋት እንደሚያስቀምጡት ነገሩኝ ይህን ስሰማ ከልቤ ተደሰትኩ እግዚአብሔር እሱን አጥብቀው የሚፈልጉበትን ፍላጎት በልባቸው ስላስቀመጠ አመሠገንኩት ከመሠረት በላይ ደሞ ፍቅርተ በጣም ጠንካራ ሆናለች የእግዚአብሔርን ነገር አጥብቃ ይዛለች ለሱም ደሞ ማሳያ የሚሆነው በፀባይዋ በጣም ብዙ ለውጥና መሻሻል እያየሁባት ስለሆነ ነው ፤ መሠረትም የእሷን ፈለግ እንደምትከተል እምነቴ ነው እናም ይህን ከነገሩኝ በሗላ እኔ እነበሱፈቃድ ጋር ሁለት መፅሀፍ ቅዱስ ስላለ የኔን ለነሱ ልተውላቸው ወሰንኩ ግን ደሞ እናቴ ካየች ከኔ የከፋ ነገር እነሱ ላይ ልታደርግባቸው እንደምትችል አውቅ ስለነበር እጅግ በጣም እንዲጠነቀቁ አበክሬ ነገርኳቸው ምክንያቱም የሚመጣባቸውን ችግር በዛ እድሜያቸው ለዛውም ሰው ሳይኖራቸው ይቋቋሙታል ብዬ በፍፁም አላስብም ደሞ ታላቃቸውም ስለሆንኩ ይሆን ወይም አባት ስለሌለን ጉዳት ላይ እንዳይወድቁ በጣም እሳሳላቸዋለሁ



እኔም ብሆን መጠለያና ቤተሠብ ባገኝም ባጠቃላይ ግን ክርስቲያን የሆነው ህብረተሰብ ላይ የሚደረግበት ጥላቻ እየነገሠ መጣ አንድ ቀን ሀገር ሰላም ብለን በተቀመጥንበት ሰአት አገልጋዬች ላይ ድብደባ እንደተፈፀመ ሰማን በወቅቱ ደሞ የበሱፈቃድ አባት አቶ ታራኩ አገልጋይ ስለሆኑ ለአገልግሎት ወጥተው ነበር እሳቸው አንድ ነገር ሆኑ ብለን ልባችን ተንጠለጠለ ግን ስለተከሰተው ነገር እንቅጩን የሚነግረን ሰው ጠፋ ወይ ተመተዋል ፣ ወይ አልተመቱም ፣ እዚ ጋር አየናቸው የሚለን ጠፋ ብዙ ከተጨነቅን በሗላ ግን አመሻሽ ላይ የቤቱ በር ተንኳኳ ሶስታችንም ከተቀመጥንበት ተስፈንጥረን ተነሳን ተሽቀዳድመን በሩን ስንከፍተው ጓደኞቻቸው ተሸክመዋቸዋል ፊታቸውን ሳየው በህይወት ያሉ አልመሠለኝም ነበር ክፉኛ ተጎድተዋል በሱፈቃድ ሲመታ ከደነገጥኩት በላይ ድንጋጤ ተሰማኝ ትልቅ ሰው ሲደበደብ ይበልጥ ስለሚያሳዝን ይሆን ባላውቅ ልቤ ተሰበረ አይኖቻቸው አብጠው ፣ ድምፃቸው ስልል ብሎ ሲያቃስቱ ሁኔታቸው አስፈራኝ በወቅቱ በሱፈቃድ እና እናቱ እራሳቸውን መቆጣጠር ተስኗቸው ነበር ከድንጋጤያቸው የተነሳ እንደውም ሳይሞቱ ሊያለቅሱላቸው ቃጥቷቸው ነበር የተሻልኩ ሆኜ የተገኘሁት እኔ ነበርኩ እራሴን አረጋግቼ እነሱን ተረጋጉ ማለት ጀመርኩ ቢረጋጉ ብዬ ፤ ነገር ግን አቶ ታሪኩን ያመጡ ወዳጆቻቸው ተቆጥተው ከስንት ሰአት በሗላ ተረጋጉ የተደበደቡትም ምዕመኑን ሰብስበው ሲያስተምሩ ስለተገኙ መሆኑን ነገሩን ከሌሎቹ በላይ የእድል ነገር ሆኖ እሳቸው ላይ በረቱባቸው እሳቸው ግን ክፉ ነገር አልተናገሩም እንኳን ሊራገሙና ሊሳደቡ ቀርቶ እኛንም ከክፉ ንግግርና ከአስተያየት እንድንቆጠብ ተቆጡን "የሚረግሟችሁን መርቁ ተብሏል ስለዚህ እየረገሙን እንመርቃቸዋለን ፤ እየሰደቡን እንወዳቸዋለን አሳዳጆቻችንን የሚያሳድድ ጌታ ብቻ ነው ስለዚህ በእርሱ ስራ ጣልቃ አትግቡ " አሉን እኛም ውስጣችን ቢከነክነንም ዝም አልን ።


ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur