Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፲፮ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፲፮
@yanetmasra

እመኑኝ አለችን ......
   የዛን ቀን ከዘፍጥረት ጀመርኩላቸው በመጀመሪያ ቃል እንደነበር ሁሉም ነገር የተፈጠረው እግዚአብሔር ይሁን ብሎ እንደሆነ ከሠኞ-እሁደ ከፋፍሎ በምድር ላይ ያለው ነገር እንደተፈጠረ ምድርን ካበጃጀ በሗላ በመጨረሻ ቀን እንደተፈጠርን ስለአዳም እና ስለሄዋን ፣ ሄዋንን ስላሳታት እባብ ፣ ከገነት ስለመባረራቸው ብቻ የዛን ለት ሠፊ ጊዜ ወስጄ አወራሗቸው በማህል ቀና ብዬ ሳያቸው የተመሠጡ ይመስላሉ " እና ወደዳችሁት ወይስ አልወደዳችሁትም ? " አልኳቸው መሠረት ቀጥላ " ይሄ የተፃፈው ነገር እውነት ነው ? ይሄ ምድር የተፈጠረው በ7 ቀን ውስጥ ነው ? እኛም ከአፈር ነው የተፈጠርነው እንዴ ? " አለቺኝ " አዎ ይሄ የእግዚአብሔር ቃል ነው ፤ የእግዚአብሔር ቃል ደሞ እውነት ነው ። እኛ ማድረግ የማንችለውን ማድረግ የሚችል ፍፁም አምላክ ነው በ7 ቀን ውስጥ ይሄን ሁሉ  ማድረግ ችሏል እኛንም በአምሳሉ ከአፈር አበጃጅቶ እስትንፋስን ሰጥቶናል " አልኩና ወደ ፍቅር ዞሬ " አንቺ የምትይኝ ነገር የለም ? " አልኳት " እኔ ስታነብልኝ ከራሴ ጋር እየተሟገትኩ ነበር ምናልባት ሁሉንም ስላላነበብክልን ይሆን እንጃ እንጂ ለምን መፅሀፍ ቅዱስ ማንበብ እንደ መጥፎነት ይታያል ለምንስ ብዙ ሰው አያነብም ብዬ ሳስብ ነበር ምክንያቱም ካነበብክልኝ ውስጥ ሠይጣን የሚያደርግ ወይም እምነት የሚያስቀይር ነገር የለም እንደውም ታሪኩ በጣም ይስባል ፤ ግን ሠው አይወደውም ለምንድነው ? አለቺኝ " ለምን መሠለሽ ፍቅር እውነት ሁል ጊዜ አሸናፊ ስለሆነች ውሸት ሊደብቃት ይሞክራል ሆኖም ግን አንድ ቀን መውጣቷ አይቀርም ሰይጣን ኢየሱስን ሊጋርደው ይሞክራል ብዙ ህዝብ ደሞ በሠይጣን መንግስት ውስጥ ነው ያለው ወደ እግዚአብሔር መንግስት ለመግባት ደሞ ኢየሱስን አምኖ ንስሀ መግባት ያስፈልጋል " አልኳት




ግን ስለቃሉ ብዙ እውቀት ስለሌላቸው ያብራራልኛል ብዬ የምጠቀመው ቃል ጭራሽ ብዥታን እየፈጠረባቸው መሆኑን ተረዳሁ እንዳልኩትም " ኢየሱስና እግዚአብሔር ምንድነው ልዩነታቸው ? " ብለው ጠየቁኝ ስለዚ ከአዲስ ኪዳን መጀመር እንዳለብኝ እና በማውቀው ጥቂት እውቀት ኢየሱስን ላስረዳቸው አሠብኩ ታድያ ከዛን ቀን ጀምሮ እናታችን በማትኖርበት ሰአት እቤት ስኖር ከብሉይ እና ከሀዲስ ኪዳን እያደረግን መፅሀፍ ቅድስን ማጥናት ጀመርን ከቀን ቀን እነሡ ላይ ለውጥ እያየሁ መጣሁ ራሳቸውም መፅሀፍ ቅዱስ ማንበብ እና ቁጥርን ምዕራፍን መለየት እየተለማመዱ ነበር እኔም እንዲያነቡ ካለኝ ፍላጎት የተነሳ እኔ በማልኖርበት ጊዜ ካነበባችሁ የምትፈልጉትን እንድትገዙበት ሳንቲም እሰጣችኋለሁ " ብያቸዋለሁ የማገኘው ጥቂት ቢሆንም ለእናቴና ለእነሱ አብቃቅቼ እሠጣቸዋለሁ እነሱም መጀመሪያ አካባቢ ሳንቲሙን የማግኘት ፍላጎታቸው እየገፋፋቸው ያነቡና ያነበቡትን ክፍል ከተረዱት ጋር ጨምረው ይነግሩኛል ከጊዜ በኀላ ግን እንደ ቋሚ ስራ ወሰዱት ከሳንቲሙ ይልቅ ያልገባቸውን እንዳስረዳቸውና አብርያቸው እንዳጠና ይገፋፉኝ ጀመር እንደውም አንድ ቀን እንደ ልማዴ ሳንቲም ልሰጣቸው ከኪሴ ሳወጣ እንደማይፈልጉና መፅሀፍ ቅዱስ ማንበብ ለራስ እንጂ ጠቀሜታው ለማንም እንዳልሆነና ለራሳቸው ሲሉ ስለሚያነቡ ብር እንደማያስፈልጋቸው ነገሩኝ ፤ ከንግግራቸው ብስለትን አስተዋልኩ አሁን ቢያንስ መስመር ይዘዋል ሌላው በጊዜ ሂደት የሚቀጥል ይሆናል ብዬ ለውስጤ ነገርኩት ነፍሴ ሀሴት ስታደርግ ይሰማኝ ጀመር ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው ሗላ ሲያድግ ከዛ ፈቀቅ አይልም የሚባለው ነገር እውነት ነው ....ይቀጥላል


ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur