Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፲፭ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፲፭
@yanetmasra

በ14 አመቷ ይህን ማሰቧ እንድገረምባት አደረገኝ መለስ ብዬ የኔን እህት ፍቅርተን አሰብኳት እሷ በዚ እድሜዋ ይህን ታስብ ይሆን ብዬ አሰብኩ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ሁለቱንም እህቶቼ ምንም እንደማያውቅ ህፃን ልጅ ነው የማያቸው
   የዛኑለት እቤት ገባሁና ሁለቱንም ጠራሗቸው ትንሽ አጫወትኳቸውና እናቴ ስትወጣ ጠብቄ " መፅሀፍ ቅድስ አብረን ብናነብ ቅር ይላችሗል  " አልኳቸው የሁለቱም ፊት ተለዋወጠ " ምነው ?" አልኳቸው ለመናገርም ላለመናገርም ቃጣቸው ከተናገርን በሗላ ቢቆጣንስ ብለው የፈሩ መሠለኝ " ግድ የለም የመሠላችሁን መናገር ትችላላችሁ  " ብዬ ፈገግ አልኩላቸው ፍቅርተ ደፈር ብላ " እንዳንተ ጴንጤ ልታደርገን ነው መፅሀፍ ቅድስ እናንብብ የምትለን ደሞ እማዬ ብታይ ትገርፈናለች አንፈልግም " አለች  "ቆይ ያለቻችሁ ነገር አለ እንዴ " አልኳት
ፍቅርተ ለመደበቅ ፈልጋ " ኧረ ምንም አላለችም አለች " መሠረት ግን " ከዩሀንስ ጋር መጫወት ቀንሱ የሱን ጴንጤነት ያስተምራችሁ እና የሰይጣን መጫወቻ ትሆናላችሁ እኔም እናታችሁ አልሆንም በሰው ዘንድም የተጠላችሁ እና በፈጣሪም ዘንድ የተረገማችሁ ነው የምትሆኑት " ብላናለች አለች ፍቅርተም በአይኗ ተቆጣቻት ያኔ አትናገሩ ብላ እንደነገረቻቸው ተረዳሁ " እውነት ነው ፍቅርተ ?" አለኳት ፈራ ተባ እያለች " አዎ እማዬ በእምነት ዙሪያ ያለ ወሬ ካንተ ጋር እንዳናወራ እና እንዳንሰማክ አስጠንቅቃናለች " አለች " ቆይ ግን ለምን ? " አልኳት " የሰይጣን እምነት መከተል ስለማንፈልግ ነዋ " አለቺኝ " አሀ ሠይጣን እንዳትሆኑና እንዳትጠሉ ፈርተሽ ነው "አልኳት ጭንቅላቷን እየነቀነቀች የአዎንታ ምላሽ ሰጠቺኝ " ታድያ እንደሱ ከሆነ ለምን ከኔጋር ታወራላችሁ እናንተ እንደምታስቡት ከሆነ እኔም ሰይጣን ነኝ ማለት ነው ስለዚ ከሠይጣን ጋር አታውሩ " ብዬ አልኳቸው " እንዴ አንተማ ወንድማችን ነህ እንዴት አናወራህም እኛ ያልነው እምነቱን ነው " አለቺኝ መልሳ




" እኮ እምነቱ የሰይጣን ነው ካልሽ እኔ የሰይጣን ተከታይ ነኝ ማለት ነው ስለዚ አትቅረቡኝ " ብዬ ከመቀመጫዬ ተነሳሁ " እንዴ እንደሱ እኮ አደለም " ብለው እጄን ያዙኝ " ታድያ እንዴት ነው ? " አልኳቸው የሚሉኝ ጠፍቷቸው አንዴ ሰማይ አንዴ መሬት ያያሉ መልሰው አሳዘኑኝ " እሺ የፈለጋችሁትን ማሰብ ትችላላችሁ ግን ምንም ሳታውቁ በደፈናው አንድ ነገር ላይ አትፍረዱ መጀመሪያ ስለዛ ነገር ለማወቅ ፍላጎት ይኑራችሁ ስታውቁ የፈለጋችሁትን መናገር ትችላላችሁ ስለዚ በስርአት እናውራና ከዛ የፈለጋችሁትን ትላላችሁ እኔ ጴንጤ ሁኑ አላልኳችሁም መፅሀፍ ቅድስ አንብቡ እንጂ ቆይ እኔም እናንተም እግዚአብሔርን እናምን የለ ? አልኳቸው " አዎ " አሉኝ " ስለዚ እኔ የሰይጣን እምነት የምከተል ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔርን አልወደውም አላምነውም ነበር  ደሞ ሰው አንድ ነገር መጥፎ ነው ስላለ ይሀ ነገር መጥፎ ነው ማለት አደለም ጥሩም ነው ስላለ ጥሩ ላይሆን ይችላል ይሀን የምታውቁት በአእምሮአችሁ በማመዛዘን ነው ስለዚ መፅሀፍ ቅድስ ላንብብላችሁና ካልወደዳችሁት እተወዋለሁ ከወደዳችሁት ደሞ ሁሌ እናነባለን " አልኳቸው ሁለቱም ተስማሙ ግን ከፊታለው በድጋሚ ቅሬታ አየሁ "ምነው ? " አልኳቸው ወደ ፍቅር ዞሬ " እማ ብታውቅ ግን ትገለኛለች ባለፈው አንተን በርበሬ እንዳጠነችህ እኛን ብታጥነንስ ወይ ብትደበድበንስ " አለቺኝ እኔም " ስለሱ አታስቡ እማዬ ስትኖር ዝም ብለን እንጫወታለን ስትወጣ ደሞ እናነባለን ታድያ እንዳታውቅ ከፈለጋችሁ እናንተም ፀጥ ማለት ነው ያለባችሁ ለእናታችን ምንም አትነግሯትም ሁላችንም ዝም ካልን አታውቅም በዚ ትስማማላችሁ ? " አልኳቸው አሁንም ፍቅርተ ቀደም ብላ " እኔ እስማማለሁ መሲ ግን ብትናገርስ እሷ አፏ አይቋጥርም " አለቺኝ " ትናገርያለሽ እንዴ አልኳት " አልናገርም " አለቺኝ " ቃል ትገቢያለሽ ለሁለታችንም ? " አልኳት " እግዚአብሔርን ለማንም አልናገርም እመኑኝ " አለችን ....ይቀጥላል


ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur