Get Mystery Box with random crypto!

#የእግዚአብሔር_ስራ_በችግራችን_ይገለጥ (የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 9) 2፤ ደቀ መዛሙርቱም። መም | የክርስቶስ ደቀመዝሙር ✞

#የእግዚአብሔር_ስራ_በችግራችን_ይገለጥ

(የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 9)
2፤ ደቀ መዛሙርቱም። መምህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕውር ሆኖ እንዲወለድ ኃጢአት የሠራ ማን ነው? እርሱ ወይስ ወላጆቹ? ብለው ጠየቁት።
3፤ ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰ። የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው እንጂ እርሱ ወይም ወላጆቹ ኃጢአት አልሠሩም።


(John 9)
2 And his disciples asked him, saying, Master, who did sin, this man, or his parents, that he was born blind?
3 Jesus answered, Neither hath this man sinned, nor his parents: but that the works of God should be made manifest in him.

***
በዮሐንስ ወንጌል ይህን መሰል ሀሳብ በ ምዕራፍ 11 : 4 ላይም እናገኛለን " ኢየሱስም ሰምቶ። ይህ ህመም የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም አለ።"

ኢየሱስ በእነዚህ ኹለት ስፍራዎች እንዴት ለሰዎች ከባድና ችግር የኾነባቸውን ነገር ለእግዚአብሔር ግን ሥራውንና ክብሩን መግለጫው እንደኾነ ሲያሳያቸው እናነባለን፡፡


ዛሬም በሕይወታችን የበዙ የተለያዩ ችግሮች ይኖራሉ፡፡ እነዛም ችግሮች ሰቅዘው አላስኬድ ብለው ይዘውን እንዲሁም ሕይወታችንን ሙሉ አመሰቃቅለው ሊሆን ይችላል፡፡ ደግሞም በሀዘን አቆራምተው ሕይወትን አጨልመው ይኾናል፡፡ ግን ከነ ድካማችን፣ ሀዘናችንና ችግራችን ወደ ክርስቶስ እየተመለከትን "ጌታ ኾይ በችግሬ ላይ አንተ ክበር" እንበለው

ኢየሱስ ወደእኛ ሲቀርብና በአጠገባችን ሲያልፍ የኛ ችግር ለእሱ ክብር መገለጫ ይኾናል፡፡
መልካም ሳምንት!
@christdisciples