Get Mystery Box with random crypto!

#ያለኢየሱስ_ምንም_ነኝ ' እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። #ያለ_እኔ_ምንም_ | የክርስቶስ ደቀመዝሙር ✞

#ያለኢየሱስ_ምንም_ነኝ

" እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። #ያለ_እኔ_ምንም_ልታደርጉ_አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።"
(የዮሐንስ ወንጌል 15:5)

"5 I am the vine, ye [are] the branches: He that abideth in me, and I in him, the same bringeth forth much fruit: #for without_me_ye_can_do_nothing."
(John 15:5)

***
የክርስትና ሕይወት የተመሠረተው በኢየሱስ ላይ ነው፡፡ መሠረታችንም እርሱ ነው፡፡ እኛ የክርስቶስ ደቀመዝሮች የተጣበቅንበት ግንድ ኢየሱስ ይባላል፡፡

አንዳንድ ጊዜ ግን ግንዱን ኢየሱስን ትተን በራሳችን አቅም ፣ ችሎታ፣ መልካምነት ለመፍጨርጨር እንሞክራለን። ይህ ግን ከንቱ ድካም ነው፡፡ ማንኛውም ቁጥር በዜሮ ቢባዛ ዜሮ እንደሆነ የኛም መንፈሳዊ ሕይወት ያለ ኢየሱስ ባዶ ነው፡፡ ለዚህ ነው ኢየሱስ አስቀድሞ ያለ እኔ ምንም ማረግ አትችሉም ያለው፡፡

ስለዚህ ምን እናድርግ?
ሁልጊዜ ለኢየሱስ "ያላንተ ምንም ነኝ" እንበለው ። ከነድካማችንና ከነሀጢያአታችን በፀጋው ፊት ወድቀን "ያላንተ ምንም" ነኝ እንበለው፡፡

@Christdisciples