Get Mystery Box with random crypto!

#ከባርነት_መለቀቅ ' እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው። ወደ ፈርዖን ግባ እንዲህም በለው። እግዚአብ | የክርስቶስ ደቀመዝሙር ✞

#ከባርነት_መለቀቅ

" እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው። ወደ ፈርዖን ግባ እንዲህም በለው። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።"
(ኦሪት ዘጸአት 8:1)

"1 And the LORD spake unto Moses, Go unto Pharaoh, and say unto him, Thus saith the LORD, Let my people go, that they may serve me."
(Exodus 8:1)

**
እግዚአብሔር በባርነት ለያዘን ነገር ሁሉ ዛሬም ልጆቼን ያገለግሉኝ ዘንድ ልቀቅ ይላል። ከሕይወታችን ተጣብቆ የያዘን የኀጢት ስርና የአለም ምኞትን ልቀቅ ይለዋል፡፡

ነገር ግን እኛ ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር ወደሚወስደን የነፃነት ምድር ስንጓዝ የፈርዖን አገዛዝንና የፈርዖን ምድርን እንሻለን፡፡ እግዚአብሔር በበረሀ በተዓምር ከሚመግበን መና ይልቅ የግብፅ ሽንኩርት ይናፍቀናል፡፡ ብዙዎች እስራኤራዊያን በበረሀ የቀሩት በዚህ ሀሳባቸው ነው፡፡

ወደ ነጻነታችን ስንጓዝ እግዚአብሔርን ፈፅመን እንመነው ዛሬም ያዘኝ አጥብቀህ እንበለው


እጄን ያዘኝ ጌታ ፣ እጄን ያዘኝ
እጄን ያዘኝ ኢየሱስ ፣ እጄን ያዘኝ

ያለማመኔን ደካማነቴን አግዘህ በፍቅርህ
እድፍ ቁሸቴን አጥርተህ
ባንተ ነው ከረግረግ ውስጥ መውጣቴ
በመቆም የተቀየረው ሕይወቴ

------

የቆምኩ ሲመስለኝ መውደቅ አለና
ሁሉን አሻግረኝ በእጅህ ያዝና ...

@Christdisciples