Get Mystery Box with random crypto!

ጽናትና ውሳኔ (መጽሐፈ ሩት ምዕራፍ 1) ---------- 12፤ ልጆቼ ሆይ፥ ተመለሱ፤ ባል ለማግ | የክርስቶስ ደቀመዝሙር ✞

ጽናትና ውሳኔ

(መጽሐፈ ሩት ምዕራፍ 1)
----------
12፤ ልጆቼ ሆይ፥ ተመለሱ፤ ባል ለማግባት አርጅቻለሁና ሂዱ፤ ተስፋ አለኝ ብል፥ ዛሬ ሌሊትስ እንኳ ባል ባገባ፥ ወንዶች ልጆችም ብወልድ፥

13፤ እነርሱ እስኪያድጉ ድረስ ትቆያላችሁን? ስለ እነርሱስ ባል ማግባት ትተዋላችሁን? ልጆቼ ሆይ፥ እንዲህ አይደለም፤ የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ወጥቶአልና ከእናንተ የተነሣ እጅግ ተመርሬአለሁ።

14፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው እንደ ገና አለቀሱ፤ ዖርፋም አማትዋን ሳመች፤ ሩት ግን ተጠጋቻት።

15፤ ኑኃሚንም። እነሆ፥ ባልንጀራሽ ወደ ሕዝብዋና ወደ አማልክትዋ ተመልሳለች፤ አንቺም ደግሞ ከባልንጀራሽ ጋር ተመለሽ አለቻት።

16፤ ሩትም። ወደምትሄጅበት እሄዳለሁና፥ በምታድሪበትም አድራለሁና እንድተውሽ ከአንቺም ዘንድ እንድመለስ አታስቸግሪኝ፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ፥ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፤

17፤ በምትሞችበትም ስፍራ እሞታለሁ፥ በዚያም እቀበራለሁ፤ ከሞት በቀር አንቺንና እኔን አንዳች ቢለየን እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ እንዲሁም ይጨምርብኝ አለች።

18፤ ኑኃሚንም ከእርስዋ ጋር ለመሄድ እንደ ቈረጠች ባየች ጊዜ እርስዋን ከመናገር ዝም አለች።

"14 And they lifted up their voice, and wept again: and Orpah kissed her mother in law; but Ruth clave unto her."
(Ruth 1:14)

**

በዚህ የሩት መጽሐፍ ውስጥ ድንቅ ታሪክ እናነባለን፡፡ እሱም እንዴት አንዲት ሴት የወሰነችው ቁርጥ ውሳኔ ሕይወቷን ለዘላለም እንደቀየረው ነው፡፡

በዚህ ምድር ኹላችንም የምንኖረው የውሳኔዎቻችንን ፍሬ ነው፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ነገሮችን በጽናት ሳይኾን በስሜት ስንወስን ብዙ ዎጋ እንከፍልባቸዋለን፡፡

ከሩት የጸና የአልመለስም ውሳኔ ምን እንማለን
****
ሩት በውሳኔዋ በመጽናቷ ከአህዛብ ወገን ኹና ሳለ - የኢየሱስን ዘር ትውልድ ተቀላቀለች

ሩት የኑሀሚንን ችግር ሳታይ በእምነት ስለተከተለቻት የእስራኤል አምላክ ህይወቷን በበረከት አትረፈረፈው

ሩት ጸንታ ኑሀሚንን በመከተሏ ታሪኳ ዘላለማዊ ኾነ ዖርፋ ግን ከዛ በኀላ ምን እንደደረሰባት ራሱ አይታወቅም

ሩት ያመነችው ኑሀሚንን ሳይኾን የሳን አምላክ ነበር እና በውሳኔዋ እምነቷን ገለጠች አምላክም መልሶ ታመነላት

ዛሬስ እኛ በሕይወታችን የጸናንባቸው ውሳኔዎች ምንድን ናቸው?
ምን ያህል ነገሮችን ሁሉ አልፈን ሳንመለስ በጽናት ጌታን እየተከተልነው ነው?
***
ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት በመጽናት ወደኀላ ላንመለስ ጌታን ይዘን መከተል ይኹንልን፡፡ ሩት ወደ ኑሀሚን በእምነት እንደተጠጋች እኛም ዘወትር ወደ ጌታ መጠጋት ፣ ወደሱ መቅረብ ይኹንልን