Get Mystery Box with random crypto!

ነገ አሉት ሳይመጣ ያላዩት ከዛሬ 'ሚሻል ፈክቶ ያበበ ሳቅ የሞላበት በደስታ ሀሴት የተከበበ የምና | ጨረቅረቃ

ነገ አሉት
ሳይመጣ ያላዩት
ከዛሬ 'ሚሻል ፈክቶ ያበበ
ሳቅ የሞላበት በደስታ ሀሴት የተከበበ
የምናብ ዓለም ውል አልባ ምኞት
ባላዩት ነገ ዛሬን ማሞኘት
ሕልም አሉት ፍቺ የሌለው
በጄ ያ'ዝኩትን አሁኔን ገለው
ያ ሞኙ ልቤ ተስፋን መርኩዞ ሳቁን የገታ
ዛሬን አምኜ ካፍህ የነጠኩህ የራስህ ፋንታ
የማልመልስህ ትላንቴ ይቅርታ
#እሙ_ሠላም