Get Mystery Box with random crypto!

ደስ አይልም! አበባ ተሰጠኝ ያውም በጣም ብዙ መያዝ አስኪከብደኝ እጅግ የሚያምሩ በሚገርም ሸምቀቆ | ጨረቅረቃ

ደስ አይልም! አበባ ተሰጠኝ
ያውም በጣም ብዙ መያዝ አስኪከብደኝ
እጅግ የሚያምሩ
በሚገርም ሸምቀቆ ሰርክ የተቋጠሩ
አመስጋኜ ለጉድ አድናቂዬ በዝቷል
ዘመን የናፈኩት እልፍኜ ሰው ሞልቷል
ቆጫት መሰል እሷም አለች
እንቡጥ ይዛ ፊት ቆማለች
ብዙ ክምር
የሚያምር
በነጭ በቢጫ በቀይ ባ'ረንጓዴ
ለካ ሚስኪን ልቧ ይወደኛልዴ
ብዬ እስክገረም
እስክናፍቅ ዓለም
ጠልቼ ያለፍኳት ያቺን ክፉ ምድር
ያስናፍቀኝ ጀመር
ምኞት ከረፈደ
ዕድል ባለቀበት ጊዜ ከነጎደ
አንባሽ ላይፈይደኝ እንቡጥ ላይሆን ፍራሽ
ይቅር በለኝ ብትይ ምን ዋጋ'ለው ብለሽ
ነይ ስልሽ ብትመጪ እኔም ባልሞትብሽ
#እሙ_ሠላም