Get Mystery Box with random crypto!

ብቸኝነት ሲያክም የስነ አዕምሮ ሊቅ ይነግረን ይሆናል ሰው ከሰው እንዳይርቅ ለኔ ግን አይደለም ከግ | ጨረቅረቃ

ብቸኝነት ሲያክም የስነ አዕምሮ ሊቅ
ይነግረን ይሆናል ሰው ከሰው እንዳይርቅ
ለኔ ግን አይደለም
ከግል ስብዕናው ከሌለው ተቃርኖ
ብቸኛ አይሆንም ሰው ከራሱ ሆኖ
የስነ ፍጥረት ሊቀ በበኩሉ ደግሞ
ብቸኝነት ሲገልጽ በቃላት አስታሞ
ከሌሎች ተዋዶ ከራስ መለያየት
ይነግረን ይሆናል ብሎ ብቸኝነት
ለኔ ግን አይደለም
ከራሱ ቢጣላ ሆኖ ሞገደኛ
ሰው ከሰው ጋር ሆኖ አይሆንም ብቸኛ
ለኔ ብቸኝነት
ከዓለም ሕዝብ መሃል ቅሩብ የሚቀርቡት
አንድ ሰው ይኖራል እጅግ የሚወዱትን
ከራስ ሳይጣሉ በሰውም ተከበው
ከዓለም ሕዝብ መሃል ያ'የሚወዱትን ሰው
ያጡት እንደሆነ ፈልገው ፈልገው
ብቸኝነት ይህ ነው