Get Mystery Box with random crypto!

የክርስትና እውነቶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ cchristiantruth — የክርስትና እውነቶች
የቴሌግራም ቻናል አርማ cchristiantruth — የክርስትና እውነቶች
የሰርጥ አድራሻ: @cchristiantruth
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K
የሰርጥ መግለጫ

📖መጽሐፍ ቅዱሳዊ📖 የሆኑ መንፈሳዊ ጽሑፎችን የሚያገኙበት ቻናል ነው❗
📲Join/Subscribe📲 ብለው ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑ!👥
↪Share↩ በማድረግም "የክርስትና እውነቶችን" ለወዳጅዎ ያጋሩ!👇
https://t.me/Cchristiantruth

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-10-01 21:30:38 የፍጥረቱ ደጋፊ ይደግፋቹሃል!!

አንዳንዴ ነገሮች ምስቅልቅል ይላሉ ነገር አለሙ ግራ ይሆንብናል ።ለፍተን አይሳካልንም አጭበርባሪዎች ግን ይከብራሉ ። ሰርተን አመድ አፋሽ እንሆናለን ልንከበርበት ልሞገስበት የሚገባ ተግባራችን የመዋረጃችን መሳሪያ ይሆናል ።በችግራቸው የደረስንላቸው በችግራችን አናገኛቸውም ።ሳናወራ የሚስቁልን ወዳጆቻችን ግንባራቸው ከአሳ ቅሪፊት ይሻክራል ።ቆዳቸው ከአዞ ቆዳ ይጠነክራል ።

አንዳንዴ ግራ የሚጋቡ ነገሮች ተከታትለው ነው የሚመጡት ይህ ችግር ለምን በዚህ ሰአት ስንል አንደበታችን ሳንዘጋ ትናጋ የሚዘጋ ነገር ይከተላል።የግል ጉዳይ ሲያሳስበን ማህበራዊው ነገር ደግሞ ይለጥቃል (ይከተላል) የቤተሰብ ጉዳይ ደግሞ ሊበላሽ ይንደረደራል ።

እንዲህ አይነት ሰው በእውነት ማፅናናት ከባድ ነው ግን አንድ ተስፋ አለ ።

ምንድነው ይህ ተስፋ ? ደጋፊ ቃል ነዋ!!

የዕብራውያን መፅሃፍ የኢየሱስን ታላቅነት ትልቅነትና ከማስረዳት የሚጀምር መፅሃፍ ነው። እንዲህ በማለት ይጀምራል ። ኢየሱስ እርሱ በስጋ የተገለጠው ክርስቶስ አማኑኤል የሆነው እርሱ አለማትን ሁሉ የፈጠረ ነው ይለናል።ዕብ 1:1-3 ምድርን ብቻ አይደለም አለሙን ሁሉ የፈጠረ ነው!! ዕብ 2:10

ይቀጥልና ፈጣሪ ብቻ ሳይሆን የፈጠረውን ፍጥረት በስልጣኑ ቃል የሚደግፍ ነው ይለናል ።

“እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ #ሁሉን_በስልጣኑ_ቃል_እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤”
— ዕብራውያን 1፥3

ማንን ይደግፋል? ሁሉን!!

እሰይ የምስራች ከሁሉም ውስጥ የሆንን እኛንም የሚደግፍ ደጋፊ አለ እርሱም ኢየሱስ ሰው የሆነው ክርስቶስ ነው።

ወገኖቼ በኢየሱስ ስር ተጠለሉ !! ብትወድቁ ያነሳቹሃል
በኢየሱስ ስር ተቀመጡ ብታለቅሱ ያፅናናቹሃል።
በኢየሱስ ስር ተሰወሩ በሚያስፈልጋቹ ጊዜ የሚረዳ ፀጋ ይለቅላቹሃል ።

“እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።”
— ዕብራውያን 4፥16

የሚረዳ የእግዚአብሔር ፀጋ የሚደግፍ የስልጣን ቃል ያግኛችሁ አሜን!!


በግሩም ድፈቅ
መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆኑ መንፈሳዊ ጽሑፎችን የሚያገኙበት ቻናል ነው

Join/Subscribe ብለው ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑ!
Share በማድረግም "የክርስትና እውነቶችን" ለወዳጅዎ ያጋሩ!

https://t.me/Cchristiantruth
https://t.me/Cchristiantruth
299 viewsGirum Difek, edited  18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 06:11:28 ፍቅሩ ባህሪው ይህ ነው ያፋቅራል!!

መፅሃፍ ቅዱስ የፍቅርን ትርጉም ይነግረናል ።ብዙ የፍቅር ትርጉሞች ቢኖሩም የፍቅር ባለቤት ራሱ እግዚአብሔር ሲነግረን ግን በመልክተኞቹ በኩል በመፅሃፉ በኩል ሲያስተዋውቀን ግን ከፍቅር እውነተኛ ትርጉም ጋር እንገናኛለን ።

ታዲያ እግዚአብሔር በመፅሃፉ በሐዋሪያው ዮሃንስ በኩል ስለ ፍቅር ምን ይላል ?

“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።”
— 1ኛ ዮሐንስ 4፥10
ዮሃንስ የእውነተኛውን ፍቅር ትርጉም ሊነግረን ፈልጎ ፍቅር እንደዚህ ነው ይለናል !!

ቀጥለን እንዴት ነው? ፍቅር ብለን ብንጠይቀው እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደወደደ ይለናል ።የፍቅር መነሻ እኛ አይደለም የፍቅር መነሻ ራሱ እግዚአብሔር ነው ።ካለንበት መጥቶ ፍቅሩን ያካፈለን እርሱ ነው ።ከሰማያት በልጁ በኩል የፍቅር እጁን ዘርግቶ ያደነን ወደ ልጁ መንግስት ያፈለሰን እርሱ ነው።ወደ ሞትንበት ስፍራ (ወደ ሞትነው) የመጣው እርሱ ነው ።ሰው ፍቅሩን በሞት ሲጨርስ እርሱ ፍቅሩን ከሞትንበት ቦታ ጀምሮ አሳየን። እውነትም ፍቅር እንደዚህ ነው ።

እግዚአብሔር ይህንን ፍቅሩን ለመግለፅ እና ተፈቃሪ የሰው ልጅን ለማዳን ስለ ሃጢያታችን ልጁን በስጦታ መልክ ሰጥቷል።ለጥሩ ነገራችን አይደለም ስጦታ የተሰጠን ለሃጢያታችን ነው ።ዘመናችን እንደዚህ አይነት ፍቅር አያውቅም የዘመናችን ፍቅር በደላችንን የመታገስ እንኳ አቅም ያጥረዋል።እግዚአብሔር ውድ ልጁን ለመሰቀል ሞት አሳልፎ ሰጠ።

“ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?”
— ሮሜ 8፥32

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
— ዮሐንስ 3፥16

ታዲያ እግዚአብሔር ፍቅሩን ሲገልጥልን ከእኛ የሚጠብቀው ነገር አለ !! ፍቅሩ እንዲባክንበት አይፈልግም ፍቅሩ ሳይገባን እንድንመላለስ አይፈልግም ።ፍቅሩ የህይወት ትርፍ ያመጣል የኑሮ አቅጣጫ ያስቀይራል ።ሁል ጊዜ የእግዚአብሔር ፍቅር ከተወራ በኋላ ቀጣይ ማሳሰቢያ አለ ምን!?

“ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል።”
— 1ኛ ዮሐንስ 4፥11

የእግዚአብሔር ፍቅር ከላይ ፈሶ ወደ ህብረት ይዛመታል ።ፍቅሩ ባህሪው ይህ ነው ያፋቅራል በህብረት ውስጥ መዋደድን እንዲበዛ ያደርጋል ።ሰውን ጠልተን የእግዚአብሔር ፍቅር አውቃለሁ ማለት ተላላነት ነው።ፍቅሩ አፍቃሪነትን ካላመጣ በትክክል ፍቅሩ ያለመረዳት ችግር አለ ማለት ነው ።ፍቅሩ ለሰዎች መኖርን ለወንድሞች ነፍስን አሳልፎ እስከመስጠት ሊያደርስ የሚገባ መሆኑን ነው መፅሃፉ የሚነግረን ።

“እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል።”
— 1ኛ ዮሐንስ 3፥16

ስለዚህ የፍቅር ህይወት የመተሳሰብ ህይወት የመረዳዳት አንዱ ለአንዱ የመኖር ህይወት እግዚአብሔር በልጁ ሞት ያስገኘልን በፍቅሩ የመጣልን የክርስቲያኖች የህይወት መርህ ነው።

የተፈቀረ ሰው በፍቅር ይኖራል!!

ጌታ መፋቀርን መዋደድን ያብዛልን አሜን!!!!

ግሩም ድፈቅ

https://t.me/Cchristiantruth
339 viewsGirum Difek, edited  03:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 23:31:19 በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ አስተሳሰብ !!

ጳውሎስ በክርስቶስ ስለነበረው አስተሳሰብ(ሃሳብ) ሲናገር እንዲህ ይላል።

“በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው ያ አስተሳሰብ፣ በእናንተም ዘንድ ይሁን፤”
— ፊልጵስዩስ 2፥5 (አዲሱ መ.ት)

በእርግጥ ይህ የክርስቶስ ሃሳብ ምንድነው ? ብለን መጠየቅ አለብን ለምን ቢባል ሁኑ እየተባልን ያለው ነገር ስለሆነ ወይም በእናንተ ዘንድ ይኑር እየተባልን ያለው አስተሳሰብ ስለሆነ !!

ምንድነው ይህ ሃሳብ ካልን የትህትና ሃሳብ ነው ።ራስን ዝቅ የማድረግ ሃሳብ ነው። የክርስቶስ ሃሳብ ወይም አስተሳሰብ የሚለው ይህንኑ ራስን ዝቅ ማድረግን ነው።በዚህ ዘመን ይህንን መመከር እንዴት ከባድ መሰላቹህ ሰዎች ራሳቸው ከፍ ማድረግ በሚፈልጉበት በዚህ ዘመን ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ በትህትና ተመላለሱ ማለት ከባድ ነው።

ትህትና ማለት የሌለንን ነገር እንዳለን በመቁጠር ዝቅ ማለት ሳይሆን እንዳለን እያወቅን ዝቅ ማለትን የሚያመለክት ቃል ነው።ኢየሱስ የሆነው ይህንኑ ነው። እርሱ መለኮት ሆኖ ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር በእኩልነት በእኩልነት የሚኖር የእግዚአብሔር አብ አቻ መለኮት በባህሪው ፍፁም ከእርሱ የሚስተካከል ሆኖ ሳለ ለሰው ልጆች ሲል በስጋ የውርደትን ህይወትና ሞት ለመኖርና ለመሞት በማሪያም ማህፀን ተፀነሰ!!

ትሁታን ምንሆነው ከእውቀት ነፃ ስለሆንን አይደለም !ትሁታን የምንሆነው ገንዘብ ስለሌለን ዲግሪ ስለሌለን ማስተርስ ፒኤችዲ ስለሌለን በስጋ የሚያስመኩ ነገሮች ስለ ሌሉን አይደለም ። ኢየሱስ እግር ያጠበው ሁሉ እንደተሰጠው አውቆ ከሚል ቃል በኋላ እንደሆነ አስተውላቹሃል።

ዮሐንስ 13

³ ኢየሱስ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲሄድ አውቆ፥
⁴ ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤
⁵ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ።

ጳውሎስ ይህንን ነው ሚለን ይህ በክርስቶስ ውስጥ ያለው አስተሳሰብ በእናንተ ሊኖር ይገባል ።ኢየሱስ ትሁት እንደሆነ ትሁታን ሁኑ አንዳቹ አንዳችሁን አክብሩ በመከባበር እንጂ በመወቃቀር ህብረት አይፀናም ነው እያለ ያለው ለትህትና የመረጠው ምሳሌ የኢየሱስን ሰው መሆን ነው ።

በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ( in the form of God) በባሪያ (በሰው)መልክ ተገኘ ነው የሚለን

ፊልጵስዩስ 2 (አዲሱ መ.ት)
⁶ እርሱ በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን ሊለቀው እንደማይገባ አድርጎ አልቈጠረውም፤
⁷ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ፣ በሰውም አምሳል ተገኝቶ፣ ራሱን ባዶ አደረገ፤

Philippians 2 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ Who, being in the form of God, thought it not robbery to be #equal_with_God:
⁷ But made himself of no reputation, and took upon him the form of a servant, and was made
in the likeness of men:

ትሁት መሆን ሞኝነት አይደለም ።ትሁት መሆንን ልንፈፅመው የሚገባ ኢየሱስን በመምሰል የምንመላለሰው ህይወት ነው ።

ጌታ እግዚአብሔር ይህንን እንድንሆን ፀጋ ያብዛልን አሜን!!


ግሩም ድፈቅ
239 viewsGirum Difek, 20:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 15:25:45

220 viewsGirum Difek, 12:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 13:19:34 ስለ ኃጢአት ምንነት መጽሐፍ የሚናገረውን ለማድመጥ ከታች ያለውን መስፈንጠሪያ ይጫኑ። ትምህርቱ ከጠቀመዎት ወደ ፊት የሚለቀቁ ሌሎች ክፍሎችን ለመከታተል Subscribe በማድረግ ቤተ ሰብ ይሁኑ



233 viewsGirum Difek, 10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 13:16:54 አምላካችን እና መድሃኒታችን
ተፃፈ በ Girum Difek

በብሉይ ኪዳን መፅሃፍት ውስጥ እግዚአብሔርን አምላካችን እና መድሃኒታች ብሎ መጥራት የተለመደ ነው። እንዲያድናቸው ሲፈልጉ መድሃኒት እንዲሆናቸው ሲሹ እግዚአብሔርን አምላካችን መድሃኒታችን እያሉ ይጠሩታል።ለምን ካልን እውነትም እርሱ አምላክና መድሃኒት ስለሆነ ነው።

“ቤተ መቅደስህ ቅዱስ ነው በጽድቅም ድንቅ ነው። በምድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስፋቸው የሆንህ፥ #አምላካችንና_መድኃኒታችን ሆይ፥ ስማን።”
— መዝሙር 65፥5
“#አምላካችንና_መድኃኒታችን ሆይ፥ እርዳን፤ ስለ ስምህ ክብር፥ አቤቱ፥ ታደገን፥ ስለ ስምህም ኃጢአታችንን አስተሰርይልን።”
— መዝሙር 79፥9

እስራኤላውያን ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ማንም አምላካችን እና መድሃኒታችን ብለው አይጠሩም ።ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ አምላክ የለምና። ይህንን በገማሊያል እግር ስር ቁጭ ብሎ የተማረው ጳውሎስም ወንጌላትን የፃፉልንም ጠንቅቀው ያውቁታል።

ስለዚህ የወንጌላት ፀሃፊዎች እና ብዙ መልዕክታትን የፃፈልን ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ እና ሌሎቹም ሐዋሪያት ኢየሱስን አምላክና መድሃኒት ብለው ሲጠሩት እርሱ እግዚአብሔር ነው ከማለት ወጪ ሌላ ምን አስበው ሊሆን ይችላል?

“ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም #የታላቁን_የአምላካችንንና #የመድኃኒታችንን_የኢየሱስ_ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤”
— ቲቶ 2፥12-13

ጴጥሮስ የሁለተኛ ጴጥሮስ መልዕክቱን በሰላምታ ሲጀምር እንዲህ ይላል።

“የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ የሆነ ስምዖን ጴጥሮስ፥ #በአምላካችንና_በመድኃኒታችን_በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ፤”
— 2ኛ ጴጥሮስ 1፥1

ይሁዳም በመልዕክቱ እንዲህ ይለናል።

“ብቻውን ለሆነ #አምላክ_መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።”
— ይሁዳ 1፥25

ኢየሱስ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ህይወት መድሃኒትም ነው።

ክብር ምስጋና ለእርሱ ይሁን አሜን!!
383 viewsGirum Difek, 10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 10:19:31 የተባለለት ይህ ነውና

ነብዬ ኢሳያስ ስለ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል

“የአዋጅ ነጋሪ ቃል፦ የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካከሉ።”
— ኢሳይያስ 40፥3
የአዋጅ ነጋሪው ቃል ምን ይላል ?

1ኛ የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ !

የሚጠረገው መንገድ የእግዚአብሔር መንገድ ነው ።የሰው የፍጡር ወይም ደሞ የአንድ የተለየ አካል መንገድ አይደለም!

2ኛ የአምላካችን ጎዳና በበረሃ አስተካክሉ !

ስለዚህ የሚስተካከለው ጎዳና የአምላክ ጎዳና ነው !!

ታዲያ ይህ እግዚአብሔር ተብሎ በትንቢት የተነገረት አምላክ ተብሎ ጎዳና እንዲስተካከል የተተነበየለት እርሱ ማን ነው?

ያህዌ (ጌታ) ኢየሱስ ነው።

“በነቢዩ በኢሳይያስ፦ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ የተባለለት ይህ ነውና።”
— ማቴዎስ 3፥3

ቃሉ በሚገርም ሁኔታ እንዲህ ተቀምጧል

"የተባለለት ይህ ነውና"

ሉቃስም በወንጌሉ የትንቢቱ ፍፃሜ ኢየሱስ እንደሆነ ተናግሯል። ይህ ማለት መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሃንስ አምላክ እና እግዚአብሔር ተብሎ በትንቢት ለተጠቀሰው ለጌታ ለኢየሱስ መንገድ ተራጊ ሆኖ መምጣቱን ይገልፅልናል !!

“በነቢዩ በኢሳይያስ ቃል መጽሐፍ፦ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፤ ዐዘቅቱ ሁሉ ይሙላ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፥ ጠማማውም የቀና መንገድ ይሁን፥ ሸካራውም መንገድ ትክክል ይሁን፤ ሥጋም የለበሰ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ ተብሎ እንደ ተጻፈ ለኃጢአት ስርየት የንስሐን ጥምቀት እየሰበከ በዮርዳኖስ ዙሪያ ወዳለችው አገር ሁሉ መጣ።”
— ሉቃስ 3፥3-6

#ኢየሱስ_እርሱ #እግዚአብሔር ነው!
346 viewsGirum Difek, 07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 16:29:09

386 viewsGirum Difek, 13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 15:45:46
483 viewsGirum Difek, 12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 15:45:30 ሁለቱ ሶስት አስራ ስድስቶች

ፒተር ለፕሮፌሰሩ ጌታ ያገኘበትን መንገድ እያብራራ ነው።

ኢየሱስን ያገኘበትን የመጀመሪያ ቀን በማሰታወስ ለፕሮፌሰር ማስረዳት ጀመረ ።እግዚአብሔር እኮ አስገራሚ አምላክ ነው እኔ የሱ ሰለማድረጉ ሳስብ እና ለኔ ያሳየው ፍቅር ስረዳ ሌሎች ይህንን ፍቅር እንዲረዱ እና በፍቅሩ እንዲረኩ እመኛለሁ ።ለዛ ነው በዚች ትንሽ መንደር ውስጥ የተገኘውት ሰዎች ወደ ጌታ እንዲመጡ ማድረግ የዘወትር ስራዬ ነው ብዬ እንዳምን ያደረገኝ ፍቅሩ ነው ። ሌሎችም ፍቅሩ እንዲህ ሲያደርጋቸው ማየት ረፍት ይሰጠኛል።

ከእለታት አንድ ቀን በትምህርት ገበታዬ ላይ ሆኜ እየተማርኩ አስተማሪው ፊዝዮሎጂ( physiology )የሚባል የህክምና አንደኛውን ኮርስ ያስተምራል። የሰው ልጅ አጥንት የሰው ልጅ ደም የሰው ልብ ስራዎችንን እየተነተነ የሰውን የነርቭ ስርአት ( nerve system )ን እያብራራ እኔ ሌላ ሃሳብ ውስጥ ገብቻለሁ ።

ይህንን የሰራ ውስብስብ የሆነ የሰው ልጅን ተፈጥሮ ያስተካከለ የሆነማ አካል አለ? እንዴት በድንገት ይህ ውስብስብ ተፈጥሮ በትክክል ሊሰራና ሊቀናጅ ይችላል።ሳምባችንና ልባችን እንዴት ተጣጥመው ኦስጂን እና ካርቦንዳይ ኦክሳይድ እየተለዋወጡ የሰውን ህይወት ሊያቆዩት ይችላሉ ። አጥንት እና አጥንት እንዳጎዳዱ በመገጣጠሚያ ላይ ዘይት መሳይ ፈሳሽ በማድረግ ፍሪክሽንን እንዳይኖር ያደረገ የሆነማ አካል አለ ።የሚል ሃሳብ አእምሮዬን ወጥሮ ያዘኝ ሃይማኖት የሌለኝ ሰው ብሆንም የሆነ ጥናት ማድረግ እንዳለብኝ ወሰንኩ ከክላስ ወጥቼ በጎዳና ላይ እያዘገምኩ እያለ ገጥሞኝ የማያውቅ አንድ ክስተት ገጠመኝ!!

አንድ በእድሜ ሸምገል ያሉ ሰውዬ ሰላም ካሉኝ በኋላ አንድ ነገር ባወራህ ፍቃደኛ ነህ ሲሉ ደስ ከሚል ፈገግታቸው ጋር ጋበዙኝ

እሺ ብዬ ተስማማው

ኢየሱስ ስለሚባል ጌታ ላወራህ እፈልጋለሁ ።እርሱ የሰው ልጆችን ሁሉ ከሞት ሊያድን ወደ ምድር የመጣ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። እርሱ የዘላለም ህይወት ያስገኛል እርሰ ሰላምና ረፍት ይሰጣል እሱ ብቸኛ መዳኛ ነው።አለና ሁለት ሶስት አስራ ስድስቶችን አነበብልኝ

“እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል።”
— 1ኛ ዮሐንስ 3፥16

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
— ዮሐንስ 3፥16

ውስጤ መናወጥ ጀመረ ልቤ መምታት አበዛ ውስጤ ሲቃጠል ይሰማኛል ።እጅ ሰጠው አይኔን እንባ ሞላው ተንበረከኩ ።የሚመሰክርልኝ ሰው ለሰላሳ ደቂቃ ያህል መንገድ ላይ ሲፀልይልኝ ነበር እኔ ስለዚህ ነገር አላውቅም ነበር ።ፀሎቱን እንደደጨረሰ ወዳጄ ተነሳ ብሎ መፅሃፍ አንብብ ብሎ ሰጠኝ ።ማታ መፅሃፍ ቅዱስን ከዮሐንስ ወንጌል አንስቶ ማንበብ ጀመርኩ ማንበብ ሱስ እስኪሆንብኝ ድረስ ይሄው መፅሃፍ ቅዱስን በቀን የወሰነ ምዕራፍ ሳላነብ አላድርም ። ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ሳስብ ፍቅሩ ድቅን ይልብኛል ።በእውነት እኔ ምኔ ይወዳል እላልሁ ግን እንደ ሰው አይደለም ጌታ ያለ ምክንያት ወዶኛል

አንድ ቀን ይህ እኔን ያገኘኝ የፍቅር ወላፈን ሌሎችን እንዲያገኝ ኢየሱስ የሌሎችም የዘላለም ህይወት መፍትሔ መሆኑን መመስከር እንዳለብኝ ተሰማኝ ትምህርቴን እስክጨርስ ለንደን ነበርኩ ።

ልክ ትምህርት እንዳለቀ ሻጣዬን ይዤ በኢትዮጵያ ከተሞች ላይ ወኔጌልን መስራት ጀመርኩ እስካሁን በእኔ የስብከት አገልግሎት እስከ ሁለት ሺ ሰዎች ጌታን ተቀብለዋል ።ለዚህም ደግሞ በኔ አልፎ የሰራውን መንፈስ ቅዱስን አመሰግናለሁ ።ጌታ ጤና ከሰጠኝ ከዚህ በላይ ለመሆን ለማገልገል እቅድ አለኝ!!

ፕሮፌሰር በእንባ ሆነው የሚያወራውን እየሰሙት ነው ።

ዶር ፒተር ፕሮፌሰር ይህንን ፋይል ያዙት ብሎ ዳጎስ ያለ የጥናት ስራዎች የሚመስሉ በጥራዝ ያሉ ፅሁፎችን አቀበላቸው ።

ፕሮፌሰር የሚያዩት ማመን አልቻሉም የጥራዞቹን ርዕስ እያዩ እንባ በአይናቸው ግጥም አለ።

ይቀጥላል.....
561 viewsGirum Difek, 12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ