Get Mystery Box with random crypto!

Bunna Bank

የቴሌግራም ቻናል አርማ bunnabanksc — Bunna Bank B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bunnabanksc — Bunna Bank
የሰርጥ አድራሻ: @bunnabanksc
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.11K
የሰርጥ መግለጫ

Welcome to Bunna Bank s.c. The best multinational financial service provider based in Ethiopia.

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-14 09:51:29
ባንካችን ሁሌም ከባለራዕዮች ጎን ነው!
ለቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት ፍላጎትዎ በቅርብዎ ነን!

ቡና ባንክ
የባለራዕዮች ባንክ!
1.2K views06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 10:09:27
1.6K views07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 15:16:05 ቡና ባንክ እና የአማራ ቤቶች ልማት ድርጅት የአጋርነት ውል ተፈራረሙ !

ቡና ባንክ እና የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ቤቶች ልማት ድርጅት (አቤልድ) ደንበኞች ወርሃዊ የኪራይ ገቢያቸውን ከሃምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በባንክ እንዲከፍሉ የሚያስችላቸውን ሲስተም ስራ ላይ ለማዋል ተፈራርመዋል፡፡

የሁለትዮሽ ስምምነቱ ከዚህ በፊት የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት የኪራይ ገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ በደንበኞች በኩል የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ነው፡፡

የኪራይ ገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ በደንበኞች በኩል የሚፈጠሩ ችግሮችን ሊፈታ እንዲችል ተደርጎ የሲስተም መተግበሪያ እንዲዘጋጅ በባንኩ እና አቤልድ ተደጋጋሚ ውይይትና ምክክር በማድረግ ትግበራውን ከሃምሌ 1 ቀን2014 ዓ.ም ጀምሮ በባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት በሙከራ ደረጃ የጀመሩ ሲሆን በቀጣይ በሁሉም የድርጅቱ ቤቶች ባሉበት ከተሞች ሲስተሙ እንዲጀምር ይደረጋል፡፡

ቡና ባንክ ከላይ የተገለጹትን ችግሮች የሚፈታ ሲስተም ከመዘርጋት ባለፈ ወደባንኩ መሄድ ሳያስፈልግ በየዕለቱ ማን እንደከፈለ እና ከየት እንደተከፈለ እንዲሁም የመኖሪያና የንግድ ቤት ኪራይ ገቢ መሆኑን ለመለየት የሚያስችለውን መተግበሪያ በተመረጠ ኮምፒዩተር በመጫን መከታተል እንዲቻል እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ከዚህ በፊት የባንክ ስቴትመንት ለማምጣት በየሳምንቱ ወደባንኮች በመሄድ የሚባክነውን ጊዜ በማስቀረት የባንክ ስቴትመንቱን ድርጅቱ ራሱ በፈለገበት ሰዓት ፕሪንት አድርጎ መጠቀም እንዲችልም ተደርጓል፡፡

ውሉን የተፈራረሙት የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አበረ ሙጬ እና የቡና ባንክ ግሽ አባይ ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ ተፈራ ናቸው፡፡

በቀጣይ ድርጅቱና ቡና ባንክ ከኪራይ ገቢ ባለፈ በኮንስትራክሽን ፋይናንሲንግ ዘርፍ አጋር ሆነው ለመቀጠልም ተስማምተዋል፡፡
1.9K views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 15:16:00
1.7K views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 16:05:23
2.0K views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 14:05:18
ባንካችን የተለያዩ የስራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ከዌብሳይታችን ላይ ይህን ሊንክ ተጭነው ይመልከቱ

https://bunnabanksc.com/job-openings/

የቡና ባንክ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ለወዳጅ ዘመድ ያጋሩ
ድረገፅ፡ https://bunnabanksc.com/
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/BunnaBank/
ቴሌግራም፡ https://t.me/bunnabanksc
ትዊተር፡ https://twitter.com/bunna_bank
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/bunnabank/
ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/channel/UCD9Ck4n3QZNLtw5aOXbdORA
ሊንክዲን: https://www.linkedin.com/company/bunna-bank/
2.1K views11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 21:16:49
ቡና ባንክ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የኢድ አል አድሐ (አረፋ) በዓል እንዲሆንላችሁ ይመኛል!
ቡና ባንክ
የባለራዕዮች ባንክ!
5.2K views18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 14:41:40 ቡና ባንክ ደንበኞቹ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ግብር መክፈል የሚያስችላቸውን አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ተፈራረመ
• ስምምነቱ የተፈረመው ከገቢዎች ሚኒስቴር እና ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር ነው
በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከዛሬ 4 ዓመት በፊት ያበለጸገው “ደራሽ” የተሰኘ የኤሌክትሮኒክስ መላ የግብር አከፋፈል ስርዓት ከሰው ንክኪ ነጻ በሆነ መንገድ እንዲከናወን ለማስቻል ያለመ ቢሆንም እስካሁን ድረስ በዚህ ዘዴ ተጠቅመው ግብር የሚከፍሉ ግለሰቦች ቁጥር ገና ከ13 ሺህ 796 ነው።
ከ16 ሺህ ጥቂት ከፍ የሚሉ ግለሰቦች ደግሞ መረጃዎቻቸውን በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ላይ ያስገቡ ቢሆንም ገና ወደክፍያ ስርዓቱ አልገቡም። ለዚህ አንዱ ምክንያት ደግሞ የክፍያ ስርዓቱ ከባንኮች ጋር የተሳሰረ ባለመሆኑ ነው ይላሉ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ መሰረት መስቀሌ።
ይህንን የኢ-ታክስ ክፍያ አሰራር ከባንኮች ጋር ለማስተሳሰር የተጀመረውን ተግባር በሚፈለገው ፍጥነት ለማጠናቀቅ አንዱ እንቅፋት ለአሰራሩ ቀልጣፋነት አጋዠ የሚሆን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሊጂ መሰረተ ልማት ያሟሉ ባንኮች በቁጥር ጥቂት ሆነው መገኘታቸው መሆኑን ሚኒስትር ዲኤታዋ ይገልጻሉ።
ሚኒስትሯ እንዳስታወሱት እስካሁን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ ይህንን ስርዓት ተቀብለው የመተግበር አቅም ያዳበሩ ባንኮች ስምንት ሲሆኑ ከነርሱም ጋር የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈርሟል ።
እነሆ ዛሬ ደግሞ ቡና ባንክን ጨምሮ ደቡብ ግሎባል ባንክ እና እናት ባንክ ለዚህ አሰራር ብቁ ሆነው በመገኘታቸው አገልግሎቱን ለመጀመር የሚያስችላቸውን የሶስትዮሽ ስምምነት ከሚኒስቴሩ እና ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር ተፈራርመዋል።ይህ ሲጨመር እስካሁን ስምምነቱን የፈረሙት ባንኮች ቁጥር 11 ደርሷል።
በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የቡና ባንክ ቺፍ ኮርፖሬት ሰርቪስ ኦፊሰር አቶ ሙሉነህ አያሌው እንዳሉት ቡና ባንክ የፋይናንስ ስርዓቱን ዲጂታይዝ በማድረግ የሃገርን የገቢ አሰባሰብ ስርዓት ለማቀላጠፍ ሙሉ ዝግጁነት አለው።
ባንኩ ደንበኞች ጊዜያቸውን ቆጥበው ሳይጉላሉ ባሉበት ስፍራ ሆነው በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ግብር እንዲከፍሉ ለማስቻል ባንኩ የሚጠበቅበትን ሁሉ ይወጣል ነው ያሉት አቶ ሙሉነህ።
ዛሬ ሃምሌ ቀን 2014 ዓ.ም በገቢዎች ሚኒስቴር በተካሄደው በዚሁ የሶስትዮሽ ፊርማ ስነስርዓት ላይ ሌሎች ባንኮችም በዚህ ስርዓት ውስጥ ለመግባት የሚያስችላቸውን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሊጂ ስርዓት በማዘመን አሰራሩን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቧል።
ስምምነቱ የቡና ባንክ እና ሌሎች የስምምነቱ ፈራሚ ባንኮች ደንበኞች በኤሌክትሮኒክስ መላ ባሉበት ሆነው ግብር ለመክፈል የሚያስችላቸውን ዕድል ይፈጥራል።
2.7K views11:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 14:41:26
2.1K views11:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 15:41:14
አብረን ነን ?!

ባንካችሁ ቡና በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቹ በቁጥር ከሁለት ሚሊዮን በላይ ወደሆኑ ቤተሰቦቹ ለመድረስ ጠንክሮ እየሰራ ነው።

የቡና ባንክ ቤተሰቦች ደንበኞቹ፣ ባለአክሲዮኖቹ እና ሰራተኞቹ ናቸው።

ምን ያህሎቻችን ከባንካችን ጋር ነን ?

“አለን !” ያልን ይህንን ፖስት ላይክ በማድረግ አብሮነታችንን እናረጋግጥ።

ዛሬ ከኛ ጋር የሌሉትን ቤተሰቦች ደግሞ በጉዟችን እንዲቀላቀሉን ከታች ያሉትን የባንካችንን ማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ሊንኮች ሼር በማድረግ እንጋብዛቸው።
ለአብሮነታችን መጠናከር ይጠቅማል የምንለው አስተያየት ካለ ደግሞ በዚህ ፖስት ስር በሚገኘው የኮሜንት ሳጥን ውስጥ ቤተሰብነታችንን ለማጠናከር የሚያስችል ሃሳብ እንስጥ።

የባንካችን ቤተሰቦች …..አብረን ነን ?

ላይክ፣ ሼር፣ኮሜንት፣ፎሎው፣ ሰብስክራይብ፣ጆይን
https://www.facebook.com/BunnaBank
https://t.me/bunnabanksc
https://www.youtube.com/channel/UCD9Ck4n3QZNLtw5aOXbdORA
https://www.instagram.com/bunnabank/
https://twitter.com/bunna_bank
https://www.linkedin.com/bunnabank
2.6K viewsedited  12:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ