Get Mystery Box with random crypto!

ማንኛውም ሰው በደንብ በማስተዋል በማንበብ እራሱን መጠበቅ ይችላል። በመድኃኒት መልክ የሚሠሩ እ | ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን

ማንኛውም ሰው በደንብ በማስተዋል በማንበብ እራሱን መጠበቅ ይችላል

በመድኃኒት መልክ የሚሠሩ እና ለሕመም ማስታገሻ፣ ለእንቅልፍ ማስተካከያ ተብለው የተሠሩ፧ ከተሠሩበት ዐለማ ውጪ መድኃኒቶች በተደጋጋሚ እየተወሰዱ ያሉና ኅብረተሰቡ ለሱስ ጥገኝነት የሚዳርጉና እየዳረጉ ያሉት ተጠቃሽ ናቸው:


እነኚህ መድኃኒቶች በዋነኝነት የጤና ባለሙያዎችን እየጎዱና የግለሰቦች የሀብት ማከማቻ የሆኑ Narcotic (ናርኮቲክ) የሚባሉ ሲሆኑ በቅጽልና በምሥጢር ስማቸው “አውሬው” የሚባሉ በኮንትሮባንድና በሕጋዊ የግልና የከነማ ፋርማሲዎች እንዲሁም በሆስፒታሎች ውስጥ ባሉ ፋርማሲዎች በልዩ ማዘዣ፣ በደረሰኝና ያለደረሰኝ በኮንትሮባንድ በሙያተኞችና ሙያተኞች ባልሆኑት በግልና በመንግሥት ፋርማሲዎች፤

በባሙያዎች በኩል በአገሪቱ ውስጥ እየተሠራጩ ያሉ በአምፑል (በመርፌ የሚሰጡ ፈሳሽ የሚይዙ) ለአገሪቷ እጅግ አስፈላጊና ከፍተኛ የሆኑ የጤና ባለሙያዎችን (Health professionals) ከሙያ ሥነ መግባራቸው ውጪ እንዲሆኑ ከማድረጉ በላይ እየፈጀ የሚገኝ ነው።

እነዚህ መድኃኒቶች እንዴት ባለ መልኩ እየገቡ እንዳሉ፣ ከየት ወደየት እንደሚደረሱ፣ እንዴት እና በምን ደረጃ እንዲሁም መንገድ እየተሠራጩ እንዳሉ ያልተደረሰባቸው፤ በስውርና መረጃ በማጥፋት የሚሠራጩ ቊጥር አንድ ገዳይ የሆኑ መድኃኒቶች ናቸው።

ከዚህ በታች በዓለም እና በአገር አቀፍ የመድኃኒት ቊጥጥር ሕግና ሥርዐት የተዘረጋላቸው መድኃኒቶች አሉ: እነዚህን በዝርዝር መግለጡ ያስፈለገበት ምክንያት

ሕዝብ ይህን አውቆ ራሱን፣ ቤተ ሰብንና ማኅበረሰቡን ያለ አግባብ ከመጠበቀም እንዲቆጠቡ ለቊጥጥሩም አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ በማሰብ ነው::


ሳይናርኮቲክ (Narcotics)

1. ብሮማዛፓም
(Bromazepam)

2. ክሎሮዳይዛፖኤክስድ
(chiorodiazepoxide)

3. ክሎናዛፒም(clonazepam)

4. ዳዜፓም(Dazepam)

5. ሚዳዜፓም(Medazepam)

6. ኦክሲዜፓ(Oxazepam) geodg

7.ፔንታዞኪን(Pentazocime)

8.ፔንቶባርቢታል(pentobarbital)

9.ፌኖባርቤታል(Phenobarbital)

10. ቴማዛፓም(Temazepan)


ትሮፒክ (psychotropic)

1. ቴትዲን  (Pethidine)

2. ሞርፊን (Morphine)

3.ሜታዶን(Methadone)

4. ፌንታኒል (Fentanyl)

5.ኮዲን (Codeine)


ከላይ የተጠቀሱት ለከፍተኛ ሕመም ማስታገሻ ከቀዶ ጥገና በፊትና በኋላ ለሕመምተኛ የሚታዘዙና የሚሰጡ መድኃኒቶች ሲሆኑ፤ የጤና ባለሙያዎች በተለያዩ ምክንያት በተደጋጋሚ መውሰድ ከጀመሩ በራሳቸው ማቆም ይከብዳቸዋል ። ስለዚህም ከፊት ሲወስዱት ከነበሩት መጠን በላይ በተደጋጋሚና መጠኑን በመጨመር መውስዱን ስለሚቀጥሉበት በአካልና በአእምሮ ከፍተኛ ጉዳት ያደርስባቸዋል ።  ከሱሱ በቀላሉ መውጣት  በማይችሉበት ደረጃ ውስጥ ይገባሉ፣ እንዲገቡም ያደርጓቸዋል። 

በመድኃኒት ሱስ እንዴት ልንጠቃ(ልንጠመድ)
እንችላለን?


ይቀጥላል


@BiniGirmachew    @BiniGirmachew

  

ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን  የቴሌግራም ቻናል


ሼር አድረጉ በጣም በእርግጠኝነት ብዙ ቤተሰብ ትጠቀማላችሁ