Get Mystery Box with random crypto!

በሴቶች ላይ የሚደርስ የአዕምሮ ጭንቀት    ክፍል 7 የወንድ ፍቅር ማጣት ሴቶች የወንድን | ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን

በሴቶች ላይ የሚደርስ የአዕምሮ ጭንቀት

   ክፍል 7


የወንድ ፍቅር ማጣት

ሴቶች የወንድን ፍቅር ሳያገኙ መኖር እንደማይችሉ አንዳንድ አዋቂዎች ይናገራሉ። ስለሆነም ለደስታ ስሜቷ ወሳኝ ከወንድ የምታገኘው ፍቅር ነው።

ይህ ህብረተሰቡ የተቀበለው እምነት ነው። ወንድ ግን ያለ ሴት ፍቅር መኖር እንደሚችል አዋቂዎች ይናገራሉ። ለወንድ ከሴት ፍቅር ሌላ በህይወቱ ሌሎች ብዙ ነገሮች አሉት።

ይኸውም ፣ --በሥራው የሚያገኘው እርካታ ፣ በትርፍ ጊዜው የሚሠራቸው ልዩ ልዩ ነገሮች ፣ የሚጫወታቸው ወይንም የሚያያቸው እስፖርቶች ወዘተ የመሳሰሉ ናቸው። ሴት የሚያፈቅራት ፍቅረኛ ከሌላት ፣ ብዙ ጊዜ ደስታ የሌላት ፣ ያልተፈለገችና ዝቅተኛ የሆነች መስሎ ይሰማታል።

"እግዚአብሔር የኑሮ ጓደኛ የማይሰጠኝ ለምንድነው?" በማለት የሚጠይቁ ብዙ ሴቶችና ወንዶች አሉ። በዚህ ምክንያት ብዙዎች ደስታ የራቃቸውና መራራነት በልባቸው ውስጥ የሞላባቸው ይሆናሉ።

ሴት ያለወንድ መቆም እንደምትችል ፤ የራሷ ሙሉ ሰውነት ያላት መሆኗን እንድትረዳና እንድትቀበል ማድረግ ይገባል።

ወደ ሕይወቷ ምንም ዓይነት ወንድ ባይመጣ ያንን እንደ እርግማን አድርጋ መቁጠር አይገባትም።

እራሷን ሙሉ ሰው እንዳልሆነችና ያለወንድ ፍቅር መኖር እንደማትችል አድርጋ ከቆጠረች ባዶነት ይሰማታል። ይህም ስሜት ከቀጠለ ወደ አዕምሮ ጭንቀት ውስጥ ይከታታል።

ጋብቻቸው እንደጠበቁት ሳይሆን ሲቀር


#ይቀጥላል

@BiniGirmachew    @BiniGirmachew

  

ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን  የቴሌግራም ቻናል