Get Mystery Box with random crypto!

እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በ | ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ!

✥✥✥ሰኔ ፲፪ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ ብዙ #ክብር_የተሾሙበት፤ #የባሕራንን_የሞት_ደብዳቤ_ወደ_ሕይወት_የቀየረበት፤ #አፎምያን_ያዳነበት እለት ነው።✥✥✥

#እግዚአብሔርም_እንዲህ_አለው....

"ሚካኤል ሆይ ምእመናን ይለምኑሃል፤ እንሆ እኔም መታሰቢያህን ያደረጉትን የሚቻልህን ያህል ሦስት ጊዜ በእሳታውያን ክንፎችህ ተሸክመህ ወደ ሕይወት እንድታስገባቸው አዝዣለሁ።"

#ወንድሞቼ_ሆይ...
"ስለዚህ ነቅተን ተግተን የመላእክት አለቃ የከበረ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል መታሰቢያ እንደተቻለን እናድርግ።"

✟#ምልጃው ከሁላችን ጋር ይሁን፤
✟በመካከላችን #ፍቅርን_ያድርግልን፤
✟እስከ ዕለተ ሞታችንም #በቀናች_ሃይማኖት_ያጽናን።
✟ልመናው #ከሲኦል_ረግረግ_ያድነን፤
✟ከርጉም ተኩላ አፍም ያውጣን፤
✟ ከክፉ የሰይጣን ወጥመድም ያድነን።


ለዘላለሙ አሜን!

ምንጭ:-
ድርሳነ ሚካኤል ዘሰኔ
ሥዕል ቅዱስ ሚካኤል http://t.me/ethioicons