Get Mystery Box with random crypto!

ሁሉንም ጽሑፎች በኃላፊነት ስሜት ነው የጻፍኳቸው። ሁሉም ጉዳይ ተኮር እንጂ ግለሰብ ወይም ቡድን ተ | በትረማርያም አበባው

ሁሉንም ጽሑፎች በኃላፊነት ስሜት ነው የጻፍኳቸው። ሁሉም ጉዳይ ተኮር እንጂ ግለሰብ ወይም ቡድን ተኮር አይደሉም። ሲኖዶስ የቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና ካልጠበቀና ካላስጠበቀ የ60 ሽማግሌዎች ስብስብ ብቻ ነው የሚሆነው የሚለው ግልጽ አማርኛ ነው። ካልጠበቀና ካላስጠበቀ የሚል ቅድመ ሁኔታ ስላለበት ማለት ነው። ካልጠበቀና ካላስጠበቀኮ እንዲያውም የከኃድያን ጥርቅም ቢባልም ያስኬዳል። ስለዚህ ጉዳዩ ካልጠበቀና ካላስጠበቀ እንጂ ከጠበቀና ካስጠበቀማ ከእግዚአብሔር በታች አክብሩት የተባለለት ጉባኤ መሆኑን በተከታታይ በተማማርነው በሥርዓት ትምህርት ገልጸናል። ሁሉንም በደንብ ተመልከቷቸው። የሚጎረብጡ ጽሑፎች አይደሉም። ለሌባ እና ለወንበዴ ግን የማይመቹ እንደሆኑ አውቃለሁ። የተጻፉም በዋናነት ሌባው ከሌብነቱ ወንበዴ ከወንበዴነቱ እንዲመለስ ነው።

ብፁዓን አባቶቻችንን እንወዳቸዋለን። እናከብራቸዋለን። ይህ የሚሆነው ግን የቤተክርስቲያኒቱን ዶግማና ቀኖና ሲጠብቁና ሲያስጠብቁ ነው። ካልጠበቁ እና ካላስጠበቁ ግን ለእግዚአብሔር አድልተን የእነርሱን የቀኖና ጥሰት ሳንፈራ ሳናፍር በአደባባይ እንናገራለን። የተማርነው ለዚህ ነውና።