Get Mystery Box with random crypto!

እግዚአብሔርን ማመስገን ለልብ የንጽሕና ምንጭ ይሆናል። ሕይወት ሁልጊዜም ተወዳጅ የምትሆነው በምስጋ | በትረማርያም አበባው

እግዚአብሔርን ማመስገን ለልብ የንጽሕና ምንጭ ይሆናል። ሕይወት ሁልጊዜም ተወዳጅ የምትሆነው በምስጋና ስንኖር ነው። ቅዱሳን ሰማዕታት ከእሳት ሲጣሉ፣ በሰይፍ ሲቀረደዱ እግዚአብሔርን ማመስገንን ግን ትተው አያውቁም ነበር። በመከራ ውስጥም ሆነው ያመሰግኑታል። በደስታቸው ጊዜም ያመሰግኑታል። በአጸደ ሥጋ እያሉም ያመሰግኑታል። በአጸደ ነፍስም ያመሰግኑታል። ምስጋና የሚገባው ምስጋና የባሕርይው የሆነ እግዚአብሔር ነውና። ስለሁሉ ነገር እግዚአብሔርን ማመስገንን አንዘንጋ።

የቅዱሳን መላእክት ምግባቸው፣ ዕረፍታቸው ምስጋና ነው። በሀገራችንም ውሉደ ያሬድ ሊቃውንት እግዚአብሔርን ስቡሕ ውዱስ ቅዱስ እያሉ በፍቅር ያመሰግኑታል።

አቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር
እግዚአብሔርን እናመስግን።