Get Mystery Box with random crypto!

'ጸጋ ነሣእነ ወሕይወተ ረከብነ በኃይለ ጸሎቱ ለያሬድ አቡነ። ኪያከ ነአኵት ነሢአነ ጸጋ ዘእመንፈስ | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

"ጸጋ ነሣእነ ወሕይወተ ረከብነ በኃይለ ጸሎቱ ለያሬድ አቡነ። ኪያከ ነአኵት ነሢአነ ጸጋ ዘእመንፈስ ቅዱስ"

የሰው ልጅ የተፈጠረው እግዚአብሔርን እያመሰገነ በክብር ላይ ክብር እየተጨመረው ይኖር ዘንድ ነው። ሰው እግዚአብሔርን በማመስገኑ ራሱ ሰው ይጠቀማል እንጂ ለእግዚአብሔር ያሚጨምርለት ነገር የለም። እርሱ በባሕርይው ምስጉን ነውና።

ኑ ካለመኖር በቸርነቱ የፈጠረንን እግዚአብሔርን እናመስግነው።

ኑ ክረምትና በጋን፣ መዓልትና ሌሊትን እያፈራረቀ ምድር እንድታበቅል እያደረገ የሚመግበንን የሚያኖረንን እግዚአብሔርን እናመስግነው።

ኑ ብንበድል መመለሻ ንስሓን የሰጠን፣ ከሕይወት ብንራቆት እንታደስ ዘንድ ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ ብሎ የሰጠንን እግዚአብሔርን እናመስግነው።

ኑ ስለእኛ በመስቀል ተሰቅሎ ያዳነንን ኢየሱስ ክርስቶስን እናመስግነው።

በእውነት ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል።
እንኳን አደረሳችሁ።