Get Mystery Box with random crypto!

'ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ። ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ' ቅዱስ ያሬድ | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

"ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ። ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ" ቅዱስ ያሬድ። ቅዱስ ያሬድ እግዚአብሔርን በጥዑም ዜማና በረቀቀ ምሥጢር በማመስገኑ ይታወቃል። ድጓውን ስናነብ የሚነግረን ቅዱስ ያሬድ እግዚአብሔርን የሚወድ፣ ነገረ ሥጋዌንና ነገረ ሥላሴን ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ ቅዱሳኑን የሚያከብር፣ ሰባኬ ወንጌል፣ ተርጓሚ መሆኑን በሚገባ እንረዳለን። ብሉያቱን እና ሐዲሳቱን እያስማማ በዜማ ቀምሞታል። ያልተተረጎመውን ዘይቤ ዘይቤ እያለ ተርጉሞታል። የሊቁ የቅዱስ ያሬድ በረከት ይደርብን።