Get Mystery Box with random crypto!

መስክ ስለሆነ በራሱ ኃጢአት አይደለም። ሰው ካመለከው ግን እግር ኳስ ብቻ ሳይሆን እርሻም ንግድም | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

መስክ ስለሆነ በራሱ ኃጢአት አይደለም። ሰው ካመለከው ግን እግር ኳስ ብቻ ሳይሆን እርሻም ንግድም እንጀራም ዳቦም ጣዖት አምልኮ ነው። በተረፈ እግር ኳስ ተመልካች ጣዖት አምላኪ ነው የሚል ትምህርት ግን የለም። ምናልባት ከመበለቶች መጽሐፍ ከተገኘ እንጃ። የመበለት አጫዋቾችን ጠይቁ። አንዱ ስለዶሮ ብልት ይተነትናል። አንዱ ወንጌል በሚነገርበት ዓውደ ምሕረት ስለኳስ ይሰብካል። እረ ተው ጎበዝ እንዳታስቀስፉን። መጋቤ ኳስ ወቡና ወዶሮ ብልት ወእንቁላል እየሆናችሁ ስንት አመስጥሮ ያላትን ቤተክርስቲያን በእናንተ ተራ ወሬ አታሰድቧት ለማለት ያህል ነው።

ሌላው የምዕራባውያን የሆነውን ሁሉ እንደ ርኩስ መቁጠር ነውር ነው። መልካሙን መያዝ ክፉውን መተውን እንልመድ። ምዕራባውያንን መጥላትምኮ ክርስትና አይደለም። ክርስትና ሁሉንም ሰው መውደድ ነው። ለይተን ክፉ ሥራቸውን ለመጥላት እንሞክር። በአሁኑ ጊዜኮ ከእኛ አይብሱም። በሚልየን ሕዝብ የተገዳደልን እኛ ነንኮ። ከእኛም ከእነርሱም ክፉውን እንተወው። ከእኛም ከእነርሱም መልካሙን እንያዝ። በኳስ ምክንያት፣ በእርሻ ምክንያት፣ በትምህርት ምክንያት፣ እና በመሳሰሉት ከቅዳሴ መቅረት አይገባም። አንድ ሰው በእነዚህ ምክንያት ከቅዳሴ ስለቀረ ግን ትምህርት፣ እርሻ፣ ኳስ፣ ጽሕፈት ጣዖት አምልኮ ናቸው አይባልም።

ፍልጢ አርዌ ምድር___አንቺ እባብ ለዪ

መ/ር በትረማርያም አበባው